No summary available.
ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ብሓራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ኃላ.የተ. የግል ኩባንያ ተጠሪ፡- ዲኒ ድሪሉንግ ኃላ.የተ. የግል ኩባንያ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ የጉድጓድ ቁፊሮ ሥራ ውል ስምምነትን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በግልግል ዲኝነት ጉባኤ ነው። በአመልካችና በተጠሪ የተቋቋመው የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ/ም በሰጠው ውሣኔ አመልካች ለተጠሪ ብር 579,450.35(አምስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ብር ከሰላሣ አምስት ሣንቲም) እንዱከፍል ወስኗል። ይህንኑ ውሳኔ አመልካች በመቃወም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 351 መሰረት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ታኅሣስ 17 ቀን 2001 ዓ/ም በፃፈት አራት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ በፍሬ ነገር እና በሕግ ረገድ ተፈፀሙ የሚለባቸውን ስህተቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ በራሱ አነሳሸነት ውለን ባቋረጠበትና ዉለን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት በላለበት ሁኔታ ተጠሪ ስራ ለፈታበት ሰላሳ አምስት ቀናት ብር 700,000. 00 ቅጣት አመልካች እንዱከፍል መወሰኑ የውልም ሆነ የሕግ መሰረት የላለው መሆኑን፣የግልግል ጉባኤ ዲኝነቱን የመራው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 317(1) ስር በተመለከተው ሣይሆን ከዚህ ውጪ ተገቢውን ጭብጥ ሣይይዝ መሆኑን፣ውሣኔው በፍትሐብሕር ሕጉ የተመለከቱትን የውል አተረጓጓም ድንጋጌዎችን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑን፣ተጠሪ በወቅቱ ማስጠንቀቂያ ባልሰጠበት ሁኔታም ቅጣት መጠየቅ እንደማይችል፣ተጠሪ ውለ አልተፈፀመልኝም የሚል እንደመሆኑ መጠን ሉደርስ የሚችለውን ኪሣራ ለመቀነስ በሕጉ ግዳታ ያለበት ሲሆን ጉዲት ሳይደርስበት ቅጣት እንዱከፈለው መጠየቁ ያላግባብ መሆኑንና በውለ ላይ ዓይነተኛ መጣስ የላለ ስለሆነ ውል እንዱፈርስ ዳኞች ውሣኔ ማሳለፍ እንደማይችለ፣እንዱሁም በጉዲዩ የተሰጠው ውሣኔ የቀረቡትን ማስረጃዎችን በሚገባ ያልመዘነ መሆኑን በሰፉው በመዘርዘር የግልግል ዳኞችና ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሣኔ በማስረጃ ምዘናም ሆነ በሕጉ አተረጓጓም እንዱሁም አፈጻጸም ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብል ሉሻር ይገባዋል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም ተጠሪን ያስቀርባል ተብል ጠበቃው መጋቢት 01 ቀን 2001 ዓ/ም በተፃፈ አራት ገፅ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። የመልሱ ይዘትም የጉባኤው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑን 23-05-1998 ዓ/ም ግራ ቀኙ በፈፀሙት ውል የተስማሙ መሆኑን ገልፀው ለሰበር ችልቱ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የማይቻል ስለሆነ በዚህ ምክንያት ችልቱ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ እንዱያደርግ፣ይህን የሚያልፍ ከሆነም ለአቤቱታው መሰረት የሆኑት የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ክርክሮች ተቀባይነት የላላቸው በመሆኑ ውድቅ ሉደረጉ ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው የሰበር ችልቱ ጉዲዩን ለማየት ሕገ-መንግስታዊ ሥልጣን ያለው መሆኑን በመዘርዘር የተጠሪ ጠበቃ መቃወሚያ የሕግ መሰረት የለውም በማለት የተቃወሙ ሲሆን ላልችን ነጥቦችን በተመለከተም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር መጋቢት 18 ቀን 2001 ዓ/ም በተፃፈት የመልስ መልስ ማመልከቻ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልጉት አበይት ጭብጦች፡- 1ኛ/ ግራ ቀኙ ባደረጉት ስምምነት መሰረት አመልካች ቅሬታውን ለሰበር ችልት ለማቅረብ ይችላል? ወይስ አይችልም?፣ 2ኛ/ አመልካች ለሰላሳ አምስት ቀናት የጉዲት ካሳ ለተጠሪ እንዱከፈል ተብል የተወሰነው የውሳኔ ክፍል በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው ውል መሰረት አመልካች ግዳታውን ስለአለመወጣቱ ተጠሪ አስረድቶ ነው ወይስ አይደለም? የሚለት ሲሆን ላልች ነጥቦች በዚሁ ጭብጥ ስር እልባት ሉያገኙ የሚችለ ሆነው ተገኝተዋል።
1.የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- ይህን ጭብጥ ለመመለስ በአገራችን ውስጥ የሰበር ስርኣት እና ስለአማራጭ ሙግት መፍቻ ዘዳዎች አላማና በሕጉ ያላቸውን ማእቀፍ መመልከቱ ተገቢ ነው።
የሰበር ስርዓት አይነተኛ አላማ ከሆኑት አንደ በአንድ ሀገር ውስጥ ወጥ የሆነ የሕግ አተረጎጎም እና አፈጻጸም(Uniform interpretation and application of the law ) መኖሩን ማረጋገጥ መሆኑ እሙን ነው። በዚህም መሰረት የሰበር ሥርዓት የሕግ የበላይነት ማረጋገጫ ዘዳ ነው ተብልም ሉታሰብ የሚችል ነው። የሕግ የበላይነት በሰበር ሥርዓት ሉከበር ወይም ሉረጋገጥ የሚችለው ደግሞ ጥራት፣ወጥነት ያለው ፍርድ/ ውሳኔ ለመስጠት ሥልጣን በተሰጣቸው አካለት በሰጡት ውሳኔ ላይ የዲኝነት አካለ በራሱ ዲኝነታዊ ቁጥጥር(Judicial Control) ሲኖረው መሆኑ ግልፅ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ተመሳሳይ ጉዲዮች በተመሳሳይ መንገድና ሁኔታ ማየትን የፍትሕ አሰጣጥ ሥርዓት የግድ የሚለው ጉዲይ ነው።
በልላ አገላለጽ የፍትሕ መሰረቱ ተመሳሳይ ጉዲዮችን በተመሳሳይ መንገድ ማሰተናገድ ነው ተብልም ይታሰባል። ይህ የሚተገበረውም አዋጆች፣ደንቦችና መመሪዎች እንዱሁም ፖሉሲዎች በትክክልና በወጥነት ሲተረጎሙና ሲፈጸሙ ነው።
ወጥነትና ትክክለኛነት ያለው የሕጎች አተረጎጎምና አፈፃፀም መኖሩ የሚረጋገጠው ደግሞ በዲኝነት አካለ በመጨረሻ ደረጃ በሚገኝ በሰበር ተቋም ነው።
ላላው ጉዲይ የሕጎች ወጥነት ያለው አተረጎጎምና አፈፃፀም መኖር የዜጎችን በሕግ ፉት እኩል የመሆን መብት የሚጠበቅ መሆኑ የሚታመን ሲሆን የዲኝነት አካለ የዜጎችን በሕግ ፉት እኩል የመሆን መብት የማክበርና የማስከበር ሕገመንግስታዊ ግዳታ የመወጣት ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ደግሞ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 13(1)፣ 25 እና 85(1) ድንጋጌዎች ስር ከአሰፈረው ሁኔታ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። የሰበር ሥርዓት ይህንኑ ግዳታ የዲኝነት አካለ የመወጣቱን ሁኔታ የሚቆጣጠርበት መሆኑም የሚታመን ነው። ላላው በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ተቀባይት ያለው ጉዲይ የሕግ ስህተት ያለበት ውሳኔ ፀንቶ ሉቆይ የማይገባው ጉዲይ መሆኑ ነው። የሕግ ስህተት ያለበት ውሳኔ ፀንቶ እንዱቆይ ማድረግ በዲኝነት አካለ የራሱ የሆነ አለታዊ ተጽእኖ ያስከትላል። ምክንያቱም የሕግ ስህተት ያለበትን ውሳኔ ጸንቶ እንዱቆይ ማድረግ ሕብረተሰቡ በዲኝነት አካለ እምነት እንዲይኖረው የሚያደረግ ነውና። በመሆኑም የሰበር ሥርአት የሕግ ስህተት ያለበት ውሳኔ ፀንቶ እንዲይቆይ በማድረግ የዲኝነት አካለ በሕብረተሰቡ ዘንድ የሚታመን፤ከበሬታ የተቸረው እንዱሆን ያደርጋል።
ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው የሰበር ሥርአት ለሕግ ስርዓቱ፣ለዲኝነት አካለና ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ተብል የሚቋቋም መሆኑን ነው። ይህ ስርአት በኢትዮጵያ የህግ ስርዓት ውስጥ ተካቶ ለረዥም ጊዜያት ሲሰራበት የቆየ ሲሆን በ1987 ዓ/ም የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት በአንቀፅ 83 ስር ተመልክቶ ከመገኘቱም በላይ ዝርዝሩ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አዋጅ ቁጥር 454/97 የተደነገገለት ሥርዓት ነው። የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት በአንቀፅ 80 ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ ስር የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፋዳራል ጉዲዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዲኝነት ሥልጣን እንዲለው ሲደነግግ በንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ስር ደግሞ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልለ ጉዲይ ላይ የበላይና የመጨረሻ የዲኝነት ስልጣን ይኖረዋል ሲል ደንግጓል። ሕገ-መንግስቱ በፋዳራልና በክልል ጉዲዮች የመጨረሻ የዲኝነት ስልጣን ያላቸውን ፍርድ ቤቶች ለይቶ ካስቀመጠ በኋላ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ስልጣን ያለው መሆኑን በአንቀጽ 80(3(ሀ)) ስር ደንግጓል። ሰበር ችልት ይህ ስልጣን የተሰጠው ከላይ የተመለከቱትን አላማዎች ለማሳካት መሆኑ የሚታመን ነው። በተለይ አዋጅ ቁጥር 454/1997 ሲታይ ከአምስት ያላነሱት ዳኞች በተሰየሙት ችልት የሚሰጥ የሕግ ትርጉም ይኸው ችልት ራሱ በልላ ጊዜ እስካልለወጠው ድረስ በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤት ላይ የአስገዲኝነት ኃይል(Precedence) ያለው ስለመሆኑ በአንቀፅ 2(4) ስር አስቀምጧል። ይህም የሰበር ስርዓት በዲኝነት ስልጣን ተዋረድ በመጨረሻ እርከን ላይ ሆኖ ሕጎች በትክክልና በወጥነት መተርጎማቸውንና መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል፣ለተከራካሪ ወገኖች ጥቅም ወይም መብት ብቻ ሳይሆን ለዜጎች ጥቅም ተብል የተዘረጋ ሥርአት ወይም አሰራር መሆኑን ነው። በመሆኑም ሰበር ሕጋዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች የሚሰበሩበት ወይም ጸንተው እንዲይቆዩ የሚደረግበት ሥርአት ነው። በልላ አገላለፅ ሰበር መደበኛ የይግባኝ ማቅረቢያ አሰራር ሳይሆን ፍርድ ቤቶች በውሳኔዎቻቸው ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል በሚባልበት ልዩ ሁኔታ ብቻ የሕጉ አተረጎጎም ወይም አተገባበር የሚቃናበት ወይም የሚታረምበት ሥርዓት ነው። በዚህም ሥርአት የሕግ አንድ ወጥ አተረጎጎምና አፈፃፀም በፍርድ ቤቶች ሁለ ይረጋገጣል።
ወደ አመራጭ የሙግት መፍቻ ዘዳዎች አላማ ስንመለስ ደግሞ ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸውን ከፍርድ ቤት ውጪ በግልግል ዲኝነት ለመጨረስ የመስማማት መብት ያላቸው መሆኑን ያሳዩናል። የግልግል ዲኝነት የሚቋቋምበት አይነተኛ አላማ ተካራካሪዎቹ ወገኖች ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በመሄድ የሚያጠፈትን ጊዜና ገንዘብ ለማስቀረት መሆኑ የሚታመን ነው።
