No summary available.
ጥቅምት 2 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሪት ሮማን ግዛው - ጠበቃ አቶ ግርማ ተጠሪ፡- አቶ ግርማ አብርሃም - ጠበቃ አቶ አምዳ አበበ - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ችልትና የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ስላመለከቱ ነው። የጉዲዩ መነሻ ሟች ወ/ሮ አስካለ ወልደየስ መስከረም 1ዐ ቀን 1993 ዓ.ም. አመልካችን ኑዛዜ ወራሽና ተጠቃሚ የሚያደርግ ኑዛዜ አድርገዋል። የሟች የኑዛዜ ወራሽ መሆኔ ይታወቅልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ በመመርመር አመልካች የሟች ወ/ሮ አስካል ወልደየስ የኑዛዜ ወራሽ መሆኗን በማረጋገጥ የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካቲት 21 ቀን 1997 ዓ.ም. ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ ይህንን ፍርድ በመቃወም የሟች የወንድም ልጅ የሆንኩት እኔ እያለሁ አመልካች የኑዛዜ ወራሽ ነኝ በማለት በፍርድ ያስወሰነችው አላግባብ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ሟች በአመልካች ያደረጉትን ኑዛዜ ጥቅምት 9 ቀን 1997 ዓ.ም. ባደረጉት ኑዛዜ ተክተውታል በማለት የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ አቅርቧል። በተጨማሪም ኑዛዜውን ሟች ያላደረጉት ነው የሚል መከራከሪያም አቅርበዋል።
አመልካች በበኩላቸው ተጠሪ ሟች ያደረጉትን ኑዛዜ ያውቃለ በኑዛዜው መሰረት ለላልች ሰዎች ሲፈፀም በምስክርነት ተገኝተዋል። ፊርማው የሟች ነው። ዋናው የሚገኘው በልላ ሰው እጅ በአደራ ተቀምጦ ነው በማለት ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት የኑዛዜ ዋና ቅጂ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ የአመልካች የኑዛዜ ወራሽነት ማመልከቻ ተቀብል በሚያጣራበት ሰዓት ቀርቦ ከኮፑው ጋር የተገናዘበ መሆኑን ኮፑው ላይ ዲኛ አረጋግጦ የፈረመበት መሆኑን በመተቸትና በአሁኑ ወቅት ዋናው አለመቅረቡ የፕሉስ ምርመራ ባይደረግም ማስረጃ ተዓማኒነት ያለውና ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ነው። ሟች ጥቅምት 9 ቀን 1997 ዓ.ም. ያደረጉት ኑዛዜ በፉት ካደረጉት ኑዛዜ የተለየና ሟች ለአመልካች ያደረጉትን ኑዛዜ ጋር የማይቃረንና የማይተካ ነው በማለት የተጠሪን የፍርድ መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ ኑዛዜውን በመቃወም የሟች ፊርማ እንዲልሆነ ገልፆ ሲከራከር ፊርማውን ለማስመርመር ዋናው ኮፑ ሲፈለግ አመልካች ሉያቀርቡ አልቻለም። ስለዚህ አመልካች ዋናውን ኑዛዜ በማቅረብ ትክክለኛነቱን ማስረዲት ስላልቻለ ኑዛዜው ሕጋዊ ተቀባይነት የለውም በማለት የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሯል። አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው የሰበር ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ወስኗል።
አመልካች እኔ የሟች የኑዛዜ ወራሽ መሆኔን ባመለከትኩበት መዝገብ የኑዛዜው ዋና ኮፑ ከቀረበው ፍቶ ኮፑ ጋር ተገናዝቦ ትክክለኛነቱ ምልክት ተደርጎበት ምስክሮችን አስመስክሬ ውሣኔ ተሰጥቷል። ተጠሪ የፍርድ መቃወሚያ ያቀረቡት ይህ ሁለ ሂደት ሲከናወን እያወቁ ቆይተው ነው።
