No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 15 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ አቶ ሐዱስ ዓለመስላሴ - ጠበቃ ጌታቸው ውብሸት ቀረቡ ተጠሪዎች፡- ወ/ሮ ብላኔ ዓለመስላሴ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው ይግባኝ መነሻ የሆነው ጉዲይ ኑዛዜን መሰረት በማድረግ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ነው። የአቤቱታው ይዘትም የአሁኑ አመልካቾች እናት ሐምል 30 ቀን 1986 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካቲት 27 ቀን 1990 ዓ.ም መጽደቁን ገልፀው ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም በማለት ኑዛዜው እንዱፈርስላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካቾችም ለክሱ በሰጡት መልስ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም ተጠሪ ክስ ለመመስረት መብት ወይም ጥቅም የላቸውም ኑዛዜውን ለመቃወምም ይርጋ ያግዲቸዋል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲያቀርቡ በፍሬነገር ደረጃም ተገቢ ነው ያለትን ክርክር አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤትም ተጠሪ ኑዛዜውን የተቃወሙት ኑዛዜው ከተደረገ ከአስራ ሁለት አመታት በሁዋላ ስለሆነና ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 974(2) ድንጋጌ ተቀባይነት የላለው ነው በሚል ምክንያት አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጏታል። በዚህ ብይን የአሁኗ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የተጠሪ ጥያቄ ኑዛዜው የተደረገው መብት በልላቸው ንብረት ስለሆነ ይፍረስልኝ የሚል በመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 974 ለጉዲዩ አግባብነት የለውም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ብይን በመሻር በላልች ነጥቦች ላይ አከራክሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት መልሶለታል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
እኛም የአመልካቾች ጠበቃ የካቲት 18 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካቾች ከስር ጀምረው አቅርበው ሲከራከሩበት የቆዩት የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ የተደረገበትን አግባብ ለመመርመር ነው።በዚህ መሰረትም ይህ ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የስር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ እንደተመለከተው አከራካሪው ኑዛዜ የተደረገው ሐምል 30 ቀን 1986 ሲሆን ተጠሪ ኑዛዜውን በመቃወም አቤቱታ ያቀረቡት ሕዲር 19 ቀን 1999 ኑዛዜ ከተደረገ ከ12 /አሥራ ሁለት/ አመት በኋላ ነው። ይሁን እንጂ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ የኑዛዜው አድራጊ ወራሽ ስለሆንኩ ኑዛዜው መብቴን /ጥቅሜን/ ነክቷል ይስተካከልልኝ ሳይሆን ኑዛዜው የተደረገው በተናዛዡ ንብረት ላይ ብቻ ሳይሆን በልላ ሰው ሀብት (በተጠሪ አውራሽ ሀብት) ጭምር ነው ኑዛዜው ተፈጻሚነት የለውም በሚል ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ ተገልጾአል።
ኑዛዜን በመቃወም የሚቀርብ ማንኛውም መቃወማያ መታየት ያለበት አግባብነት ካላቸው የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች አንፃር ነው። የአመልካቾች ጠበቃ ለጉዲዩ አግባብነት አለው በማለት ከሚጠቅሱት ድንጋጌዎች አንደ በፍ/ብ/ሕግ ቁ.973 የተመለከተው ነው። ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል መቃወሚያ ያላቸው ኑዛዜው ሲነገር /ሲፈስ/ የነበሩትን ሰዎች የሚመለከት ነው።
ይህም ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከለ ሰዎች ኑዛዜው አይፀናም ወይም በኑዛዜው የተነገረ ቃል አይፀናም የሚለትንና የመሳሰለትን በመቃወም ክስ የሚያቀርቡ ሲሆን ይህን ማድረግ ያለባቸው ኑዛዜው ከተነበበት አንስቶ እስከ አስራ አምስት ቀን ድረስ እንደሆነ ያመላክታል። ከዚህም በተጨማሪ ክስ የማቅረብ ሃሣብ መግለጫው በጽሐፍ ካልሆነና ለአጣሪው ወይም ለዳኞች ወይም በውርስ ላይ የተነሣውን ነገር ለመጨረስ ለተመረጡት የሽምግልና ዳኞች እንዱደርስ ካልተደረገ በቀር እንደማይፀና /መቃወሚያ አለ ለማለት እንደማይቻል/ በዚሁ ቁጥር 973/2/ ስር ተደንግጓአል።
በመጨረሻም መግለጫው ከተሰጠበት ቀን አንስቶ እስከ ሦስት ወር ድረስ ክስ ካልቀረበ መብቱ ከነጭራሹ እንደሚቀር በንኡስ ቁጥር /3/ ተመልክቶአል። በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 974/2/ በግልጽ እንደተመለከተው ኑዛዜው ከፈሰሰበት /ከተነበበት/ ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለኑዛዜው መጽናትም ሆነ ስለክፍያው ድልድል መቃወሚያ ማቅረብ አይቻልም። እነዚህ ድንጋጌዎች በግልጽ የሚያሳዩት ስለወራሾች መቃወሚያ አቀራረብና የጊዜ ገደቡ ነው እንጂ ወራሽ ያልሆነ ሰው ስለኑዛዜ የሚቃወምበትን የጊዜ ገደብ አይደለም።
No topics extracted.
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው ተጠሪ የኑዛዜ አድራጊ ወራሽ አይደለም መቃሚያ ያቀረቡት በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 973 በግልጽ የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ እንዲልሆነም ተረጋግጧል።
በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973 እና 974 ድንጋጌዎች ለጉዲዩ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ተፈጻሚነት የላቸውም። ሲጠቃለል ተጠሪ የወ/ሮ የሸዋዘርፍ ዓለማየሁ ወራሽ ነኝ ኑዛዜ ሲነበብ /ሲፈስ/ አልነበርኩም ወይም አልሰማሁም በማለት ክስ ባላቀረቡበት ሁኔታ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973 እና 974 ድንጋጌዎች መሰረት ሁነው ተቃውሞአቸው በይርጋ ቀሪ ነው ልባል የሚችልበት የሕግ አግባብ የላለ በመሆኑ በዚህ ረገድ በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በመ. ሕዲር 27 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ የዚሁ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሕዲር 19 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348/1/ መሰረት ጸንተዋል።
ተጠሪ በኑዛዜው ላይ ያቀረቡት መቃወሚያ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።