No summary available.
ጥቅምት 4 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ቀለሟ ወርቅነህ ሺበሺ ተጠሪ፡- ሻምበል ጌታሁን ገብሬ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የሟች እህትዋ ወራሽ መሆንዋን መሰረት በማድረግ ያቀረበችው የውርስ ንብረት የመካፈል ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል በማለት ውድቅ በመደረጉ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ከተጠሪ የቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ በመቀበል እና በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1ዐዐዐ/1/ የተቀመጠውን የሦስት ዓመት የጊዜ ወሰን መሰረት በማድረግ ክሱን ውድቅ አድርጎአል። አመልካች ውሣኔውን በመቃወም ለፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ብታቀርብም፤ ውሣኔው ጉድለት የለበትም ተብል ይግባኙ ተሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች መስከረም 21 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ አቤቱታ ባቀረበችበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የምትልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱን የሚያርም ውሣኔ ይሰጥላት ዘንድ ጠይቃለች። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የተባለው በአግባቡ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በዚህ መሰረትም ግራ ቀኝ ወገኖች ጭብጡን በማስመልከት ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው አመልካች ክስ የመሰረተችው የወራሽነት መብትን መነሻ በማድረግ ነው። ለክሱ ምክንያት የሆነው ንብረት ባለሃብት ነበረች የተባለችው የአመልካች እህት የሞተችው መጋቢት 11 ቀን 88 ዓ.ም ሆኖ አመልካች የውርስ ንብረቱ እንዱሰጣት ክስ የመሰረተችው ደግሞ ጥር 26 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም እንደሆነ ከመዝገቡ ተመልክተናል። ተጠሪ የይርጋ መቃወሚያ ያቀረበው ከዚህ በመነሣት ሲሆን፣ የሥር ፍ/ቤቶችም ተመሣሣይ ምክንያት በመስጠት ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል በማለት ወስነዋል። አመልካች ግን ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ ትክክል አይደለም በሚል ክርክርዋን በመግፊት የሰበር አቤቱታ አቅርባለች። በዚህ ረገድ የሰጠችው ምክንያት ሟች እህቴ የተወችልኝን ኑዛዜ በፍ/ቤት ሳላስፀድቅ በውርስ ንብረቱ ላይ ጥያቄ ማንሣት አልቻልኩም ነበር።
ስለዚህም ኑዛዜው እንዱፀድቅልኝ ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቤ ስከራከር ከቆየሁ በኋላ ሲፀድቅልኝ በንብረቱ ላይ ክስ መሥርቻለሁ የሚል ነው። ተጠሪ ኑዛዜው መጽደቅ የለበትም በማለት ሲከራከራት እንደቆየም በአቤቱታዋ የገለፀች ሲሆን፣ ተጠሪም ይህ እውነት አይደለም የሚል መልስ ወይም ክርክር አላቀረበም።
