No summary available.
ሕዲር 02 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ኑን ስንታየሁ ጎዝ - ጠበቃ ሙለቀን ልመንህ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ወ/ሚካኤል - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክርን መሰረት ያደረገ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። አመልካችና ተጠሪ ባልና ሚስት የነበሩ ሲሆን የካቲት 07 ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችልት በፍቺ ውሳኔ ጋብቻው ፈርሷል። ከዚህም በሁዋላ አመልካች አይነቱንና መጠኑን በመለየት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ሲያቀርቡ ተጠሪም የጋራ ላሆን የማይችለውን ንብረት አይነቱንና ብዛቱን በመለየት ለአመልካች ክስ መልስ ከመስጠታቸው በተጨማሪ የጋራ ነው የሚለትን ንብረትም ለይተው እንዱካፈለ ይወሰን ዘንድ ገልፀው ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶና ተገቢ ነው ያለውን ሁለ አጣርቶ ጉዲዩን በመመርመር በእያንዲንደ ንብረት ላይ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ በአመልካች በኩል የጋራ እዲ ተብል በተጠቀሰው ገንዘብና አመልካች ከተጠሪ ከተለዩ በኋላ ፍቺው በፍርድ ቤት እስከሚወሰን ድረስ የወሰደትን ደመወዝ ላይ እንዱሁም አንድ አንድ ንብረቶች ላይ አመልካች የግላ ናቸው በሚል ካቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ላይ በተሰጠው የውሳኔ ክፍል ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ፍቺ ከመፈፀሙ በፉት ያገኙ የነበሩትን ገቢ እኩል ይካፈለ አመልካች ከመስሪያ ቤታቸው የተበደሩትን የብድር ገንዘብ ተጠሪን አይመለከታቸውም ተብል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ሲያፀናው የአመልካች የግል ንብረቶች መሆናቸውን ያረጋግጣቸውን ንብረቶችን ለይቶ ለአመልካች እንዱመለስላቸው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው የበታች ፍርድ ቤቶች ፍቺ ከመፈፀሙ በፉት አመልካች ያገኙት የደመወዝ ገቢ ከተጠሪ ጋር እኩል እንዱካፈለ አመልካች ከመስሪያ ቤታቸው የተበደሩት እስከ ፍቺው ጊዜ ድረስ አለመከፈለ የተረጋገጠው የብድር ገንዘብ ግን ተጠሪን አይመለከትም ተብል በተወሰነው የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካች በጠበቃቸው አማካኝነት ግንቦት 12 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ በማቅረባቸው ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታመኑ ተጠሪ እንዱቀርቡ ተደርጏ ሐምል 08 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ጠበቃም መስከረም 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ በትዲር ተሳስረው በነበረበት ዘመን ብር 265‚827.10 (ሁለት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ሰባት ብር ከአስር ሳንቲም) የፍቺ ውሳኔ ከመሰጠቱ ከአስራ አንድ አመት በፉት አመልካች ከሚሰሩበት ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የብድርና ቁጠባ ሕብረት ሥራ ማህበር ላይ በተለያዩ ጊዜአቶችና በተለየዩ የወለድ መጠኖች ወስደው ለቤት መኪና መግዣ ለተጠሪው የግል መኪና የሞተር እድሳትን ጨምሮ ለላልች እድሳቶች፣ ለተለያዩ የቤት እቃዎች ማሟያ ለባለ አንድ ፍቅ መኖሪያ ቤት መስሪያና ለላልች የቤተሰብ ወጪዎች ማሟያ አገልግልት እንደአዋለ እዲው በትዲር ዘመን ከአመልካች ደመወዝ እየተቆረጠ ሲከፈል ቆይቶ የፍቺ ውሳኔ በተሰጠበት የካቲት 07 ቀን 1995 ዓ.