No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን - ዐ/ህግ ወርቅነህ ዓለማየሁና ታደለ ተስፊዬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዲንኤል መኮንን አልቀረቡም በዚህ መዝገብ የቀረበውን ጉዲይ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው አቤቱታ ተጠሪ የተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት በሕግ አያስጠይቀውም በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ነው ሲል አመልካች ይኸው እንዱታረም በመጠየቁ ነው።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ ተጠሪው ነሐሴ 22 ቀን 1996 ዓ.ም መጠኑ 46.96(አርባ ስድስት ነጥብ ዘጠና ስድስት) ኪ.ግ የሆነ የሀገር ውስጥ ጥፍጥፍ ወርቅ በሕገወጥ መንገድ ከአገር ለማስወጣት ወደ ጅቡቲ በማጓዝ ላይ እያለ በክትትል በወለንጪቲ እና በመተሐራ መካከል በመያዙ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89 በአዋጅ ቁጥር 368/95 እንደተሻሻለው አንቀጽ 2(28) እና አንቀጽ 66/2/ በመተላለፍ የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈጽሟል በማለት ክስ የቀረበበት ሲሆን በአማራጭ የገንዘብ እና የባንክ አዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59/2/ለ ሥር የተጠቀሰውንና የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ስለወርቅ ግብይት ቁጥጥር ያወጣውን መመሪያ ቁጥር CTG/001/97 አንቀጽ 1 እና 2 በመተላለፍ በሕገ-ወጥ መንገድ ወርቅ ሲያዘዋውር በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ወንጀል ፈጽሟል በማለት አመልካች ተጠሪ ላይ ክስ መስርቷል።
ተጠሪ ሥር ፍ/ቤት ቀርቦ ድርጊቱን አልፈጸምኩም ጥፊተኛም አይደለሁም ብል ክድ ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የመጀመሪያውን ክስ በተመለከተ ተጠሪ በመከላከያ ማስረጃ አስተባብለዋል በማለት ከክሱ በነፃ እንዱሰናበቱ ወስኗል። በአማራጭ የቀረበውን ክስ በተመለከተ በማስረጃ ተረጋግጧል በማለት በክሱ መሰረት ጥፊተኛ ነው ሲል ፈርዶል። ቅጣቱንም በተመለከተ ጥፊተኛ በተባለበት አዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59/2 (ለ) መሰረት በአምስት ዓመት (5) ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ብር አንድ ሚሉዮን የገንዘብ መቀጮ እንዱከፍል የተያዘው ወርቅ በመንግሥት እንዱወረስ እና ለሦስት (3) ዓመት ጊዜ ምስክር ከመሆን መምረጥ እና ከመመረጥ መብት ተገድቧል በማለት ወስኗል።
በዚህ የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ ላይ ተጠሪ ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ 1ኛው ክስ የኮንትሮባንድ ወንጀል ስለመፈጸሙ የዐ/ሕግ ማስረጃ አላረጋገጠም በማለት ሲወስን በአማራጭ የቀረበውን ክስ በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59/2/(ለ) ላይ ወርቅን አስመልክቶ ያስቀመጠው ክልከላ የለም፤ መመሪያ ቁጥር 001/97 ሕግ ሆኖ አስገዲጅነት እንዱኖረው በአዋጅ ቁጥር 3/87 እና 14/88 መሰረት በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ያልወጣ እንዱሁም በአማርኛ ቋንቋ ያልተፃፈ በመሆኑ ሕግ ሆኖ ቅጣት ሉጥል አይችልም በወንጀል ተጠያቂ ሉያሰኝ አይችልም በሚል ምክንያት ተጠሪው እንዱከለከል ብይን መስጠቱ ተገቢ አልነበረም ሲል በውሳኔው ሐተታ ገልጿል።
በፍሬ ነገር ረገድም ወርቁን ወደ ጅቡቲ ሳይሆን ወደ ጎንደር ያጓጓዘ መሆኑን በመከላከያ ማስረጃ በተሻለ ሁኔታ አረጋግጧል በሚል የሥር ፍ/ቤት ጥፊተኛ በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት እንደለላው ወስኗል።
ባጠቃላይ በሕግም ሆነ በፍሬነገር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ ስሕተት ነው በማለት ተጠሪ(ተከሳሽ) በነፃ እንዱሰናበት ወስኗል።
