No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ዘይነባ ከልፊ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ከድጃ ሲራጅ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ጥያቄን መነሻ ያደረገ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በአላባ ቆሉቶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
በተጠሪ እና በተከሳሽ አቶ ሐጂ መሐመድ ሐሉስ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ እንዱፈርስ መደረጉን ተከትል የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ተጠሪ አቅርባለች። የአሁኑ አመልካች ደግሞ ከተከሳሽ ጋር ከ1984ዓ.ም ጀምሮ በጋብቻ ተሳስራ ያለች መሆኗን ገልፃ የሚሰጠው ውሳኔ መብቷን የሚነካ ስለሚሆን ጣልቃ ገብታ ለመከራከር አመልክታለች። የከተማው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ጣልቃገብ ለመካፈል የጠየቀችው ንብረት በተጠሪ እጅ ያለ ከመሆኑም ላላ ይህንን ቤት የገነባች ለመሆኑ አልያም ወጪ ያወጣች ስለመሆኑ አላስረዲችም በሚል በቤቱ መብት የላትም ሲል አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጎ ተጠሪና ባለቤቷ ሐጅ መሐመድ ሐሉስ ለሁለት እኩል እንዱካፈለ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝታ ለአላባ ልዩ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረበች ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች ጠበቃ ጥቅምት 23 ቀን 2002ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የስር ፍ/ቤት አመልካች ነዋሪነቷ ሳውዱ አረቢያ በመሆኑ ገንዘብ ልካ ለጣውንቷ ቤት ትሰራለች ተብል አይታመንም የሚለው አገላለጽ የተሳሳተ መሆኑን ቤቱ የተሰራው የአመልካች ባለቤት/የሥር ተከሳሽ/ ከሳውዱ አረቢያ በላከው ገንዘብ ስለመሆኑ የአመልካች እና የስር ተከሳሽ ጋብቻ አሁንም ፀንቶ ያለ ስለመሆኑና በክልለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 71/2/ መሰረት በባለቤቷ ስም የተፈራ ንብረት የጋራ ስለመሆኑ ጠቅሰው በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ እንዱታረም አመልክተዋል።
የሰበር ችልቱም የሰበር አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ሚስት መሆኗ ካልተካደ እና ከባለቤቷ ጋር የምትኖር መሆኗ ከተረጋገጠ የንብረት ክፍፍል ድርሻ ጥያቄዋ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው ወይም አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። ተጠሪ መጋቢት 27 ቀን 2002ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። ይዘቱም አመልካች ከሐጅ መሐመድ ሐሉስ ጋር ጋብቻ ያልመሰረተች ስለመሆኑ ንብረቱንም በሚመለከት ቤቱ የተሰራው በተጠሪ እና ባለቤታቸው ሐጅ መሐመድ ሐሉስ የጋራ ጥረት ብቻ ስለመሆኑ ስር ፍ/ቤት በማስረጃ ስለማረጋገጡ አመልካች ንብረቱን በማፍራት ረገድ ያደረገችው አስተዋጽኦ ስለመኖሩ በስር ፍ/ቤት ጭብጥ አስይዛ ያላስረዲች መሆኑን በመዘርዘር በተጨማሪም ለማዘጋጃ ቤቱ ከ1990-2001ዓ.ም ድረስ ግብር ብር 16,516.50 ውስጥ ግማሽ ድርሻውን ብር 8,258.25 የከፈለ መሆኑን ጠቅሰው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል።