ጉባኤው የሚቋቋመውም በተካራካሪ ወገኖች ስምምነት ሲሆን ተካራካሪዎቹ ባላቸው የመዋዋል ነፃነት ጉዲያቸውን ከፍርድ ቤት ውጪ በግልግል ዲኝነት ለመጨረስ የሚስማሙት ሁኔታ መኖሩ በራሳቸው ፍላጎትና ምርጫ የተቋቋመው ጉባኤ በተገቢው ጊዜና በአነስተኛ ወጪ ጉዲያቸውን ለመወሰን ይችላል የሚል እምነት ኑራቸው ነው ተብል ይታሰባል። በፍ/ብ/ሕጉ ከቁጥር 3325 እስከ 3346 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንዱሁም በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ከቁጥር 315-319 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ይህንኑ የሚያስገነዝቡን ሲሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 350(2) በተለይ ሲታይ ደግሞ ተከራካሪ ወገኖች የግልግል ዲኝነት ጉባኤ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል በሚል ለመስማማት መብት ያላቸው ስለመሆኑ ያስረዲናል።
በዚህ ሁኔታ ስምምነት ከተደረሰም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 356 ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች በስተቀር የጉባኤው ውሳኔ በፍርድ እንዱሻርላቸው ለመጠየቅ እንደማይችለ ተደንግጓል። ይህ ተከራካሪ ወገኖች የግልግል ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ ስምምነት ያላቸው ከሆነ የሚፈፀም ስነ ስርዓት ሲሆን ስምምነት ባይኖርም ይግባኝ የሚቻለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 351 ስር በተመለከቱት ውስን ምክንያቶች ብቻ ነው። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 351"ም" ሆነ 356 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለው የግልግል ጉባኤ ውሳኔ በሰበር ስርዓት የሚታይበት አግባብ ስለመኖሩ አይጠቁምም። በልላ አገላለፅ ድንጋጌዎች የሚያወሱት በግልግል ታይቶ የተወሰነ ጉዲይ በይግባኝ የሚታይበትን ሥርዓት ብቻ ነው። በፍ/ብ/ሕጉ ከቁጥር 3325 እስከ 3346 ድረስ በተመለከቱት ድንጋጌዎችና በፍትሒ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸውን በግልግል ለመጨረስ መሰረቱ ሕጋዊ ውል መኖሩ ሲሆን ውል ደግሞ የተከራካሪ ወገኖች መብትና ጥቅም ማስገኛ ምንጭ ነው። በልላ አገላለፅ ውለ መብትና ጥቅም የሚሰጠው ለተዋዋይ ወገኖች ወይም መብትና ጥቅሙ በሕጉ አግባብ ለተላለፈላቸው ለላልች ሶስተኛ ወገኖች ነው(የፍ/ህ/ቁጥር 1731 እና 1957 ይመለከቷል)።እ ንዱሁም ተዋዋይ ወገኖች ጉዲያቸውን ከፍርድ ቤት ውጪ ለመጨረስ መብት ያላቸው መሆኑ በሕጉ ተቀባይነት ያለው ሲሆን ሕጉ ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ ያላቸውን ሚናም ደንጓጓል።
እነዚህ ድንጋጌዎች በ1952ቱ የፍትሐብሕር ሕግና በ1958ቱ የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕጋችን ውስጥ ያለት ሲሆኑ ከእነዚህ ሕግጋት በኋላ የወጡት የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስትና አዋጅ ቁጥር 25/1988 እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 454/97 ስለሰበር ሥርዓት ደንግገው እናገኛለን።
የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በማናቸውም የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ስልጣን ያለውና የሚሰጠው የሕግ ትርጉምም በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት እስካልተለወጠ ድረስ የፋዳራልንም ሆነ የክልል ፍርድ ቤቶችን የሚያስገደድ መሆኑ በሕጉ የተቀመጠና አላማው በአገሪቱ ወጥ የሆነ የሕግ አተረጎጎምና አፈጻጸም እንዱኖር ማረጋገጥ ነው ከተባለ ተከትል ሉነሳ የሚችለው ጥያቄ በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዳዎች ከሆኑት አንደ በሆነው በግልግል