ዋናው ኮፑ አንድ ጊዜ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ከታየ ከተረጋገጠ በኋላ መጥፊቱ ኑዛዜውን ለማስረዲት የሚችል ማስረጃ የለሽም የሚያስብል አይደለም። ኑዛዜው የሟች ኑዛዜ መሆኑ በሰው ምስክሮች ተረጋግጧል። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ለሕጉ የተዛባ ትርጉም በመስጠት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች ያቀረቡት ፍቶ ኮፑ በሬጅስትራር ቀርቦ መረጋገጡን አያመለክትም። ዋናውን ሰነድ ለማስቀረብ የተሰጠውን ተደጋጋሚ ትዕዛዝ አመልካች ሉፈጽሙ አልቻለም። ስለዚህ አመልካች በሕግ በተደነገገው መሰረት የኑዛዜውን ዋና ኮፑ በማቅረብ ለማስረዲት ስላልቻለ የበታች ፍርድ ቤቶች ኑዛዜው በሕግ ፉት ውጤት የለውም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልሰ ሰጥተዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የአዱስ አበባ ከተማ የሰበር ችልት አመልካች የኑዛዜ ወራሽና ተጠቃሚ መሆኗን የኑዛዜውን ዋናውን ሰነድ አቅርባ ባለማስረዲቷ ኑዛዜው ፈራሽ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ ይዘናል።
No topics extracted.
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን ኑዛዜውን የማስረዲት ሸክም ስላለበት ወገንና ኑዛዜውን ለማስረዲት ሉቀርቡ ስለሚገቡ ማስረጃዎች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 896 እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 897 የተደነገገውን ማገናዘብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። ኑዛዜ መኖሩንና በኑዛዜው የሰፈረውን ቃል የማስረዲት ግዳታ ያለበት የኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሰው መሆን እንዲለበት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 896 ይደነግጋል። የኑዛዜ ተጠቃሚው መብቱን ያገኘው በግልጽ ወይም በተናዛዥ ጽሁፍ በተደረገ ኑዛዜ በሆነ ጊዜ የኑዛዜውን መኖር ለማረጋገጥ የኑዛዜውን ጽሁፍ ዋናውን ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ሹም ትክክለኛ ሆኖ የተመሳከረ ግልባጭ በማቅረብ እንደሆነ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 897 ንዐስ አንቀጽ 1 የሚደነግግ ሲሆን ኑዛዜዎቹን ለማስፈፀም በማናቸውም ላላ መንገድ ማስረዲት እንደማይቻል የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 897 ንዐስ አንቀቀጽ 2 ይደነግጋል።
አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሟች ወ/ሮ አስካለ ወልደየስ መስከረም 1ዐ ቀን 1993 ዓ.ም. ያደረጉት ኑዛዜ ተጠቃሚና ወራሽ መሆኗን አረጋግጦ እንዱወስንላት ስታመለክት የኑዛዜው ዋና ሰነድ በወ/ሮ ንግሥት መታፈሪያ እጅ መሆኑን ገልፀው ፍርድ ቤቱ ዋናውን በማስቀረብ እንዱመለከተው በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 223 መሰረት የካቲት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ባቀረቡት የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ጠይቀዋል። የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤትም የኑዛዜው ዋና ሰነድ ለየካቲት 15 ቀን 1997 ዓ.ም. እንዱቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ የካቲት 15 ቀን 1997 ዓ.ም. የኑዛዜው ዋና ሰነድ ቀርቦ የታየና የተረጋገጠ መሆኑን በኮፑው ጀርባ የዲኛ ፊርማ የተፈረመበት ሲሆን ዋናው የኑዛዜ ሰነድ የቀረበውም ፍርድ ቤቱ የኑዛዜውን ዋና ሰነድ እንዱቀርብ ትዕዛዝ በሰጠበት የካቲት 15 ቀን 1997 ዓ.ም. መሆኑን ይህ የሰበር ችልት በትዕዛዝ ካስቀረበው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመ/ቁ. 1185/97 ለመገንዘብ ችለናል።
