No summary available.
ጥቅምት 2 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ገብረሥላሴ አማረ አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ አብርኸት ተጫኔ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የሚያከራክረው ጉዲይ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍያ የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍች መፍረሱን ገልፀው በጋብቻ ወቅት በጋራ ያፈሩት የቤት ቁሣቁስ በልደታ ክፍለ ከተማ ተከራይተው ከሚኖሩበት ቤት ግቢ ውስጥ የሰሩት አንድ ክፍል ቤትና በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 2 ሣይት ህንፃ ቁጥር 29 የቤት ቁጥር ቢ29/48 የሆነ ኮንደሚኒየም ቤት የጋራ ስለሆነ ያካፍለኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በቀበላ ቤት ግቢ ውስጥ የተሰራው ቤት ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ከመፈፀማቸው በፉት የተሰራ መሆኑን የኮንደሚኒየም ቤቱ ደግሞ ከተጠሪ ጋር የነበረንን ጋብቻ ታህሣሥ 18 ቀን 1999 ዓ.ም በስምምነት አፍርሰን ተጠሪ ብር 1300/አንድ ሺ ሶስት መቶ ብር/ ተቀብላ ከሄደች በኋላ የደረሰኝ ስለሆነ የጋራ ንብረት አይደለም በማለት ተከራክረዋል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከቀበላ ከተከራዩት ግቢ የተሰራው አንድ ክፍል ቤት አመልካች ተጠሪን ከማግባቱ በፉት የሰራው የግል ንብረቱ መሆኑን በተሻለ ማስረጃ አስረድቷል። የኮንደሚኒየም ቤቱ የደረሰው የአመልካችና የተጠሪ ጋብቻ በፍርድ ቤት ውሣኔ በፍች ከመፍረሱ በፉት ነው። የተጠሪና የአመልካች ጋብቻ የፈረሰው መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም እንጂ ታህሣሥ 18 ቀን 1999 ዓ.ም አይደለም። ስለዚህ ኮንደሚኒየም ቤቱ የጋራ ንብረት ስለሆነ በቤቱ ላይ ያለውን መብትና ግዳታ አመልካችና ተጠሪ እኩል ይካፈለ ።
የቤት ቁሣቁስ ይካፈለ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቷል።
አመልካች ኮንደሚኒየም ቤት ለማግኘት የተመዘገብኩት ተጠሪን ከማግባቴ በፉት ነው። ከዚህ በተጨማሪ እኔና ተጠሪ በስምምነት ጋብቻችንን ኀዲር 23 ቀን 1999 ዓ.ም አፍርሰናል። ስለዚህ የተመዘገብኩት ተጠሪን ከማግባቴ በፉት እጣ የወጣልኝና ያገኘሁት እኔና ተጠሪ በስምምነት ጋብቻችንን ካፈረስን በኋላ በመሆኑ ኮንደሚኒየም ቤቱ የጋራ ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ሰኔ 8 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አመልክቷል። ተጠሪ በበኩላቸው ከቤት የወጣሁት በስምምነት ጋብቻችንን በማፍረስ ሣይሆን አመልካች ስለሚደበድቡኝ የቀለብ ገንዘብ ሰጥተውኝ ነው። ኮንደሚኒየም ቤቱ የደረሰን ጋብቻው ከመፍረሱ በፉት በመሆኑና አስር ፏርሰንት የቅድሚያ ክፍያ የተከፈለው ከጋራ ንብረት በመሆኑ ቤቱ የጋራ ንብረት ነው መባለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መረምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የአመልካችና የተጠሪ ጋብቻ መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም በፍርድ ቤት ውሳኔ መሆኑንና ኮንደሚኒየም ቤቱ የደረሳቸው ጋብቻው በፍች ከመፍረሱ በፉት መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች ለኮንደሚኒየም ቤት የተመዘገብኩት ተጠሪን ከማግባቴ በፉት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክርም ቤቱን እዱገዙ እጣ የወጣበት ጊዜ ጋብቻው ፀንቶ እስካለ ድረስ ተጠሪን ከማግባታቸው በፉት ስለተመዘገቡ ብቻ ቤቱ የግል ንብረት እንደማይሆን ከተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 62 ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻል በመሆኑ አመልካች ያቀረቡት ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ ለቤቱ ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ የሚከፈለውን ክፍያ ከአመልካች ጋር አብረው የመጋራትና ግማሹን የመክፈል ግዳታ እንዲለባቸው ግልጽ በማድረግ አመልካችና ተጠሪ በኮንደሚኒየም ቤት ላይ ያለውን መብትና ግዳታ እኩል እንዱካፈለ በማለት መወሰኑን ተገንዝበናል። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለበት ሆኖ ስላገኘነው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ይኸ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.