የአመልካች ጠበቃም የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው የመልስ መልስ በጽሐፍ አቅርበዋል።
እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃርና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል። ከመዝገቡ መረዲት የተቻለው ፍሬ ነገር አመልካች ከሐጅ መሐመድ ሐሉስ ጋር በ1984ዓ.ም ጋብቻ መስርታ አብረው ሳውዱ አረቢያ የሚኖሩ ስለመሆኑ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ በ1987ዓ.ም ከሐጂ መሐመድ ሐሉስ ጋር ጋብቻ የመሰረተች ሲሆን ባለቤቷ ለረዥም ዓመታት ውጪ አገር የሚኖር በመሆኑና እሷንም ወደ ውጪ እወስድሻለሁ ብል የገባውን ቃል ባለማክበሩ ፍቺ እንዱወስን ለመጠየቅ ምክንያት እንደሆናት ነው።
እንግዱህ ከዚህ መረዲት የሚቻለው ጉዲይ ተጠሪም ሆኑ አመልካች ከሐጅ መሐመድ ሐሉስ ጋር ጋብቻ መስርተው የነበሩ ስለመሆኑ ነው። የተጠሪ ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ እንዱፈርስ መደረጉን ተከትል የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ከመቅረቡ ወጪ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ተፈፀመ በሚል የቀረበ ክስ ስለመኖሩ አልተጠቀሰም። እንዱህ በሆነ ጊዜ ሁለቱም ሚስቶች በየፉናቸው ከአንድ ወንድ ጋር ጋብቻ መስርተው ሲኖሩ ቆይተው ጋብቻው በአንደኛዋ ተጋቢ ጥያቄ በፍቺ ሲፈርስ የንብረት ክፍፍል አፈፃፀም በምን መልክ ሉከናወን ይገባል የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀሬ ነው።
የፋዳራለም ሆነ የክልልች የቤተሰብ ሕግ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል የሚደነግገው ክፍል አንድ ጋብቻ ብቻ መኖርና መፍረስን ታሳቢ በማድረግ እንጂ ጋብቻ ላይ ጋብቻ ሲኖር የሚከተለውን ውስብስብ ጥያቄ ታሳቢ ያላደረገ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ምክንያቱም ሕጉ በጋብቻ ላይ ጋብቻ እንዲይፈፀም ግልጽ ክልከላ ያደረገ በመሆኑ ነው።
ሆኖም ግን በማህረሰቡ በተግባር እየተከናወነ ያለተግባር እንደመሆኑ ክርክር በተነሳ ጊዜ የሚሰጠው ውሳኔ ማህበራዊ ቀውስ እንዲያስከትል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የዲኝነት አካለ ኃላፉነት ይሆናል።
ስለሆነም የሕጉን መሰረታዊ ዓላማና ግብ ለማሳካት በሚቻልበት አግባብና ፍትሀዊ ውሳኔ ለመስጠት በሚያስችል አግባብ ለሕጉ ትርጉም መስጠት ተገቢ ይሆናል።
በተያዘው ጉዲይ ግራ ቀኙ የሚከራከሩት በአላባ ቆሉቶ ከተማ በ1250 ካ.ሜ ቦታ ላይ የተሰራ ቤትን በሚመለከት ነው። አመልካች በዚህ ቤት ላይ ከባለቤቷ ጋር ገንዘብ በማውጣት የሰራች መሆኑን በመጥቀስ የቤቱ ግማሽ (50 ) የባለቤቷ የተቀረው ግማሽ (50 ) ለእሷ እና ለተጠሪ እንዱካፈል እንዱወሰን የጠየቀች መሆኑን የወረዲው ፍ/ቤት ውሳኔ ይዘት ያመለክታል። ተጠሪ ደግሞ ይህንን ቤት የሰራችው በራሷ እና በባለቤቷ እንዱሁም ቤተዘመድቻቸው ጥረት መሆኑን ገልፃ ቤቱ የተጠሪ እና የባለቤቷ ብቻ እንደሆነ ትከራከራለች። በዚህ ረገድ የግራ ቀኙን ማስረጃ የሰማውና የመረመረው የወረዲ ፍ/ቤት አመልካች በቀጥታ ባለመብት ሉያደርጋት የሚያስችል አስተዋጽኦ ስለማድረጓ አላስረዲችም ሲል ደምድሟል።
ይልቁንም ቤቱ የተሰራው ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ከተፈፀመ በኋላ መሆኑን እና ተጠሪ ቤቱን ተቆጣጥረው ይዞታዋ ስር ያለመሆኑን በመጥቀስ በተሻለ ማስረጃ ባለመብት መሆኗን አረጋግጣለች ብሎል።
ይህንን የተረጋገጠ ፍሬ ነገር መነሻ አድርገን ከሕጉ ማገናዘብ ተገቢ ሆኖ አግኝተናል።