ዲኝነት (arbitration) ጉዲዩ ቢታይና ይኸው አካል በጉዲዩ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ይግባኝ የላለው የመጨረሻ ስለመሆኑ(Arbitration Finality Clause) ተከራካሪ ወገኖቸ ገልፀው ስምምነት ቢያድርጉ ጉዲዩ በሰበር ላታይ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለው ነው። ይኸው ጥያቄም ስለሰበር ሥርዓት አላማና ከሕጎዎቹ አወጣጥ ቅደም ተከተል እንዱሁም በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት ውስጥ ፍርድ ቤቶች በአማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዳዎች ላይ ካላቸው ሚና አንፃር ታይቶ ምላሽ የሚሰጠው ነው። በዚህም መሰረት ከላይ እንደተመለከተው የሰበር ሥርዓት ዓላማ ወጥ ለሆነ የሕግ ትርጉም እና አፈፃጸም ከፍተኛ ሚና መጫወት ሲሆን ይህንንም በ1987ቱ ሕገ-መንግስትም ሆነ ይህንኑ ተከትለው ከወጡ አዋጆች(25/1988 እና 454/97) የምንገነዘበው ነጥብ ነው። እነዚህ አዋጆች ከ1958ቱ የፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ በሁዋላ የወጡ ሲሆን ተቀባይነት ባለው የሕግ አተረጎጎም ደንብ መሰረትም ከ1958ቱ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ቅድሚያ ተፈጻሚነት ያላቸው ናቸው። አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዳዎች በኢትዮጵያ የሕግ ስርዓት ውስጥ ተካተው የሚገኙ ሲሆን እነዚህን የሙግት መፍቻ ዘዳዎች ፍርድ ቤቶች የሚያበረታቱበት ሁኔታ እንዲለ ሁለ የሚቆጣጠሩበት አጋጣሚም ያለ መሆኑን ከላይ የተመለከቱት የፍትሒ ብሓር ሕጉም ሆነ የፍትሒ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያሳያል። በመሆኑም የአንድ ጉዲይ ለሰበር የመቅረብ ሁኔታ በሕገ መንግስቱ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠ በመሆኑ ሥርዓቱ ሉጫወተው ከተፈለገው አቢይ አላማ አንፃር ሲታይ ጉዲያቸው በግልግል ዲኝነት እንዱታይላቸው የተስማሙበት ወገኖች የግልግል ዲኝነቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው በማለት ስለተስማሙ ብቻ ጉዲዩ በሰበር ሥርዓቱ እንዲይታይ ፍላጎት አሳይተዋል ተብል መሰረታዊውን የሕግ ስህተት ላለማረም ምክንያት ላሆን የሚችል አይደለም። በዚህም ምክንያት ይህ ሰበር ችልት በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ ሁለት ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸውን በግልግል ዲኝነት( Arbitration) ለመጨረስ ከተዋዋለና የግልግል ዲኝነት ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል በማለት በውላቸው ላይ ከተስማሙ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ውሳኔ ለሰበር ችልት ቀርቦ ላታይ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀፅ 2(4) መሰረት መለወጥ ያለበት ሁኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተጠሪ የአመልካች አቤቱታ በሰበር ችልት ላቀርብና ላታይ የሚገባ አይደለም በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለናል።