ከቀረበው ክርክር እንደምንገነዘበው በእርግጥ አመልካች በንብረቱ ላይ ክስ የመሰረተችው ሟች ከሞተች ከአሥራ ሦስት /13/ ዓመት በላይ ቆይታ ነው። ነገሩ ከዚህ ሁኔታ ብቻ በመነሳት ሲታይ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል ለማለት ይቻላል። ኑዛዜውን በፍ/ቤት ሣላስፀድቅ በውርስ ንብረቱ ላይ ክስ መመሥረት አልችልም ነበር የሚለው ክርክርም እንዲለ በቀጥታ ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም። ኑዛዜው እስካለ ድረስ ወይም አመልካች የሟች እህት ነኝ እስካለች ድረስ በንብረቱ ላይ በቀጥታ መክሰስ እየቻለች ኑዛዜ በፍ/ቤት አስፀድቃለሁ በማለት ጊዜዋን ካሣለፈች ይርጋን በተመለከተ ለቀረበበት መቃወሚያ መከራከሪያ አድርጋ ልታቀርበው አትችልም። ኑዛዜው ዋጋ የሚኖረው በፍ/ቤት ስለፀደቀ ሣይሆን በሕግ የተቀመጡትን የኑዛዜ መሰረቶች ወይም መስፈርቶች ሲያሟላ ነው። ይህ የሰበር ችልትም ከዚህ በመነሣት ኑዛዜ ለፍ/ቤት ቀርቦ መጽደቅ በኑዛዜው ሕጋዊነት ላይ የሚጨምረው ነገር የለም በማለት ቀደም ሲል በሰጣቸው ውሣኔዎች ለሕጉ ትርጉም ሰጥቶአል። በመሆኑም ኑዛዜውን በፍ/ቤት ሳላስፀድቅ በውርስ ንብረቱ ላይ ክስ መመሥረት አልችልም ነበር የሚለው የአመልካች ክርክር በሕግ ረገድ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ይህ እንዲለ ሆኖ ግን በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተነሣው ክርክር ከላላም አቅጣጫ መታየት እንደለበት ከክርክሩ አመጣጥ እና ልዩ ባህርይ ለመገንዘብ ችለናል።
ቀደም ሲል እንዲመለከትነው የኑዛዜውን መጽደቅ በተመለከተ በቀረበው አቤቱታ ተጠሪም ተካፊይ እንደነበረ የራሱ ምክንያት በመስጠት ኑዛዜው ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ሲከራከር እንደቆየ ተገንዝበናል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ31ዐ3 ግንቦት 23 ቀን 98 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ እንደተመለከተው አመልካች ኑዛዜ ይጽደቅልኝ የሚለውን አቤቱታ ለፍ/ቤቱ ያቀረበችው መጋቢት 17 ቀን 88 ዓ.ም ነው። ይህም ማለት ሟች ከሞተች /መጋቢት 11 ቀን 88 ዓ.ም/ በስድስት /6/ ቀን ውስጥ አቤቱታው ቀርቦአል ማለት ነው። ተጠሪ መልስ የሰጠው ሚያዝያ 3 ቀን 89 ዓ.ም ሲሆን፣ የኑዛዜው መደረግ አጠራጣሪ ነው፣ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ ከሟች ፊርማ ጋር አይመሳሰልም፣ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የኔም የጋራ ሐብት ነው የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክሮአል። ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም ክርክሩን ሲያይ ቆይቶ ውሣኔ የሰጠው ግንቦት 23 ቀን 98 ዓ.ም እንደሆነ ተመልክተናል።
No topics extracted.
እነዚህን ሁኔታዎች ደምረን ስንመለከት አመልካች በጊዜው በንብረቱ ላይ ክስ ሣትመሰርት የቀረችው ተጠሪም ባደረገው አስተዋጽኦ እና ፍ/ቤቱ ባጭር ጊዜ ውስጥ ውሣኔ ባለመስጠቱ ነው ለማለት ችለናል። አመልካች እና ተጠሪ ሲከራከሩ የቆዩትም አመልካች በኑዛዜው መሰረት ንብረት ልትወርስ የምትችልበት አግባብ አለ ወይስ የለም ከሚለው ጋር በተያያዘ ሁኔታ እንደሆነ መመልከቱ የሚከብድ አይደለም። ከዚህ የተነሣም ይርጋው በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1851/ለ/ በተመለከተው መሰረት ተቋርጦአል ለማለት የሚቻል ነው። ሲጠቃለል አመልካች ያቀረበችው ክስ በይርጋ ተቋርጦአል በማለት በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ ሕጉን በአግባቡ በማየት የተሰጠ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 26317 ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ498 ነሐሴ 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሕ//ሥ/ሥ/ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ አለመሆኑን በመገንዘብ ግራ ቀኝ ወገኖች በጉዲዩ ስረ- ነገር ላይ የሚያቀርቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ ተገቢውን ይወስን ዘንድ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 341/1/ መሰረት ይመለስለት።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
ተ.ወ የሰ/መ/ ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፣ 1. አቶ ጊላጋብር ገብረህይወት 2. ወ/ሮ ለተሀዋርያት ገብረህይወት ጠበቃ ስሜነህ ተክለ ቀረቡ 3. ወ/ሮ ምፅላል ዓለም ተጠሪዎች፣ 1. ወ/ሮ አረጋሽ አብርሃ አልቀረቡም 2. አቶ በርሀ አርጋው መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ስላመለከቱ ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞ ከፍተኛ 20 ቀበላ 29 የቤት ቁጥር 139 የሆነ መኖሪያ ቤትና የሰላዲ ቁጥር 3-13285 አ.አ የሆነ ቦቴ መኪና በህይወት እስካለ ድረስ አባታችን አቶ ገብረህይወት ሉያዙበት እሳቸው ሲሞቱ ወ/ሮ ብሬ አስከህይወታቸው ተጠቅመው ንብረቱ ለእኛ እንዱተላለፍ ስምምነት አድርገዋል። የሟች አቶ ገብረህይወት ባለቤት ወ/ሮ ንግስቲ ስምምነቱ የተደረገው በእኔ የጋራ ንብረት ነው በማለት ክስ አቅርበው ወ/ሮ ብሬና እኛ ግማሹን የቤትና የመኪና ግምት እንድንከፍል ውሣኔ ተሰጥቷል። ወ/ሮ ብሬ በቤቱ ሲገለገለ ቆይተው ጥቅምት 19 ቀን 2001 ዓ.ም በሞት ተለይተዋል። በቤቱ መብት ያለን እኛ ስለሆን በሥር ተከሣሽ የነበሩት አንደኛ ተጠሪ አላግባብ የያዙ ስለሆነ ቤቱን ለቅቀው እንዱያስረክቡ ውሣኔ ይሰጥልን በማለት አመልክተዋል።
አንደኛ ተጠሪ በሥር በተከሣሽነት ቀርበው በቤቱ ውስጥ የምኖረው ሟች ወ/ሮ ብሬ እየረደኝ በጥገኝነት ነው ስለዚህ በቤቱ ላይ መብት የላለኝና በሟች ወራሾች ፈቃድ የምኖር በመሆኑ ክሱ ተዘግቶ በነፃ እድሰናበት በማለት የተከራከሩ ሲሆን ሁለተኛው ተጠሪ ጣልቃ ገብ ተከራካሪ በመሆን የሟች ወ/ሮ ብሬ ወራሽ መሆኑን ገልፆ ወ/ሮ ብሬና ሟች አቶ ገብረህይወት ያደረጉት ውል በህግ ፉት የሚፀና ባለመሆኑና አመልካቾች /የሥር ከሣሾች/ የወ/ሮ ብሬ ወራሾች ባለመሆናቸው ውለም በውል አዋዋይ ፉት ያልተደረገ በመሆኑ ቤቱ የወ/ሮ ብሬ በመሆኑ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ውለ መኖሩ ባልተካደበት ሁኔታ የውለ ፍርም መቃወሚያ ላሆን እንደማይችል የሰበር ችልት በመዝገብ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። ስለዚህ ጣልቃ ገቡ በወ/ሮ ብሬና በአቶ ገብረህይወት መካከል የተደረገው ውል ፍርሙን አላሟላም በማለት ያቀረበውን መቃወሚያ አልተቀበልኩትም ቤቱ የሟች አቶ ገብረህይወት መሆኑ ታህሣሥ 22 ቀን 1983 በሁለቱ በወ/ሮ ብሬና በአቶ ገብረህይወት መካከል የተደረገው ውል ስለሚያስረዲ ተከሣሹና ጣልቃ ገብ /የአሁን ተጠሪዎች/ ቤቱን ከሣሾች /አመልካቾች/ ያስረክቡ በማለት ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ውለ የስጦታ ውል ነው የስጦታ ውል መስፈርት የማያሟላ በመሆኑ ከሣሾች ቤቱ ከወ/ሮ ብሬ ጋር አባታችን ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲኖሩ የተገዛ የጋራ ንብረት ነው በማለት ከሚጠይቁ በስተቀር የስጦታ ውል መሰረት በማድረግ ቤቱን እንረከብ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ የህግ ድጋፍ የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
አመልካቾች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካቾች መጋቢት 6 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የይግባኝ ማመልከቻ በመጀመሪያ በሰራተኝነት የገቡትና ኃላም ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነት አብረው የኖሩት ወ/ሮ ብሬ መሲሳና አባታችን አቶ ገብረህይወት ደበሣይ ወ/ሮ ብሬ እኛን ማሣደጋቸውንና ልጅ የላላቸው መሆኑን ምክንያት በማድረግ ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ዓ.ም ውል ተዋውለዋል። በውላቸውም በአዱስ አበባ ከተማ ወረዲ 20 ቀበላ 29 ቁጥሩ 139 የሆነው መኖሪያ ቤትና ቦቴ መኪና ገዝተው ስሙ በሟች ብሬ መሲሳ ሆኖ ንብረቱን በሙለ ባለሀብትነት የሚያዙበት አባታችን አቶ ገ/ሕይወት ደበሣይ እንደሆኑ አባታችን ሲሞቱ ወ/ሮ ብሬ በንብረቱ ህይወታቸው እስካለ ተጠቅመው በሟች አቶ ገብረህይወት ልጆች ንብረቱን ሉያስተላልፈ ተስማምተው የውል ግዳታ ገብተዋል ይኸ ውል ከተፈረመ ከሶስት ዓመት በኃላ ሟች አቶ ገብረህይወት በሞት የተለዩ ሲሆን ወ/ሮ ብሬ ከአስራ አምስት ዓመት በኃላ በሞት ተለይተዋል። ውለ ስለንብረት ባለቤትነትና ንብረትን ስለመጠቀም በሟች አቶ ገብረህይወት ደበሣይና በሟች ወ/ሮ ብሬ መሲሳ የተደረገ ሆኖ እያለ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውለ ስጦታ ውል ነው ስጦታ ውለ የህጉን ፍርም ባሟላ መልኩ የተደረገ አይደለም በማለት ግልፅ የሆነውን የውል ስምምነት ከተዋዋይ ወገኖቹ ፈቃድና ፍላጎት የራቀ ትርጉም በመስጠት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ቤቱና መኪናው የተገዙት አቶ ገብረህይወት ጋር ሲኖር በተፈራ የጋራ ሀብት ነው ብለው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በሟች ብሬ ሞሲሳና በእኛ ላይ ወ/ሮ ንግስቲ ገ/እግዚ ክስ አቅርበውብን መኪናውና ቤቱ የተገዙት በሟች ገብረህይወትና በወ/ሮ ንግስቲ የጋራ ንብረት ነው በማለት ውሣኔ የተሰጠ በመሆኑ ሟች ብሬ ሞሲሳ ከሟች አቶ ገብረሕይወት ጋር ያደረጉት ውል ህጋዊ ነው ሉፀና ይገባል በማለት በመዝገብ ከወ/ሮ ንግስቲ ጋር የተከራከሩበት ሆኖ እያለ የሟች ወ/ሮ ብሬ ወራሽ ነን የሚለት ሁለተኛው ተጠሪ ውለ ፈራሽ ነው ብል ያቀረበው ክርክር አውራሽ አምኖበት ለፍርድ ቤት ያረጋገጠውን ወራሹ መካደ ተገቢ ባለመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልትም ይህንን ክርክር በመቀበል ውለ ፈራሽ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ሁለተኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው ንብረቱ የተገዛው በሟች አቶ ገብረህይወት ገንዘብ ነው ተብል በውለ መጠቀሱ ንብረቱን የሟች አቶ ገብረህይወት ንብረት አያደርገውም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የሚረጋገጠው በአስተዲደሩ ክፍል በሚሰጥ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት እንደሆነ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1195 ተደንግጓል። አመልካቾች ቤቱ የሟች ወ/ሮ ብሬ አይደለም በማለት ያቀረቡት መከራከሪያ ይህን የህግ ግምት የማያፈርስ እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1196 የተመለከተ ምክንያት ባለመሆኑ አቤቱታቸው የህግ መሰረት የለውም።
አመልካቾች በአንድ በኩል የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውለ የስጦታ ውል ነው የህጉን ፍርም አላሟላም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት እያለ በልላ በኩል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ አቶ ገብረህይወት ለሟች ወ/ሮ ብሬ ያደረጉት የስጦታ ውል የወ/ሮ ንግስቲ የጋራ ንብረትና ድርሻ ያለበት ስለሆነ ግማሹን እንዱከፍለ ብል የሰጠውን ውሣኔ በመከራከሪያነት ማንሣታቸው እርስ በርሱ የሚቃረን መከራከሪያ ነው በእርግጥ ሟች ወ/ሮ ብሬ የወ/ሮ ንግስቲ ድርሻ ግማሹን እንዱከፍለ ፍርድ ቤቱ ውሣኔ ሰጥቷል ሆኖም ውሣኔው አልተፈፀመም በአጠቃላይ የአመልካቾች ክርክር የህግ መሰረት የላለውና ዕርስ በርሱ የሚቃረን በመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ሟች አቶ ገብረህይወት ደበሣይና ሟች ወ/ሮ ብሬ ሞሲሳ ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ዓ.ም ያደረጉት ውል የስጦታ ውል ማሟላት ያለበትን ፍርማሉቲ ያላሟላ ስለሆነ ተጠሪዎች ክስ የቀረበበትን ቤት ለአመልካቾች የማስረከብ ግዳታ የለባቸውም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመመስረት ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ እልባት ለመስጠት በመጀመሪያ ሟች አቶ ገብረህይወት ደበሣይና በሟች ብሬ ሞሲሳ መካከል የነበረውን ግንኙነት መሰረታዊ ባህሪ እንደዚሁም ሟች አቶ ገብረህይወትና ሟች ወ/ሮ ብሬ ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ዓ.ም ያደረጉት ውል መሰረታዊ ይዘቱ እና በሕግ ረገድ የሚያስከትለውን ውጤት መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። ሟች አቶ ገብረህይወት ደበሣይና ሟች ወ/ሮ ብሬ ሞሲሳ ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነት ለረዥም ጊዜ አብረው የኖሩ መሆናቸውንና ወ/ሮ ብሬ ሟች አቶ ገብረህይወት ደበሣይ ከላልች ሴቶች የወለዶቸውን ልጆች እንደ ወላጅ እናት ተንከባክበው ያሣደጉ መሆኑ በአመልካቾች የተገለፀና ተጠሪዎችም ያልካደት ፍሬ ጉዲይ ነው። ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩት አቶ ገብረህይወትና ወ/ሮ ብሬ ባልና ሚስት የሚያሣዩአቸውን ሁኔታዎች የሚታዩባቸው የነበሩ መሆኑንና በመካከላቸውም የመተሣሰብ የመተማመን ሁኔታ የነበረ መሆኑን በሥር ፍ/ቤት ከቀረበው ክርክርና ማስረጃ ይዘት መረዲት ይቻላል። ባልና ሚስት ከጋብቻቸው በፉት ወይም ጋብቻ በሚፈፅሙበት ወቅት በንብረት ረገድ ስለሚኖራቸው ግንኙነት የጋብቻ ውል የሚያደርጉበት ሁኔታ በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 