No summary available.
ጥቅምት 5 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም አመልካቾች፡-
በሰበር ችልቱ ሉመረመር በጭብጥነት የተያዘው ነጥብ የይርጋ መቃወሚያን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት ያደረገ ነው። ጉዲዩ ያለአግባብ የተያዘው ቤት ይለቀቅልኝ በማለት ተጠሪ ባቀረበችው ክስ መነሻነት የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንዲየነው ተጠሪ ይለቀቅልኝ የምትለው ቤት አመልካቾች ይዘውት የሚገኝ ሲሆን፣በተጠሪ ክርክር እንደተገለጸው ባለንብረት የሆኑት ወ/ሮ አፀደ ገ/የሱስ የተባለት ሴት ናቸው። ወ/ሮ አፀደ ገ/የሱስ ቤቱን አቶ ማንደፍሮ ቸርነት እና ወ/ሮ እልፍነሽ ቸርነት ለተባለት ሰዎች በስጦታ ውል እንዲስተላለፈት፣በኋላም ወ/ሮ እልፍነሽ ቸርነት ድርሻቸውን በፈቃዲቸው ለአቶ ማንደፍሮ ቸርነት እንደተው፣አቶ ማንደፍሮ ቸርነት ደግሞ የተጠሪ አውራሽ እንደሆኑ በተጠሪ ክስ ተገልጾአል።
አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መልስ በየበኩላቸው ከአቶ ማንደፍሮ ቸርነት ጋር ባደረጉት የሺያጭ ውል ቤቱን መግዛታቸውን፣ በገዙት መጠን ቤቱን ይዘው ከ11 እና ከ13 ዓመት በላይ ሲጠቀሙ መቆየታቸውን፣ወ/ሮ አፀደ ገ/የሱስ ለአቶ ማንደፍሮ ቸርነት እና ለወ/ሮ እልፍነሽ ቸርነት አደረጉት የተባለው የስጦታ ውል በሕጉ አግባብ ፍፃሜ አላገኘም፤በዚህ አይነትም ከ21 ዓመት በላይ ቆይቶአል፣በመሆኑም ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል የሚለትን ነጥቦች በማንሳት ተከራክረዋል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ ክርክሩን የመረመረ ሲሆን፣በመጨረሻም አመልካቾች ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ በማድረግ ቤቱን ለተጠሪ እንዱለቁ ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን ከሰማ በኋላ፣በአመልካቾች ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮአል በመጨረሻም ተጠሪ ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብዋ በዚህ ደረጃም ክርክር የተሰማ ሲሆን ፍ/ቤቱ አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ ይልቀቁ በማለት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካቾች ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። በመቀጠልም ከግራ ቀኝ ወገኖች የቀረበውን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው በዚህ ሰበር ችልት የሚመረመረው ጭብጥ አመልካቾች ያቀረቡት የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ ተደርጏ ቤቱን ይልቀቁ የተባለው በአግባቡ ነው ወይ? የሚለው ጭብጥ ነው። አመልካቾች በተለይ ከ1 እስከ 3 ያለት ቤቱን የያዙት ከአቶ ማንደፍሮ ቸርነት ጋር የሽያጭ ውል አድርገው በመግዛት እና የሺያጭ ዋጋውንም በመክፈል እንደሆነ በክርክሩ ተመልክቶአል።
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ቢሆን የሽያጭ ውል አልተደረገም አላለም። የሺያጭ ውለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 የተመለከቱትን መስፈርቶች አያሟላም የሚል ምክንያት በመስጠት ነው ውልን በማስመልከት አመልካቾች ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ ያደረገው 4ኛ አመልካችም ቦታውን በቃል በተደረገው ስጦታ ተላልፍልኝ ቤቱን በራሴ ወጪ ሰርቻለሁ በማለት ቢከራከርም፤ስጦታው በጽሐፍ አልተደረገም በሚል ክርክሩ ተቀባይነት ሳያገኝ እንደቀረ ተመልክተናል። ከዚህም በተጨማሪ ቤቱ በአቶ ማንደፍሮ ቸርነት ስም አልተላለፈም (የስጦታ ውለ ተፈፃሚ አልሆነም) የሚል ክርክር በአመልካቾች መነሳቱንና ተጠሪ ይህን በግልጽ አለማስተባበልዋን ተገንዝበናል። ከሁለ በላይ ደግሞ አመልካቾች ቤቱን የያዙት ተጠሪ አውራሽ ነው የምትለው ሰው (አቶ ማንደፍሮ ቸርነት) በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሆኖ ተጠሪ ክስ የመሰረተችው አመልካቾች ቤቱን ከያዙ ከ11 እና 13 ዓመታት በኋላ ነው። የይርጋው ጊዜ መቆጠር ያለበትም አመልካቾች ቤቱን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ እንጂ ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ አገኘሁ ከምትልበት ጊዜ ጀምሮ አይደለም። በመሆኑም የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ተጠሪ የወራሽነት ማረጋገጫ ያወጣችበትን ወይም አቶ ማንደፍሮ ቸርነት የሞቱበትን ቀን መነሻ በማድረግ በይርጋ ረገድ የቀረበውን መቃወሚያ መወሰኑ ትክክል ሆኖ አላገኘነውም። በአጠቃላይ የአመልካቾችን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ በሕጉ አተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
አመልካቾች ቤቱን ለተጠሪ እንዱለቁ በማለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ.31107 ሐምል 11 ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይህን ውሳኔ በማጽናት በመ/ቁ. 43519 ሰኔ 15 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረበችው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።