በመርህ ደረጃ ጋብቻ ሲፈርስ የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት እኩል የሚከፊፈል መሆኑ በፋዳራለ የቤተሰብ ሕግም ሆነ በክልለ ተቀባይነት ያለው መሰረት ሐሳብ ነው።የማጣራቱ ተግባርም በስምምነት አሉያም በሕጉ ሉወሰን ይችላል። ንብረቱ ሲጣራ ተጋቢዎች የግል ንብረታቸውን አስቀድሞ እንዱለዩና እንዱወስደ ከዚያም የጋራ ንብረት ላይ እኩል መብት እንዲላቸው ሕጉ ያመለክታል።
በተያዘው ጉዲይ ተጠቃሹ ቤት የተጠሪና የባለቤቷ የሐጂ መሐመድ ሐሉስ የጋራ ንብረት ነው ሲል የስር ፍ/ቤት ደምድሟል። የአመልካች ክርክር ባለቤቷ ሐጂ መሐመድ ሐሉስ ያፈራው ንብረት ነው ቢባል እንኳ በሕጉ ህሳቤ መሰረት ግማሽ ድርሻ ይገባኛል ባይናት።
የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 62/1/ እንደሚያመለክተው በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስት ከግል ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች የጋራ ሐብታቸው ይሆናለ። በተያዘው ጉዲይ አመልካች በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የተጠቀሰውን ንብረት ለማፍራት አስተዋጽኦ ስለማድረጓ አላስረዲችም ቢባልም በባሎ ጥረት የተፈራ ንብረትም ቢሆን የጋራ መብት እንደሚያስገኝላት ሕጉ ያመለክታል።
ምክንያቱም በጋብቻ ውስጥ እያለ የተፈራ ንብረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ሐብት ነው እስካልተባለ ድረስ የጋራ እንደሆነ ሕጉ ግምት የሚወስድ በመሆኑ ነው።
ስለሆነም ተጠቃሹን ቤት በተመለከተ ተጠሪ ቤቱ ላይ ቀጥታ አስተዋጽኦ ስለነበራት 50 /አምሳ በመቶ/ ድርሻ አላት ሲል የስር ፍ/ቤት የደረሰበትን ድምዲሜ ከማስረጃ የመነጨ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ነው ቢባልም በተቀረው 50 /አምሳ በመቶ/ ላይ አመልካች ድርሻ የላትም ልባል የሚገባ አይደለም ምክንያቱም በሕጉ አገላለጽና እሳቤ አመልካች ባለቤቷ በስሙ ያፈራው ንብረት ላይ ድርሻ እንዲላት ተመልክቷልና። ስለዚህም የስር ፍ/ቤቶች አመልካች በአከራካሪው ቤት ላይ ምንም ድርሻ የላትም ሲለ የሰጡት ውሳኔ የሕጉን መንፈስና ዓላማ በአግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
ስለዚህም አመልካች ከባለቤቷ ድርሻ ላይ እኩል የመካፈል መብት ይኖራታል ማለት ነው።
በክርክሩ ሑደት እንደተገለጠው በአመልካች እና በባለቤቷ /ሐጅ መሐመድ ሐሉስ/ መካከል ያለው ጋብቻ ያልፈረሰ በመሆኑ አከራካሪውን ንብረት ይካፈለታል ባይባልም አመልካች ድርሻ እንዲላት ሉታወቅ ይገባልና። በዚሁ መሰረት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በማረም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአላባ ቆሉቶ ከተማ የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ10/09/2001ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣ የአላባ ልዩ ወረዲ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ4/10/2001ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰበር መ/ በ05/02/2002ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽል ተከታዩ ተወስኗል።
በአላባ ቆሉቶ ከተማ በ1250 ካ.ሜ ቦታ ላይ የሰፈረው ቤት በሐጅ መሐመድ ሐሉስ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ተጠሪና ሐጅ መሐመድ ሑሉስ ለሁለት ከተካፈለ በኋላ በሐጅ መሐመድ ሐሉስ ድርሻ ላይ አመልካች እኩላታ መብት አላት ብለናል።
በዚህ መዝገብ መጋቢት 7 ቀን 2002ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.