No summary available.
ህዲር 2 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ዘነበች በቀለ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዮናስ ፀጋዬ - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጋብቻ መመስረት አለመመስረትን በተመለከተ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ ከአሁኗ አመልካች ጋር ህዲር 03 ቀን 1998ዓ.ም በአገር ባህል መሰረት ጋብቻ ፈጽመው ሲኖሩ ልጅ አለመውለዲቸውን፣ የጋራ ንብረት ግን ያፈሩ ቢሆንም ተጠሪ የጋራ ንብረት እያሸሸች በመሆኑ አብሮ መኖር እንደማይችለ ገልፀው ፍቺ ተወስኖ የጋራ ንብረት የመጠየቅ መብታቸው እንዱጠብቅላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኗ አመልካችም ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስ ጋብቻው የተፈፀመው ተጠሪ በገለፁት ህዲር 3 ቀን 1998ዓ.ም ሳይሆን ታህሳስ 21 ቀን 2001ዓ.ም መሆኑን ገልጸው ያለምንም ማሰላሰያ ጊዜ ፍቺ ቢወሰን ግን ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና የሰነድ ማስረጃ በመመርመር ጋብቻው የተፈፀመው በተጠሪ በተገለፀው ህዲር 3 ቀን 1998ዓ.ም መሆኑን በመደምደም ጋብቻው እንዱፈርስ ወስኖ የግራ ቀኙን የጋራ ንብረት ዝርዝር የማቅረብ መብት በመጠበቅ ወስኗል። አመልካች ጋብቻው ህዲር 3 ቀን 1998ዓ.ም ተፈጸመ ተብል በተሰጠው የውሳኔ ክፍል ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የውሳኔ ክፍል ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ምክንያት ጊዜውን ለማስለወጥ ነው። አመልካች በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት መጋቢት 20 ቀን 2002ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም በአመልካችና በተጠሪ መካከል በ03/03/1998ዓ.ም የባህል ጋብቻ መፈፀሙን ያረጋግጣል የተባለው አመልካች ያልተሳተፈችበት ሰነድ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 27 መሰረት የባህል ጋብቻ የተፈፀመ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ መሆን ያለመሆኑ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ሐምል 08 ቀን 2002ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሳቸውን የሰጡ ሲሆን አመልካችም መስከረም 10 ቀን2002ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መሰረት ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካችና በተጠሪ መካከል የባህል ጋብቻ ህዲር 03 ቀን 1998ዓ.ም ስለመፈፀሙ ያረጋግጣል የተባለው ከድሬደዋ 02 ቀበላ ስለመቅረቡና በ20/04/2001ዓ.ም ተጠሪ ብቻቸውን ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ስለመሰጠቱ የተረጋገጠው ሰነድ መሆኑን ነው። አመልካች ጋብቻው መፈፀሙን ያሳያል የሚለት ሰነድ ደግሞ ግራ ቀኙ በተገኙበት በድሬደዋ አስተዲደር ከተማ ስ/አ/ጽ/ቤት በ21/04/2001ዓ.ም መመዝገቡን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ስለመሆኑም ተገንዝበናል።
በመሰረቱ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 መሰረት ለጋብቻ መኖር ቀዲሚና ዋናው ማስረጃ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ሲሆን ይህ ሰነድ ጋብቻው በተፈፀመበት እለት ወይም ከዚያ በኋላ በክብር መዝገብ ሹም የሚሰጥ፣ ስለጋብቻው መፈፀም ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። ሕጉ ምዝገባው በክብር መዝገብ ሹም ፉት ለተፈፀሙ ጋብቻዎች ብቻ ሳይሆን በሐይማኖት ወይም በባህል ስርዓት ለተፈፀሙ ጋብቻዎች ሁለ ተፈፃሚነት እንዲለው ያሳያል። በመሆኑም በየትኛውም ስርዓት ጋብቻ ቢፈፀም የጋብቻ ምስክር ወረቀት ይኖረዋል ተብል ይታመናል። የጋብቻ መፈፀሙ ምዝገባ ስርዓት በክብር መዝገብ የሚከናወነው በሕጉ በልዩ ሁኔታ ከተገለጹት ሁኔታዎች ውጪ ተጋቢዎች ባለበት ጊዜና ቦታ ነው ተብልም ይታሰባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ አመልካች ጋር ጋብቻ በባህላዊ መንገድ ስለመፈፀማቸው የሚያረጋግጠው እና በሕጉ አግባብ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ የሚያሳየው ጋብቻው ታህሳስ 21 ቀን 2001ዓ.ም መፈፀሙን ነው። ይህ ሰነድ ጋብቻው ከዚህ በፉት የተፈፀመ /ህዲር 3 ቀን 1998ዓ.ም/ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 30/ሐ/ ድንጋጌ አነጋገር መሰረት ይገልፃል። እንዱህ ከሆነ ጋብቻው ውጤት አለው የሚባለው ምዝገባ ከተወናወነበት ጊዜ ሳይሆን ከህዲር 03 ቀን 1998ዓ.ም ጀምሮ ነው። ይህም በአዋጅ አንቀጽ 28/3/ ድንጋጌ ስር በግልጽ የተመለከተ ጉዲይ ነው። በመሆኑም አመልካችና ተጠሪ በባህላዊ የፈፀሙት ጋብቻ ስለመኖሩ ታህሳስ 21 ቀን 2001ዓ.ም በተሰጠው የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተረጋገጠ በመሆኑ እና ይህንኑ የሚያስተባብል ማስረጃም አመልካች ያላቀረቡ መሆኑን የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በግልጽ የሚያሳይ ሆኖ ስለተገኘ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
1/ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
2/ በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.