2.ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡ተጠሪ ውለን ማቋረጡን ሳይክድ የሰላሳ አምስት ቀናት ቅጣት አመልካች እንዱከፍለው ዲኝነት የጠየቀውንና የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ብር 700,000.00(ሰባት መቶ ሺህ) አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ውሳኔ ያሳረፈው በአመልካችና በተጠሪ መካከል በጥር 23 ቀን 1998 ዓ/ም የወርቅ ጉድጓድ ቁፊሮ ውል ተፈፅሞ፣ቅድሚያ ክፍያ በየካቲት 09 ቀን 1998 ዓ/ም ተከፍል ስራው መጀመር ከሚገባበት ቀን ሰላሳ አምስት ቀናት በመዘግየት በ30—7-1998 ዓ/ም ለመጀመሩ ምክንያቱ አመልካች ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ነው። አመልካች በዚህ ረገድ ኃላፉነት የላለበት መሆኑን ገልፆ የሚከራከረው የማዕድን ፍለጋ ጉድጓድ ቁፊሮ ወደሚካሄድበት ቦታ የሚያድረሰውን ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ አመቺ የሆነ መዲረሻ መንገድ የማዘጋጀት ኃላፉት የራሱ መሆኑ በውለ መገለጹን ሳይክድ ይህንኑ ግዳታ ለመወጣት ቡልድዘሩን ከተጠሪ መከራየቱን፣ሆኖም በሁለት ቀናት ውስጥ ቡልድዘሩን ወደ መቀላ ለማጓጓዝ የሚያስችል መኪና አዘጋጅቶ ለማስጫን በሚሄድበት ጊዜ የቀረበው ቡልድዘር ለታቀደው ስራ ብቃት የላለው መሆኑ በአመልካች ኤክስፏርት በመረጋገጡና ይህ ሁለ ሲደረግ ተጠሪ የወሰደት አንዲችም እርምጃ የለም በሚል ነው። ተጠሪ በዚህ ሰበር ችልት ባቀረበው ክርክር የአመልካች ክርክር በስር የግልግል ዲኝነት ያልተነሳ ነው በማለት ከመከራከር ውጪ ከላይ የተመለከተው ግዳታ በግራ ቀኙ መካከል መገባቱን በግልፅ አይክድም። ይሁን እንጂ አመልካች በስር የግልግል ዲኝነት ጉባኤው ከላይ የተመለከተውን ክርክር ያነሳ መሆኑን የግልግል ጉባኤ ውሳኔ ግልባጭ በገጽ 3 እና 4 ያሰፈረው በመሆኑ ተጠሪ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329(1)መሰረት በማድረግ ያነሳው ተቃውሞ ተቀባይነት የላለው ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካች ክርክር ውድቅ ሆኖ ለሰላሳ አምስት ቀናት የቅጣት ገንዘብ እንዱከፍል የመወሰኑን አግባብነት ስንመለከተው ደግሞ ምላሹ ከግራ ቀኙ ውል፣ክርክርና ስለውልች አተረጓጎም በጠቅላለው በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት መታየት ያለበት ጉዲይ ነው።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጥር 23 ቀን 1998 ዓ/ም የተደረገው ውል አመልካችን ለባከነ ጊዜ ክፍያ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ በአንቀጽ 4፣3.11 እና 9.1 ስር ካስቀመጣታቸው ድንጋጌዎች እንገነዘባለን። በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት አመልካች ለተጠሪ ኃላፉነት የሚኖረው የመቆፈሪያው መሳሪያ ከአመልካች ጋር በተያያዘ ኃላፉነት ያለስራ ቢቀመጥ ስለመሆኑ ተቀምጧል።ድንጋጌዎቹ በግልፅ እንደሚያሳዩት የባከነ ጊዜ ክፍያ(Idle time Payment) የመቆፈሪያው መሳሪያ በስራ ላይ እያለ ውል ሰጪ በሆነው አመልካች ምክንያት ቢቆም፤መሳሪያው ስራ ለመስራት እየቻለ ቁሞ ያላግባብ ለጠፊው ጊዜ፣አመልካች ኃላፉ የሚሆንበትን ሁኔታ የሚያሳዩ ናቸው። በልላ አገላለፅ የመቆፈሪያ ማሽን(Rig) በስራው ቦታ ላይ ተገኝቶ በአመልካች ምክንያት ስራ ቢፈታ አመልካች ኃላፉነቱን የሚወሰድ መሆኑን ያስገነዝባል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ለሰላሳ አምስት ቀናት ስራ ፈታሁ ይበል እንጂ በአመልካች ምክንያት ስራ መፍታቱን በፍሬ ነገር ደረጃ አልተረጋገጠም። ተጠሪ ስራውን የፈታሁ በአመልካች ምክንያት ነው ብል እስከተከራከረ እና አመልካችም ለመሳሪያው መቆም ምክንያት የሆነው ድርጊት በራሱ በኩል የተፈጸመ አለመሆኑን ገልፆ እስከተከራከረ ድረስ ክሱን የማስረዲት ሽክም ከሳሽ የሆነው ወገን የተጠሪ ግዳታ ነው።