42 የተደነገገ ሲሆን በተመሳሳይ መንገድ ባልና ሚስት ነን እየተባባለ ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነት አብረው የሚኖሩ ሰዎች በመካከላቸው ያለውን የንብረት ግንኙነት የሚመለከት ውል ቢዋዋለ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለው ጥያቄ የሚያስነሳ ሲሆን የባልና የሚስት ሁኔታ እያሣዩ ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነት አብረው የኖሩ አንድ ወንድና አንዱት ሴት ስለግላዊ ግንኙነታቸውና በንብረት በኩል ስለሚኖራቸው ግንኙነት የመዋዋል ነፃነታቸውን በሚያሳጣና ውል እንዲይዋዋለ የሚከለክል ግልፅ የህግ ድንጋጌ የላለ መሆኑን ተገንዝበናል።
ህግ አውጭው የመዋዋል ነፃነታቸውንና የሚዋዋለበትን መሰረታዊ ጉዲይ በህግ በግልፅ ክልከላ ካላደረገ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1678 መሰረታዊ ሁኔታዎች በማሟላት እንደባልና ሚስት የሚኖሩት አንድ ወንድና አንዱት ሴት ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነት አብረው በሚኖሩበት ጊዜ ስለሚኖራቸው የግል ግንኙነትና የንብረት ግንኙነት ውል የመዋዋል ነፃነት ያላቸው መሆኑንና ይህም በውል ህግ ድንጋጌዎች መሰረት የሚመራና ውጤት ያለው መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1676/1/ ውልች አይነታቸውና ምክንያታቸው ማንኛውም ቢሆን በዚህ አንቀጽ ጠቅላላ ደንቦች ይመራለ በማለት የደነገገውን ገዥ ድንጋጌ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ሟች አቶ ገብረህይወት ደበሣይና በሟች ወ/ሮ ብሬ ሞሲሳ ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ዓ.ም ያደረጉት ውል እንደባልና ሚስት ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነት ሲኖሩ በንብረት ረገድ የሚኖራቸውን ግንኙነት አንዲቸው በሞት ሲለዩ በተለይ አቶ ገብረህይወት በድንገት በሞት ሲለዩ በቀሪው እድሜ ወ/ሮ ብሬ በንብረቱ ላይ ስለሚኖራቸው መብት ውል አይደለም ሁለቱም ነፃ ሁነው ፈቃዲቸውን የሰጡበት የውል ሰነድ እንጅ። በዚህ በኩል ተጠሪዎችም በሆኑ ውለ የፈቃድ ጉድለት ያለበት ነው በማለት ከሥር ጀምሮ ያቀረቡት ክርክር የላለ መሆኑን በመዝገቡ ከተያያዙት የፍርድ ቤቶቹ ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል።
የውለን ይዘት ስንመለከተው አምስት መሰረታዊ ነጥቦችን የያዘ ሆኖ አግኝተነዋል።
የመጀመሪያው ውለ በአቶ ገብረህይወትና በወ/ሮ ብሬ መካከል ያለው ግንኙነት በምን መንገድ እንደተጀመረና ውለን በሚዋዋለበት ጊዜ በምን ሁኔታ ወይም ደረጃ እንደሚገኝ በስምምነታቸው የገለፁበት ነው። በውለ ወ/ሮ ብሬ በመጀመሪያ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የገቡ ቢሆንም ከዚያ በኃላ ግንኙነታቸው ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነታቸው እንደ ባልና ሚስት አብረው የኖሩ መሆኑን በግልፅ ያመለክታል።
