No summary available.
ጥቅምት 04 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- እነ ወ/ሮ ሰላማዊት አስራት (አምስት ሰዎች) ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ መሰረት ዘውዳ ከጠበቃ መስፍን እሸቱ ጋር ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ጋብቻ በሞት መፍረስን ተከትል በሟች ወራሾችና በሕይወት በቀረው ተጋቢ መካከል የተነሣውን የንብረት ክፍፍል ክርክር የሚመለከት ነው።
ከመዝገቡ እንደሚታየው ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤት አመልካች የነበሩት የአሁኑ አመልካቾች ሲሆን በአቤቱታቸውም የአሁኗ ተጠሪ ባለቤት የነበሩት ማስተር ቴክኒሺያን አስራት መኮንን ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን፣ገለፀው የሟቹ ውርስ እንዱጣራላቸው የውርስ አጣሪ እንዱሾምላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የሥር ፍርድ ቤትም ተጠሪን በመልስ ሰጪነት በመጥራት የውርስ አጣሪው እንዱሾም በማድረግ ውርስ አጣሪው የውርስ ሐብቱን በማጣራት ሪፕርቱን እንዱያቀርብለት አድርጏ ውርስ አጣሪው ሪፕርቱን ሲያቀርብለት ግራ ቀኙ አስተያየታቸውን እንዱሰጡበት አድርጓል። ከዚህም በሁዋላ በአዱስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 02/03 ክልል ውስጥ ይገኛል የተባለውና ቁጥሩ 1539 የሆነ ቤት ሟች ማስተር ቴክኒሽያን አስራት መኮንን በግላቸው የነበራቸው ቤት በመሆኑ እና በቤተሰብ ሕጉም የጋብቻ ውል ሲደረግ አስገዲጅ የሕግ ድንጋጌ መፃረር እንደላለበት በመግለጽ ቤቱ የሟች የግል ቤት ነው በማለት ተጠሪ ቤቱ በጋብቻ ውል የጋራ ተደርጓል በማለት ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ አድርጏ ወስኗል። ከዚህ በሁዋላም የአሁኗ ተጠሪ ቤቱ የሟች የግል ነው ተብል በተወሰነው የውሳኔ ክፍል ቅር በመሰኘት ይግባኛቸው ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲያቀርቡ አመልካቾች በበኩላቸው በቤቱ ላይ ከተጠሪ በፉት ከሟች ማስተር ቴክኒሺያን አስራት መኮንን ጋር ጋብቻ መስርተው የነበሩት የአመልካቾች እናት ወ/ሮ ፈትለወርቅ መንገሻ ነው ሲለ ያቀረቡት ክርክር በስር ፍርድ ቤት መታለፈ ያላግባብ መሆኑን ገልጸው የመስቀለኛ ይግባኝ አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ አከራካሪው ቤት ላይ የአመልካቾች እናት ወ/ሮ ፈትለወርቅ መንገሻ ድርሻ እንደላላቸው በማረጋገጥ ቤቱ የሟች ማስተር ቴክኒሺያን አስራት መኮንን የጋራ ንብረት እንዱሆን በጋብቻ ውል ስምምነት የተደረገበት በመሆኑ ቤቱ የጋራ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመሻር ወስኗል። ከዚህ በሁዋላም አመልካቾች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሳኔ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች ሐምል 29 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- አከራካሪው ቤት ግማሹ የአመልካቾች እናት ከሟች አስራት መኮንን ጋር በነበሩበት ጊዜ የተፈራ ሁኖ እያለና ከጋብቻ በፉት የተፈራ ንብረትን በጋብቻ ውል የጋራ ንብረት ለማድረግ የማይቻል ሁኖ እያለ ቤቱን በጋብቻ ውል የጋራ አድርገውታል ተብል ግማሹን ተጠሪ እንዱወስደ መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸውም ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታመኑ ተጠሪ ቀርበው በጠበቃቸው አማካኝነት የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት አራት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። በመልሳቸውም የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ የጋብቻ ውለንና ሕጋዊ ውጤቱን መሰረት ያደረገ መሆኑን ዘርዝረው ውሳኔው ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አመልካቾች መጋቢት 17 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት አራት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአመልካቾች አውራሽ ማስተር ቴክኒሺያን አስራት መኮንን ተጠሪን ከማግባታቸው በፉት የአመልካቾችን እናት ወ/ሮ ፈትለወርቅ መንገሻን አግብተው ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ መሆኑን፣ከፍቺው በሁዋላም የንብረት ክፍፍል ተደርጏ አሁን እያከራከረ ያለው ቤት ለማስተር ቴክኒሺያን አስራት መኮንን እንዱሆን በወቅቱ በተሰየመው የቤተዘመድ ጉባኤ ተወስኖ ይህ ውሳኔ ፍርድ ቤት ቀርቦ መጽደቁን፣ከዚህም በኋላ ሟች አቶ አስራት መኮንን ከተጠሪ ጋር ጋብቻ መስርተው ሐምል 27 ቀን 1972 ዓ.