ከዚህ በተጨማሪ የኑዛዜው ዋና ሰነድ በእጃቸው የነበረው ወ/ሮ ንግሥት መታፈሪያ ለፍርድ ቤት በምስክርነት ቀርበው ሟች ኑዛዜ ያደረጉ መሆኑን የመሰከሩ መሆኑን መዝገቡ ያስረዲል።
ተጠሪ የፍርድ መቃወሚያ ባቀረበበት ጊዜ ወ/ሮ ትዕግሥት የኑዛዜውን ዋና ሰነድ ለፍርድ ቤት ያቀረቡ መሆኑና ዋናው ሰነድ እንዲልተመለሰላቸው የገለጹ መሆኑን የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ችልት በውሣኔው ገልፆታል።
ከዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አመልካች የኑዛዜ ተጠቃሚና ወራሽ መሆኗን ለማስረዲት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 897 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት ዋናውን የኑዛዜ ሰነድ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተረጋጠውን በማቅረብ አስረድታለች ወይስ አላስረዲችም የሚለው ነው። ሟች ወ/ሮ አስካለ ወልደየስ ኑዛዜ ያደረጉት በሁለት ኮፑ እንደሆነና አንደኛው ኮፑ በወ/ሮ ንግሥት መታፈሪያ ሁለተኛው በአባ ማሞ አርጋው እጅ መቀመጥ እንዲለበት በኑዛዜው የገለጹ መሆኑን ሰነደ ያሣያል። የኑዛዜው ዋና ሰነድ ወ/ሮ ንግሥት መታፈሪያ እጅ የነበረና በልላ ሰው እጅ የካርቦን ኮፑው የነበረ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች የኑዛዜ ወራሽነቷን የሚያረጋግጥላት ሰነድ በወ/ሮ ንግሥት መታፈሪያ እጅ እንደሚገኝ በማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ላይ በመግለጽ ወ/ሮ ንግሥት መታፈሪያ ዋናውን ሰነድ ለፍርድ ቤት የካቲት 15 ቀን 1997 ዓ.ም. እንድታቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ የካቲት 17 ቀን 1997 ዓ.ም. ዋናው ሰነድ ቀርቦ ከዋናው ጋር የተረጋገጠ መሆኑ በኮፑው ጀርባ ዲኛ ጽፍ የፈረመበት በመሆኑ አመልካች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 897 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት የኑዛዜውን ዋና ሰነድ በማቅረብ አላስረዲችም በማለት የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የሰበር ችልት የሰጡት የሕግ ትርጉም ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። አመልካች ዋናው የኑዛዜ ሰነድ በአደራ ይዘውት በነበሩት ሴት በኩል ቀርቦ ትክክለኛነቱ በዲኛ ከታየና ከተረጋገጠ በኋላ ተጠሪ ተቃውሞ ሲያቀርብ ይህ ሰነድ አለመቅረቡና መጥፊቱ አመልካች ኑዛዜ መኖሩን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 897 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት አላስረዲችም ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። ተጠሪ ፊርማውን የካደ ቢሆንም በግልጽ ኑዛዜው ሲደረግ የነበሩ ምስክሮች ኑዛዜው ላይ የሟች መሆኑን ገልፀው የመሰከሩና የኑዛዜ ሰነደም በአመልካች እጅ ሣይሆን በልላ ሰው እጅ በአደራ ተቀምጦ የቆየ መሆኑን በማገናዘብ ኑዛዜው የሟች ኑዛዜ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤት የደረሰበትን መደምደሚያ የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 897 ንዐስ አንቀጽ 1 የተዛባ ትርጉም በመስጠት መሻራቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ችልትና የአዱስ አበባ ከተማ የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል
አመልካች ሟች መስከረም 1ዐ ቀን 1993 ዓ.ም. ያደረጉት ኑዛዜ ተጠቃሚና ወራሽ ናት ብለናል።
በትውስት የመጣው መዝገብ ይመለስ።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።