ሁለተኛው ወ/ሮ ብሬ አቶ ገብረህይወት ከላልች ሴቶች የወለዶቸውን ልጆች በእናትነት በመንከባከብና በማሳደጋቸው ከአቶ ገብረህይወት ጋር ለረዥም ጊዜ አብረው በመኖራቸው የሰላዲ ቁጥር 3-13285 የሆነ ቦቴ መኪናና በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞው ከፍተኛ 20 ቀበላ 29 ቁጥሩ 139 የሆነው ቤት በወ/ሮ ብሬ ስም እንዱመዘገብ የተደረገ መሆኑን የሚገልፅ ነው። ሶስተኛው ከላይ የተገለፁትና በወ/ሮ ብሬ ሞሲሳ ስም የተመዘገቡት ንብረቶች የተገዙት ወ/ሮ ብሬና አቶ ገብረህይወት ሰርተው ባገኙት የጋራ ገቢ /የጋራ ሀብት/ ሣይሆን ሙለ በሙለ በአቶ ገብረህይወት የግል ገንዘብ የተገዙ መሆናቸውን በግልፅ የሚያብራራ ሲሆን አራተኛ ንብረቶቹ በወ/ሮ ብሬ ስም ያለ ቢሆንም አቶ ገብረህይወት በህይወት እስካለ ድረስ በንብረቶቹ ላይ ሙለ የባለቤትነት መብት ያላቸው መሆኑን በቤቱም ሆነ በመኪናው ገቢ የሚያዙበት አቶ ገብረህይወት መሆናቸውን በግልፅ የሚደነግግ መሆኑ ነው። አምስተኛው ወ/ሮ ብሬ ከአቶ ገብረህይወት በፉት በሞት ቢለዩ ንብረቱ ሙለ በሙለ የአቶ ገብረህይወት እንደሆነ የሚያረጋግጥና ድንገት አቶ ገብረህይወት ከወ/ሮ ብሬ ሞሲሳ በፉት በሞት ቢለዩ በንብረቶቹ ላይ ወ/ሮ ብሬ ሞሲሳ በህይወት እስካለ የመጠቀምና አላባ የመሰብሰብ መብት ያላቸው መሆኑን ‛….. ሞት በሰው ላይ ያለ የተፈጥሮ ግዳታ ስለሆነ ከእሳቸው በፉት ህይወቴ ቢያልፍ ንብረቱ የራሳቸው ገንዘብ ስለሆነ የመኪናውም ሆነ የቤቱ ባለመብት ናቸው ከእኔ ህይወት በፉት የእሳቸው ህይወት ቢያልፍ ህይወቴ እስካለ ድረስ በመኪናውና በቤቱ ተጠቃሚ እኔ ሆኜ ከህይወት በኃላ እኔ ላሣደግኳቸው የሁለተኛ ተስማሚ ልጆች 1ኛ ህይወት ገ/ሕይወት 2ኛ ጊላ ገብረህይወት 3ኛ ለተሃዋሪያት ገብረህይወት እንዱተላለፍ በፈቀደት መሰረት ለእነዚሁ ልጆች ቤቱና መኪናው የሚተላለፈው ባለመብት የሚሆኑት ልጆች መሆናቸውን በፊርማየ አረጋግጣለሁ በማለት ወ/ሮ ብሬ የተስማሙና አቶ ገብረህይወትም ስምምነቱን የተቀበለ መሆኑን የሚያረጋግጥ የውል ሰነድ ነው።
ይህ ውል ከተደረገ በኋላ አቶ ገብረህይወት በሞት ሲለዩ አመልካቾች የውለን ድንጋጌ በመጣስ ወ/ሮ ብሬ ንብረት ያካፍለን የሚል ክስ ያላቀረቡ መሆኑን በግራቀኙ በኩል ከተደረገው ክርክር ለመገንዘብ ይቻላል። የአሁኑ ክርክር መነሻ ወ/ሮ ብሬ በህይወት እስካለ ድረስ በንብረቱ የመጠቀም መብታቸውን ተጠቅመው ካለፈ በኃላ ሁለተኛ ተጠሪ ንብረቱን ልወርስ ይገባል በማለት ያቀረቡት ክርክር ነው። በህግ አግባብ የተቋቋሙ ውልች ባቋቋማቸው ሰው ላይ ህግ ናቸው በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1731/1/ የሚደነግግ ሲሆን አንድ ሰው በሞት ሲለይ በሟች መሞት ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆኑ በስተቀር በውርሱ ውስጥ የሚገኙት መብቶችና ግዳታዎች ለወራሾቹ ወይም የኑዛዜ ባለስጦታዎች የሚተላለፍ መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 826/2/ ተደንግጓል።
ሁለተኛ ተጠሪ ሉወርስ የሚችለው በወ/ሮ ብሬ መሞት ምክንያት የማይቋረጡ መብቶችና ግዳታዎችን ነው። ሟች ወ/ሮ ብሬ አከራካሪው ቤት በስማቸው የተመዘገበ ቢሆንም ቤቱ በሟች አቶ ገብረህይወት የግል ገንዘብ የተገዛ የአቶ ገብረህይወት የግል ሀብት እንደሆነ ወ/ሮ ብሬ አብረው እስካለ ድረስ በጋራ የመጠቀም ሟች አቶ ገብረህይወት ከወ/ሮ ብሬ በፉት በሞት ቢለዩ በህይወት እስካለ ድረስ በንብረቱ የመጠቀምና አላባ የመስበሰብ መብት ብቻ ያላቸው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በመግለፅ ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ከአቶ ገብረህይወት ጋር ከጋብቻ ውጭ በግብረሥጋ ግንኙነት ሲኖሩ በንብረት ረገድ ስላላቸው መብትና ግዳታ በመዘርዘር ባደረጉት ውል ተስማምተዋል አቶ ገብረህይወት በሞት