የመቆፈሪያው መሳሪያ ከስራ ቦታ አለመድረሱ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። የግልግል ጉባኤው አመልካችን መሳሪያው ስራውን ለፈታበት ጊዜ ኃላፉነት አለበት በማለት ውሳኔ ላይ የደረሰው ከላይ የተጠቀሱትን የውለን ድንጋጌዎች በመጥቀስና መቆፈሪያ መሳሪያ ወደ ስራ ቦታ ተጓጉዞ የሚሄድበትን መንገድ አመልካች ሉያዘጋጅ አልቻለም፣የድዘር ኪራይ ውልን መሰረት በማድረግ ክስ አልመሰረተም በሚል ነው። ሆኖም ተጠሪ ስራውን ከሚያዚያ 01 ቀን 1998 ዓ/ም ጀምሮ መስራት እንደሚችል በፁሐፍ ተነግሮት ሚያዚያ 12 ቀን 1998 ዓ/ም ስራው መጀመሩ፣የሰላሳ አምስት ቀናት ጊዜ ባክኗል የተባለው ደግሞ ከየካቲት24 ቀን 1998 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 30 ቀን 1998 ዓ/ም ድረስ ስለመሆኑ በስር ክርክር የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች ናቸው።
ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው የመቆፈሪያ ማሽኑ ወደ ስራ ቦታው በመሄድ በአመልካች ምክንያት ስራውን መስራት ያልቻለ መሆኑን ሳይሆን ከመነሻውም መቆፈሪያ ማሽኑ ወደ ስራ ቦታ ያልተጓጓዘ መሆኑን ነው።በግራ ቀኙ ውል አንቀፅ 3.11 ስር የተቀመጠው ድንጋጌ የመቆፈሪያ መሳሪያ ከአሰሪው ጋር በተያያዘ ኃላፉነት ያለስራ ቢቆም ….በሚል ሐረግ የተቀመጠ ሲሆን ይህም ድንጋጌ በግልጽ መሳሪያው ከስራ ቦታ መድረሱንና ደርሶ ስራ መስራት እየቻለ በአመልካች ምክንያት ስራውን ሳይሰራ ቢቀር አመልካች ኃላፉነት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው።ግልፅ ውል ሉተርጎም የማይገባ መሆኑን ደግሞ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1733 ድንጋጌ ያስረዲል። የግልግል ጉባኤ ውለ ግልፅ ሆኖ እያለ እና ተጠሪ አመልካች ለባከነው ጊዜ ምክንያት መሆኑን ባላስረዲበት ሁኔታ የተጠሪን የማስረዲት ሸክም ወደ አመልካች በማዞር አመልካች ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት የደረሰበት መሆኑን አላስረዲም በማለት ለባከነ ጊዜ ቅጣት እንዱከፍል ሲል የሰጠው የውሳኔ ክፍል የግራ ቀኙን ክርክርና የውል ይዘት በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች ስለማስረዲት ሽክም የተቀመጡትን ሥርዓቶች፣በፍ/ብ/ሕጉ ከቁጥር 1732 እስከ 1738 ድረስ ስለውልች አተረጎጎም ከተመለከቱት ደንቦች ጋር ያላገናዘበና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
ስለሆነም አመልካች መቆፈሪያ ማሽኑ ስራ ሳይሰራ በመቆሙ ምክንያት ባከነ ለተባለው ለሰላሳ አምስት ቀናት ብር 700,000.00(ሰባት መቶ ሺህ ብር የሚከፍልበት ሕጋዊ ምክንያት ስለላለ በዚህ ረገድ የተሰሰጠው የውሳኔ ክፍል ሉለወጥ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል አመልካች ለተጠሪ በውለ መሰረት ለተከናወኑ ስራዎች መከፍል አለባቸው ተብለው የታሰቡት፤የሞቪላዜሽን ሂሳብ( ብር 90,000.00)፣ለ661.77 ሜትር ጥልቀት ጉድጓድ ቁፊሮ ሂሳብ(ብር 704,124.00)፣ለኬዚንግ ስራ(ብር138,000430.00)፣ለቁፊሮ ስራ ከጉድጓድ ወደ ጉድጓድ ለተደረገ እንቅስቃሴ የሚታሰብ(ብር 4,150.00)፣ስራ ላይ ለዋለ አምስት ከረጢት ሲሚንቶ የሚታሰብ(ብር 750.00)፣ከውሃ ቦቴ ኪራይ የሚታሰብ(50,000.00)እና የድዘር ኪራይ(ብር 3,818.40) በጠቅላላ ድምር ብር 991,272.40(ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሁለት ብር ከአርባ ሳንቲም) ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮበት ብር 1,139,962.86 (አንድ ሚሉዮን አንድ መቶ ሰላሳ ዘጥ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከሰማኒያ ስድስት ሳንቲም)እንዱከፍል የተወሰነውን የውሳኔ ክፍል ስንመለከተው በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን ውል፣ክርክርና ማስረጃ መሰረት አድርጎ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካች የሰበር ቅሬታ ተቀባይነት የላለው ሆኖ ተገኝቷል። ከዚህም በተጨማሪ አመልካች ክፍያ ለዘገዬበት ብር 40,321.60(አርባ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ አንድ ብር ከስልሳ ሳንቲም) ለተጠሪ እንዱከፍል መወሰኑም ፍሬ ነገርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በዚህ ችልት ላታይ የሚገባው ባለመሆኑ በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበውን ቅሬታ አልተቀበልነውም።