የአሁን አመልካች በዚህ ፍርድ ቅር ተሰኝቶ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ጠቅላይ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ተጠሪ በአማራጭ የተከሰሰበት ድርጊት መመሪያው በሕግ መልክ ስላልወጣ የወንጀል ክልከላ ተደርጓል ልባል አይችልም በማለት የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ አፅንቷል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሕገወጥ የወርቅ ዝውውር አስመልክቶ አዋጅ ቁጥር 52/85 እና 83/86 መሰረት አድርጏ የወጣው የብሓራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር CTG/001/97 ተፈጻሚነት ያለው ስለመሆኑ መመሪያው በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ያለመውጣቱ ሕጋዊነቱን እንደማያሳጣው፣ መመሪያው በአማርኛ ቋንቋ ያልተፃፈው ከብሓራዊ ባንክ የሥራ ባህርይ የተነሳ ስለመሆኑ እንዱሁም ወንጀል ድርጊቱ የቅጣት አወሳሰን አዋጁ ወይም የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 357 እና 358 ተፈጻሚነት ሉኖረው እንደሚገባ በመጥቀስ የይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ተሽሮ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና አመልክቷል።
የሰበር ችልቱም የቀረበውን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በዚህ ጉዲይ በአማራጭ የቀረበውን ክስ አስመልክቶ በአዋጅ መሰረት የወጣው መመሪያ በአማርኛ ተተርጉሞ ያለመገኘቱ ሁኔታ በጉዲዩ ላይ የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው? መመሪያው ተፈጻሚ ነው ከተባለ ተፈፀመ የተባለውን ድርጊት ሉሸፍን የሚችል ነው ወይስ አይደለም?
ይህም ቢታለፍ የገንዘብ እና የባንክ አዋጅ ቁጥር 83/86 በ1949 ዓ.ም ከወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 357 እና 358 አንፃር ሲታይ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ጥፊተኛ ልባል አይገባም በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። የተጠሪ ጠበቃ ህዲር 23 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ቀርበው የግራ ቀኙ ክርክርም በችልቱ ተሰምቷል።
በተጠሪ ጠበቃ በኩል የተነሱት የመከራከሪያ ነጥቦች ሥር ፍ/ቤት የባንክ ሥራ ሰርቷል ተብል ክስ ያልቀረበ ስለመሆኑ የኮንትሮባንድ ወንጀል ነው ተብል የቀረበው ክስ ውድቅ ስለመደረጉ በአማራጭ የቀረበው ክስም አዋጅ እና መመሪያ ከመጥቀስ ውጪ ድርጊቱን በተመለከተ ጥፍጥፍ ወርቅ አዘዋውሯል እንዲልተባለ መመሪያው ተፈጻሚነት ሉኖረው እንደማይገባ እንዱሁም የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 357 እና 358 መመሪያው ሕጋዊነት የላለው በመሆኑ ተፈጻሚነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክረዋል። በዚሁ አግባብ የሥር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱፀና አመልክተዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍሲል በአጭሩ የተመለከተው ሲሆን እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
ከፍሲል እንደተጠቀሰው በዚህ ሰበር ችልት እንዱመረመር የተያዘው የመጀመሪያው ጭብጥ በብሓራዊ ባንክ የወጣው መመሪያ ቁጥር ሲቲጂ/001/97 በአማርኛ ተተርጉሞ ያለመውጣቱ በጉዲዩ ላይ የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው? የሚለውን አስቀድመን እንመረምራለን። ለዚህ ጭብጥ ምላሽ ለማግኘት የሕጎች ተዋረድ እና አወጣጥ በመጠኑም ቢሆን መዲሰስ ተገቢ ይሆናል። በመርህ ደረጃ ሕግ የማውጣት ሥልጣን በሥልጣን ክፍፍል መርህ መሰረት የሕግ አውጪው አካል ስለመሆኑ ግልፅ ነው። በሕግ አውጪው የመንግስት አካል የሚወጡ ሕጎች ቀዲማዊ /primary legislations/ ተብለው የሚታወቁ ሲሆን ላልቹ እንደአስፈላጊነታቸው