ከተለዩ በኃላ በዚህ ውል መሰረት ወ/ሮ ብሬ በንብረቶቹ ላይ ያላቸው መብት ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1309 በተደነገገው መሰረት በንብረቶቹ የመጠቀምና አላባ የመሰብሰብ መብት መሆኑ በውለ በግልፅ ተገልፆል፡ በሚንቀሳቀስም ሆነ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ የአላባ የመጠቀም መብት /Usufruct Right / የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ሲሞት ቀሪ የሚሆን መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1322/1/ የተደነገገ በመሆኑ ሟች ወ/ሮ ብሬ ሞሲሳ በአከራካሪው ቤት ላይ ያላቸው የመጠቀምና አላባ የመሰብሰብ መብት በመሞታቸው ምክንያት የሚቋረጥና ለወራሻቸው ለሁለተኛው ተጠሪ የማይተላለፍ መብት መሆኑን ከላይ የተገለፁትን የህግ ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዲት ችለናል።
ስለሆነም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሟች አቶ ገብረህይወትና ወ/ሮ ብሬ ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ዓ.ም ያደረጉት ውል ከጋብቻ ውጭ እንዲባልና ሚስት ከግብረሥጋ ግንኙነት አብረው ሲኖሩ በንብረት ረገድ ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ያደረጉት ውል ሆኖ እያለ የስጦታ ውል ነው በማለት ከውለ መሰረታዊ ይዘትና ባህሪ ውጭ የራሱን ትርጉም መስጠቱና ውለ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 881 የተደነገገውን ፍርም አላሟላም በማለት የማይረጋ ነው ብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ወ/ሮ ብሬና አቶ ገብረህይወት ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ዓ.ም ያደረጉት ውል በንብረት ረገድ ያላቸውን ግንኙነትና ሁለቱም ያላቸውን መብትና ግዳታ በሙለ ፈቃዲቸው የተስማሙበት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1727 ድንጋጌዎች መሰረት በተዋዋዬቹና በምስክሮች የተፈረመ ህጋዊ ውጤት ያለው ውል ሆኖ አግኝተነዋል። በውለ ሟች ወ/ሮ ብሬ በአከራካሪው ቤት ባለሀብት አለመሆናቸውና አቶ ገብረህይወት ከሞቱ በኃላ ወ/ሮ ብሬ በአከራካሪው ቤት ላይ የነበራቸው በንብረቱ የመጠቀምና ፍሬ የመሰብሰብ መብት እንደሆነ በግልፅ ተመልክቷል።
ወ/ሮ ብሬ በቤቱ ላይ ያላቸው የአላባ ጥቅም መብት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1322/1/ መሰረት ቀሪ ስለሆነ ሁለተኛ ተጠሪ የአመልካቾች አባትና አውራሽ የአቶ ገብረህይወት ደበሣይ የግል ንብረት የሆነውን አከራካሪውን ቤት የሚወርሰበት ምክንያት የላለው በመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ በውጤት ደረጃ ፀንቷል
አከራካሪውን ቤት ተጠሪዎች ለአመልካቾች ሉያስረክቡ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥተናል።
በሟች ወ/ሮ ብሬ ሞሲሳና በሟች አቶ ገብረህይወት ደበሣይ መካከል ታህሣሥ 22 ቀን 1983 ዓ.ም የተደረገው ውል ህጋዊ አስገዲጅነትና ውጤት ያለው ውል ነው ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራቀኙ ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።