ም ብር 147‚852.10 (አንድ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከአስር ሳንቲም) መቅረቱ በንብረት አጣሪዎቹ ትእዛዝ ከሕብረት ስራ ማህበሩ በቀረበ ማስረጃ መረጋገጡን አመልካች ገልፀው የሚከራከሩ መሆኑን ተጠሪ የብድር ገንዘቡን እንደማያውቁት እና በአመልካች ለተጠቀሱት ነገሮች ያልዋለ ለትዲር ጥቅም ስለመዋለ ያልተረጋገጠ መሆኑንና ቤቱ የተሰራውም ከባንኩ ያጠራቀሙትን ገንዘብ ወጪ አድርገው መሆኑን ገልፈፀሙ ለእዲው ኃላፉነት የለብኝም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ነው። ይሁን እንጂ ብድሩ በአመልካች ከመስሪያ ቤቻው ስለመወሰደም ሆነ በትዲር ዘመን ከአመልካች ደመወዝ እየተቆረጠ ሲከፈል ቆይቶ እስከፍቺው ውሳኔ ጊዜ ድረስ ቀሪ ያልተከፈለ እዲ ያለ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ነገር ነው። የስር ፍርድ ቤት እዲው የጋራ ልባል የሚችል አይደለም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው አመልካች ከመስሪያ ቤታቸው የተበደሩትን ገንዘብ በስማቸው ወይም ከተጠሪ ጋር በጋራ በባንክ ስለማስቀመጣቸው አላስረደም፣ በአቢሲኒያ ባንክ ገነት ቅርንጫፍ እና ቦላ ቅርንጫፍ ከሚገኘው ሂሳብ ከመጋቢት 04 ቀን 1991 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 27 ቀን 1994 ዓ.ም ድረስ 151‚651.74 (አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ አንድ ብር ከሰባ አራት) ወጪ መደረጉ መረጋገጡ ቤቱ የተሰራውና ለተለያዩ አገልግልት የሚውል ብድር ወስደናል በማለት አመልካች የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የላለው መሆኑን እንዱሁም አመልካች በብድር የወሰደትን ገንዘብ በአቤቱታቸው ለዘረዘሯቸው ነገሮች መግዣ መዋላቸውን አላስረደም በሚል ምክንያት ነው።
እኛም ጉዲዩን ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል። በዚህም መሰረት በአዋጁ አንቀጽ 68(መ) ስር እንደተመለከተው በልላ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር ከብር አምስት መቶ በላይ ለመበደር ወይም ለማበደር ወይም ለላላ ሰው ዋስ ለመሆን የተጋቢዎች ስምምነት የግድ ያስፈልጋል። የስምምነት አለመኖር ስለሚያስከትለው ውጤትም ሕጉ በአንቀጽ 69 ስር ያስቀመጠ ሲሆን የተጠቀሰው አንቀጽ ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ አንደኛው ተጋቢ በአንቀጽ 68 ስር የመለከተውን ባለማክበር የውል ግዳታ ገብቶ የተገኘ እንደሆነ ላላኛው ተጋቢ ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው ጥያቄ ግዳታው ሉፈርስ እንደሚችል፣ በንዐስ ቁጥር ሁለት ደግሞ የይፍረስልኝ ጥያቄ ጠያቂው ወገን ግዳታው መግባቱን ከአወቀበት ቀን ጀምሮ ከስድስት ወር በኋላ ወይም በልላ በማናቸውም ሁኔታ ግዳታው ከተገባ ከሁለት ዓመት በኋላ ላቀርብ እንደማይችል ተደንግጓል። ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ብድሩን ከተጠሪ ጋር ፈርመው ወስደዋል ባይባልም ብድሩ ትዲሩ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ከመስሪያ ቤታቸው ተወስድ ከአስራ አንድ አመታት በላይ ከአመልካች ደመወዝ እየተቆረጠ ሲከፈል የነበረ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ብድሩ ከአመልካች ደመወዝ እየተቆረጠ ሲከፈል የነበረ መሆኑ ሲታይ ደግሞ ተጠሪ ስለብድሩ እውቅና አልነበራቸውም ለማለት የሚቻል አይደለም። በመሆኑም ብድሩ ስለመኖሩ ተጠሪ ያወቁ እንደነበር የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳያል። አከራካሪው ጉዲይ ብድሩ ለትዲር ጥቅም የዋለ መሆን አለመሆኑ ላይ ነው። ብድሩ በትዲር ወቅት የተወሰደ መሆኑ ከተረጋገጠ የሕግ ግምት ለትዲር ጥቅም የዋለ መሆኑን ያሳያል። ይኸው የሕግ ግምት ሉስተባበል የሚገባው ገንዘቡ ለትዲር ጥቅም አልዋለም ብል በሚከራከረው ተጋቢ ነው። ይህ ስለመሆኑም ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 71 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በመሆኑም ተጠሪ ቤት ለመስራት ወይም ለቤተሰቡ የተለያዩ ወጪዎች ብድሩ አለመዋለን የማስረዲት ሸክም ባልተወጡበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች ለቤት መስሪያ በልላ ባንክ ገንዘብ የነበረ መሆኑ ተረጋጋጧል በሚል ምክንያት ብቻ ተጠሪ ትዲር ከመፍረሱ በፉት አስራ አንድ አመታት በፉት ከመስሪያ ቤታቸው የወሰደትን የብድር ገንዘብ ከወርሃዊ ደመወዝ እየከፈለ ቆይተው ተጠሪ ምንም ተቃውሞ ባላነሱት ሁኔታ ብድሩ የጋራ ላሆን አይገባም ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሁኖ አግኝተናል።
ላላው አመልካች ፍቺ በፍርድ ቤት ከመወሰኑ በፉትና ከተጠሪ ጋር አብሮ መኖር ትተው በግላቸው ሲኖሩ በነበሩበት ጊዜ ያገኙት ደመወዝ የጋራ ገቢ ነው ተብል የመወሰኑን አግባብነት ተመልክተናል። በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 62(1) መሰረት ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች ሁለ የጋራ ሃብቶቻቸው እንደሚሆኑ የተደነገገ ሲሆን ከግል ጥረት ከሚገኙት ገቢዎች አንደ ደመወዝ መሆኑ ይታመናል። ሕግ አውጪው ደመወዝ የተጋቢዎች የጋራ ሀብት ነው በማለት የደነገገው የትዲርን ወጪ ለመሸፈን ሲሆን የትዲር ወጪን ደግሞ ተጋቢዎች እያንዲንዲቸው እንደ የአቅማቸውና ችልታቸው አስተዋጽኦ የማድረግ ግዳታ ያለባቸው መሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 72 ስር ከመመልከቱም በላይ በገቢው መፈጠር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ላላው ተጋቢም አስተዋጽኦ አለው ተብል የሚታሰብ መሆኑ እሙን ነው ለዚህም ምክንያቶች ደመወዝ የተጋቢዎች የጋራ ሃብት ነው ተብል በሕጉ ከተመለከተ ምላሽ የሚያስፈልገው ጥያቄ ፍቺው ከመፈፀሙ በፉት ተጋቢዎች ተለያይተው በኖሩበት ወቅት የተገኘ ደመወዝ የጋራ ነው ተብል ሉወሰድ ይገባል ወይ የሚው ነጥብ ነው። የሕጉ ዓላማ ከላይ የተመለከተው ከሆነ ተጋበዎች ተለያይተው በነበሩበት ጊዜ የተጠሪ ደመወዝ ለቀለቡ ጥያቄ በሕጉ አግባብ ከሚስተናገድ በስተቀር እንደላላው ሀብት የጋራ ነው ተብል የሚወሰድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ከዚህም ምክንያት የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የሰጡት ውሳኔም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፍቺ ውሳኔ ከመሰጠቱ ከአስራ አንድ አመታት በፉት ጀምሮ ንብረት ማፍሪያና ለትዲር ጥቅም የተወሰደውን ብድር ተጠሪው የጋራ እዲቸው መሆኑ ያውቁ የነበረ በመሆኑ እስከፍቺው ውሳኔ ድረስ አለመከፈለ የተረጋገጠውን ብር 147‚852.10 (አንድ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከአስር ሳንቲም) ግማሽ ብር 73‚926.05 (ሰባት ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ስድስት ብር ከዜሮ አምስት ሳንቲም) ለአመልካች እንዱተኩ ብለናል።
አመልካች ከተጠሪ ተለይተው ከቤት ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ካገኙት ደመወዝ ለተጠሪ ግማሹን የሚከፍለበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.