ም ባደረጉት የጋብቻ ውል አሁን እያከራከረ ያለውን ቤት የጋራ ማድረጋቸውን ነው። አመልካቾች የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ስህተት ነው የሚለት ሁለት ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ነው። አንደኛው ቤቱ ላይ የእናታቸው ግማሽ ድርሻ አለበት የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጋብቻ ውል የግል ንብረትን የጋራ ንብረት ለማድረግ አይቻልም በሚል ነው። እኛም እነዚህን ቅሬታዎች መሰረት በማድረግ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ ተመልክተናል።
የአመልካቾች እናት ወ/ሮ ፈትለወርቅ መነገሻ ከሟች አባታቸው ጋር የነበራቸውን ጋብቻ በፍቺ ካፈረሱ በሁዋላ ውጤቱን በተመለከተ ደግሞ በቤተዘመድ ጉባኤ ታይቶ ይኼው አካል የሰጠው የንብረት ክፍፍል ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ጸድቋል። በፍርድ ቤት በፀደቀው የቤተዘመድ ጉባኤ ውሳኔ ደግሞ አሁን እያከራከረ ያለው ቤት ለሟች ማስተር ቴክኒሺያን አስራት መኮንን ተሰጥቷል። ይህ ውሳኔ በየትኛውም ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት አልተለወጠም። እንዱህ ከሆነ ቤቱ የሟች አስራት መኮንን የግል ንብረት መሆኑ ከተረጋገጠ በሁዋላ ሟች አስራት መኮንን ከተጠሪ ጋር ጋብቻ የፈፀሙ መሆኑን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። ስለሆነም ቤቱ የሟች አስራት መኮንን የግል ንብረት ነው ተብል መወሰኑ በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን የግራ ቀኙን ክርክሮችንና ማስረጃዎችን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር የሚነቀፍ ሁኖ ስላላገኘን በዚህ ረገድ አመልካቾች ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የላለው ነው።
ላላው በዚህ ችልት አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት ሟች አስራት መኮንን ከተጠሪ ጋር ሐምል 27 ቀን 1972 ዓ.ም የተደረገው የጋብቻ ውል አስገዲጅነት ያለውን በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57 ስር የተደነገገውን የሚፃረር ነው የሚል ነው።
በመሰረቱ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 57 ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸውን ንብረቶች ወይም ከጋብቻ በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው የሚያገኟቸውን ንብረቶች በጋብቻ ዘመንም የግል ሁነው ይቀራለ በማለት በአስገዲጅነት ይደነግጋል። ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ በሕጉ ጥበቃ የሚደረግለት ንብረቶቹ በጋብቻ ውል የጋራ እንዱሆኑ ስምምነት ከላለ ብቻ ነው። የጋብቻ ውል ሲደረግ ደግሞ ሉከተለው የሚገባው ፍርማሉቲ ስለመኖሩ የተጠቀሰው ሕግ በአንቀጽ 44 ስር ደንግጓል። ይኸው ሕግ በአንቀጽ 42 ንኡስ ቁጥር አንድና ሁለት ስር ተጋቢዎች ንብረታቸውንና ግላዊ ግንኙነታቸውን በተመለከተ ለመወሰን እንደሚችለ ይገልፃል። ሕጉ የጋብቻ ውል አስገዲጅ የሆኑ የሕጉ ድንጋጌዎችን መፃረር እንደላለበትም በአንቀጽ 42/3/ ስር በግልጽ አስቀምጧል። የሕጉ አንቀጽ 47 እና 73 ድንጋጌዎች ሲታዩም የጋብቻ ውል የሚሻሻልበትን ሥርአት ያስገነዝባለ። ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የምንችለው የጋብቻ ውጤት በጋብቻ ውል ሉቋቋም፣ሉቀር ወይም ሉሻሻል የሚችል መሆኑን ነው።
ላላው ከድንጋጌዎች መረዲት የምንችለው ተጋቢዎች የጋብቻቸውን ውጤት በጋብቻ ውል ከወሰኑ እና ውለም አስገዲጅ ድንጋጌዎችን የማይቃረን መሆኑ ከተረጋገጠ የተጋቢዎች የንብረትም ሆነ ግል ግንኙነት ሉገዛ የሚባው በጋብቻ ውለ መሆን ያለበት መሆኑን ነው። ሕጉ የባልና ሚስት የንብረትና የግል ግንኙነት ክርክር ሲቀርብ ተፈፃሚ የሚሆነው የጋበቻ ውለ ያልሸፈነው ክፍተት ካለ ብቻ ነው። በመሆኑም ‛የጋብቻ ውል አስገዲጅ የሕግ ድንጋጌዎችን እስካልተቃረነ ድረስ ተፈፃሚነት ይኖረዋል…“ የሚለው ሐረግ አስገዲጅነት ያላቸው የሕጉ ድንጋጌዎች ማለት የትኞቹ ናቸው?
