No summary available.
ጥቅምት 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ዶ/ር ደስታ አቡኑ በለጡ ተጠሪ፡- ሲስተር አስቴር ካሣ መልደየስ - ጠበቃ አየለ ማሞ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጋብቻን በፍቺ መፍረስ ተከትል የተነሣውን የንብረት ክፍፍል ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ በአዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት ነው። ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር እና ፍ/ቤቶቹ ከሰጡአቸው ውሣኔዎች ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ግራ ቀኝ ወገኖች በጋብቻቸው ወቅት ያፈሩዋቸው ናቸው ተብለው ለክፍፍል ከቀረቡት ንብረቶች መካከል ለአሁኑ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆኑት በሁለት የተለያዩ ከተሞች የሚገኙት የመኖሪያ ቤቶች ናቸው። ክርክሩን በመጨረሻ ደረጃ የሰማው በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በወላይታ ሶድ ያለው ቤት ለአመልካች፤ በሃዋሣ ከተማ ያለው ቤት ደግሞ ለተጠሪ እንዱሆን ወስኖአል። የሃዋሣው ቤት በወላይታ ሶድ ካለው ቤት ብልጫ ስላለው ተጠሪ ልዩነቱን በገንዘብ ለአመልካች እንድታካክስም በተጨማሪ አዞአል። አመልካች በዚህ መልክ የተሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ነው የአሁኑን የሰበር አቤቱታ ያቀረበው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገውም ግራ ቀኝ ወገኖቹ ባልተስማሙበት ሁኔታ የተሰጠው የንብረቶቹ ክፍፍል ውሣኔን አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረት ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። በመቀጠልም ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በጋብቻ ተሳስረው የቆዩ ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በፍቺ ሲያፈርሱ በንብረት ረገድ የነበራቸው ግንኙነትም እልባት ማግኘት አለበት። ይህ የሚሆነው ንብረቱን በመከፊፈል ሲሆን፣ ክፍፍለ የሚከናወነው አግባብ ባላቸው የቤተሰብ ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ነው። በፋዳራል መንግሥቱ የወጣውም ሆነ የአሁኑ ክርክር በተነሳበት የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የወጣው የቤተሰብ ሕግ በንብረቱ ክፍፍል ረገድ የሚከተለት መርህ የአኩልነት መርህ ነው። የእኩልነት መርህ ድንጋጌዎቹ መሰረትም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 34/1/ የተቀመጠው ድንጋጌ እንደሆነ ግልጽ ነው። ላላው በንብረቱ ክፍፍል ሂደት ላታይ የሚገባው ጉዲይ የባለጉዲዮቹ ስምምነት መኖር እንደሆነም በቤተሰብ ሕጎቹ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ቤቶቹን በሚመለከት በተደረገው የክፍፍል ሂደት ወይም ሁኔታ አመልካች አልተስማማም። ላለመስማማቱ የሰጠው ምክንያትም የክፍፍል ሂደቱ የእኔን የእኩልነት መብት ያስጠበቀ አይደለም የሚል እንደሆነ ከክርክሩ ይዘት ለመገንዘብ ችለናል። ተጠሪ ደግሞ እኔ የምኖረው በሃዋሣ ከተማ በመሆኑ እና አመልካች የሚኖረው ከሃዋሣ ወጪ ስለሆነ የሃዋሳው ቤት ለኔ ቢሰጥ የበለጠ ተጠቃሚ እሆናለሁ በማለት ነው የምትከራከረው። የሥር ፍ/ቤት ቤቱ ለእስዋ እንዱሰጥ የወሰነውም ይህንኑ የበለጠ ተቃሚነት የሚለውን አስተሳሰብ መሰረት በማድረግ እንደሆነ ከውሣኔው ይዘት ተገንዝበናል።
እንደምናየው አመልካችም ሆነ ተጠሪ በሁለቱም ቤቶች ላይ ያላቸው መብት የእኩል ነው።
ክፍፍለ መደረግ ያለበት ይህን መሰረት በማድረግ በመሆኑ ሁለቱም ከሁለቱ ቤቶች እኩል ድርሻ ሉያገኙ ይገባል። ቤቶቹ በተለያዩ ከተሞች /አካባቢዎች/ እንደመገኘታቸው መጠን የሚኖራቸው ዋጋም እንደዚሁ እንደሚለያይ መገመቱ አይከብድም። የቤቶቹ አሰራር እና ያለበት ልዩ አካባቢም /ቦታም/ በሚያወጡት ዋጋ ላይ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታወቃል። በእርግጥ እነዚህ ልዩነቶች ቢኖሩም ግራ ቀኝ ወገኖች ስምምነት ላይ ከደረሱ ያለምንም ችግር በስምምነቱ መሰረት ሉከፊፈለ ይችላለ። ስምምነት ከላለ ግን በሕጉ የተቀመጠውን የእኩልነት መርህ እና አግባብነት ባላቸው ድንጋጌዎች የተቀመጠውን የክፍፍል ሥርዓት መሰረት በማድረግ ክፍፍለ እንዱፈጸም መወሰን የግድ ይሆናል። የሥር ፍ/ቤት ለክፍፍለ አፈፃፀም መሰረት ያደረገው የበለጠ በንብረቱ የመጠቀም ሁኔታ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ እንደ ትክክለኛ የክፍፍል ሥርዓት ተቆጥሮ ተቀባይነት የሚያገኝ አይደለም። በበኩላችን ትክክለኛ የክፍፍል ሥርዓት ሆኖ ያገኘነው በቅድሚያ ሁለቱም ቤቶች በገበያ ዋጋ መሰረት የሚያወጡት ዋጋ እንዱታወቅ ማድረግ፤ በመቀጠልም ግራ ቀኝ ወገኖች የገበያ ዋጋን መሰረት በማድረግ በዓይነት ለመከፊፈል ስምምነት ላይ ከደረሱ የበለጠ ዋጋ ያለውን ቤት የሚወስደው ወገን ገበያ ባስገኘው ዋጋ መሰረት ላላኛውን ወገን ልዩነቱን በገንዘብ እንዱያካክስ፤ ይህ የማይቻል ከሆነ ደግሞ በሕጉ በተቀመጠው የመጨረሻው አማራጭ ቤቶቹ ተሸጠው ገንዘቡን እንዱከፊፈለ ማድረግ ነው። አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ ክፍፍለን በዚህ መሰረት እንዱከናወን ባለመወሰኑ ውሣኔው በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽለዋል።
በሃዋሣ ከተማ እና በወላይታ ሶድ ከተማ ያለት ቤቶች በቅድሚያ በገበያ ዋጋ መሰረት ተገምተው ዋጋቸው እንዱታወቅ እንዱደረግ፤ በመቀጠልም ግራ ቀኝ ወገኖች የሚስማሙ ቢሆን የቀረበውን የገበያ ዋጋ መሰረት በማድረግ ቤቶቹን በዓይነት እንዱካፈለ፤ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን የወሰደው ወገንም ላላኛውን ወገን ልዩነቱን በገንዘብ እንዱያካክስ፤ በዚህ መሰረት ተስማምተው መከፊፈል ካልቻለ ግን ሁለቱም ቤቶች ተሸጠው ገንዘቡን እኩል እንዱካፈለ በማለት ወስነናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ ብለናል።