ላላው አመልካች ተጠሪ ውለን በራሱ ጊዜ አቋርጦ መሄደ ያላግባብ ነው በማለት በተከሳሽ ከሻስነት በግልግል ጉባኤው ያቀረበው ክርክር የታለፈው ባግባቡ አይደለም በማለት የሚከራከርበትን ነጥብ ስንመለከተውም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1786 እና 1788 ድንጋጌዎች አንጻር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
በአጠቃላይ በግልግል ጉባኤ ታይቶ በሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑን አንድ ተከራካሪ ወገን ቢስማማም ጉባኤው በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚል ወገን ቅሬታውን ለሰበር ችልቱ ከማቅረብ የሚከለከል ባለመሆኑና ጉባኤው አመልካች የሰላሳ አምስት ቀናት መቆፈሪያው ያለስራ ለቆመበት አመልካችን ተጠያቂ ያደረገበት አግባብ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ በመገኘቱ፣እንዱሁም ጉባኤው ወጪና ኪሳራ ያሰላበት አግባብ ይህ ችልት ለአመልካች የሚቀንሰውን የገንዘብ መጠን መሰረት ባደረገ መንገድ የሚሰራ ሆኖ በላልች ነጥቦች ጉባኤው የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ሆኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ 1.ይህ ሰበር ችልት በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ ሁለት ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸውን በግልግል ዲኝነት( Arbitration) ለመጨረስ ከተዋዋለና የግልግል ዲኝነት ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል በማለት በውላቸው ላይ ከተስማሙ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ውሳኔ ለሰበር ችልት ቀርቦ ላታይ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀፅ 2(4)መሰረት ተለውጧል።
2 ሁለት ተከራካሪ ወገኖች ጉዲያቸውን በግልግል ዲኝነት(Arbitration) ለመጨረስ ከተዋዋለና የግልግል ዲኝነት ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል በማለት በውላቸው ላይ ከተስማሙ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ ውሳኔ ለሰበር ችልት ቀርቦ ላታይ የሚችል ነው ብለናል።
3.አመልካች ለተጠሪ የሰላሳ አምስት ቀናት ቅጣት የተባለውን ብር 700,000.00(ሰባት መቶ ሺህ ብር) ለተጠሪ ለመክፈል የሚገደድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት በዚህ ረገድ የግልግል ጉባኤ የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ሽረነዋል።
4.ወጪና ኪሳራን በተመለከተ የግልግል ጉባኤው የሰጠው የውሳኔ ክፍል አመልካች ብር 700,000.00(ሰባት መቶ ሺህ ብር) ለተጠሪ ሉከፍል አይገባም ተብል በዚህ ችልት የተሰጠውን ውሳኔ ግንዛቤ ባስገባና በጉባኤው ስላት መሰረት የሚሰራ ሁኖ በወጪና ኪሳራ፣በጠበቃ አበል እንዱሁም በላልች ነጥቦች ላይ የግልግል ጉባኤው የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
5.በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.