የሚለውን መመልከትን የግድ የሚል ነው። ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የጋብቻ ውል ሲመሰረት ሉከተላቸው የሚገባቸው ፍርማሉቲዎች እና በጋብቻ ውለ ስምምነት የሚደረግባቸው ግንኙነቶች ምን እንደሆነ በሕጉ ተመልክተዋል። የጋብቻ ውለ ፍርማሉቲው ሲከተል ሉያሳካ የታሰበው ግብም ስምምነቱ የተጋቢዎችን ነፃ ፈቃድ አግኝቶ የመዋዋል ነፃነታቸው ተከብሮ የተገኘ መሆኑን ማረጋገጥ መሆኑ ይታመናል። እንዱህ ከሆነ ሕጉ ከጋብቻ በፉት የተገኘ ንብረትን የግል ንብረት ነው በማለት ጥበቃ የሚያደርገው በሕጉ አግባብ በተደረገ የጋብቻ ውል መሰረት የጋራ ያልሆነውን ንብረት ብቻ ነው። ስለሆነም አስገዲጅ የሆኑትን የሕግ ድንጋጌዎችን የጋብቻ ውለ ሉፃረር አይገባም የሚለው የሕጉ አነጋገር ከጋብቻ ውል አደራረግ ጋር የተያዙትን የፍርማሉቲ ጉዲዮችንና ከተጋቢው ግላዊ ነፃነት ጋር የተገናኙት ጉዲዮች እንጂ ከንብረት ጋር የተያያዙትን አይደለም። ከጋብቻ በፉት የተፈራን ንብረት በሕጉ አግባብ በተደረገ የጋብቻ ውል የጋራ ማድረግ አስገዲጅ የሆኑ የቤትሰብ ሕግ ድንጋጌዎችን መፃረር ነው ልባል የሚችል አይደለም። አንድ ንብረት ከጋብቻ በፉት የተገኘ መሆኑ ንብረቱ የተጋቢው የግል ንብረት ሁኖ እንዱቀር ሕጉ ያስቀመጠው ሁኔታ ጠቅላላ ደንብ ሲሆን ይህ ጠቅላላ ደንብ ተፈፃሚ የሚሆነው ንብረቱን የጋራ የሚያደርግና ልዩ ደንብ የሆነው የጋብቻ ውል በላለበት ሁኔታ ብቻ ነው። በመሆኑም ሕጋዊ የጋብቻ ውል ልዩ ደንብ (exception) ሲሆን በአንቀጽ 57 ስር የተመለከተው ሁኔታ ደግሞ መርህ ልባል የሚችል ነው። በሕግ አተረጓጏም ደንብ ደግሞ ተፈፃሚነት ያለው ልዩ ሁኔታ የሆነው ሕግ ነው።
ሲጠቃለልም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አከራካሪው ቤት በጋብቻ ውል የአመልካቾች አባትና ተጠሪ የጋራ ሁኗል በሚል ምክንያት የቤቱ ግማሽ ድርሻ የተጠሪ ይሆናል በማለት መወሰኑ የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 42፣44 እና 57 ድንጋጌዎችን ያገናዘበ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.