አግባብ ባለው አካል የሚወጡ የበታች ሕጎች (subsidiary legislations) ተብለው የሚታወቁ ናቸው። ሕግ አውጪው የመንግሥት አካል በተለያዩ ቴክኒካዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ቀዲሚውን ሕግ ለማስፈጸም የሚያስችለ ዝርዝር ሕጎች ያስፈልጋለ ብል ባመነ ጊዜ ጉዲዩ በቀጥታ የሚመለከተው አካል የበታች ሕጎችን እንዱያወጣ ሥልጣን ሲሰጥ ይስተዋላል። ይህ አሰራር በሕግም በምክንያትም የተደገፈ እና የዲበረ ልምድ ስለመሆኑ ግልፅነው። አሁን በተግባር ሥራ ላይ ያለው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 14/88 አንቀጽ 2(1) እንደሚያመለክተው ሕግ የሚላቸው አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ሲሆኑ እነዚህ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲወጡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ መውጣት እንዲለባቸው ያመለክታል። ነገር ግን ከፍ ሲል እንደተመለከትነው በላልች የመንግሥት አካላት የሚወጡት የበታች ሕጎች ማለትም ደንቦች እና መመሪያዎች በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዱወጡ የሚያስገድድ ድንጋጌ በዚህ አዋጅ አልተመለከተም። ከዚህም ላላ ከመነሻውም ይህ አዋጅ ቁ.14/88 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት የሚመለከት እንደመሆኑ በላልች አካላት የሚወጣን የበታች ሕግ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት አስመልክቶ ምላሽ የሚሰጥ አይደለም። በርግጥ በዚህ ረገድ የላልች ሀገሮች ልምድ ሲታይ በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የሚወጡት የበታች ሕጎች ሥነ ሥርዓታዊ ጉዲዮች የሚወሰነው የአስተዲደር ሥነ ሥርዓት ሕግ በሚሰኝ የሕግ ዓይነት መሆኑን የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በዚህ ረገድ በሀገራችን የወጣ ሕግ የለም። ይህም በመሆኑ በየአስፈጻሚ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚወጡ የበታች ሕጎች እንዱታተሙ እና በተወሰነ ቋንቋዎች እንዱፃፈ የሚያስገድድ ሕግ የለንም። ከዚህም የተነሳ በርካታ የበታች ሕጎች በተለያዩ ተቋማት በተለያየ መልክ ወጥተው በተግባር ላይ ውለው እናገኛለን። በተለይም መመሪያ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሲወጣ አልተስተዋለም።
በተግባር ያለው እውነት ይህ መሆኑን የምንረዲው ከመሆኑ አንፃር አሁን በእጃችን ያለው ጉዲይ ስንመለከት ብሓራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ ቁጥር ሲቲጂ/001/97 በአማርኛ ቋንቋ አልተፃፈም በነጋሪት ጋዜጣም አልታተመም ሲለ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ ይህ እንዱደረግ የሚያስገድድ ግልፅ ሕግ በላለበት ሁኔታ እና በተግባር ያለውን እውነታ ባለማገናዘብ በመሆኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ይህ አካሄድም በተግባር ሥራ ላይ ያለትን በርካታ መመሪያዎች ተፈጻሚነት ዋጋ የሚያሳጣ ነውና። ይልቁንም ለዚህ መመሪያ መውጣት ዋና ወይም እናት ሕግ የሆነው አዋጅ ቁጥር 83/86 ለባንኩ ሥልጣን ስለመስጠቱ መመሪያው በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን ለማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የተቀረፀና የሚጣጣም ስለመሆኑ በማገናዘብ ውጤት በሚያስገኝ እና የእናት ሕግ ዓላማና ግብ ለማስፈጸም በሚያስችል አግባብ ተግባራዊ እንዱሆን ማድረግ ይገባል የሚል እምነት አለን። ስለሆነም መመሪያው በአማርኛ ቋንቋ አልተፃፈም በሚል ምክንያት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉታረም ይገባል ብለናል።
በሁለተኛ ደረጃ የተያዘው ጭብጥ የመመሪያውን ተፈጻሚነት የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ መረዲት እንደተቻለው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶቹ መመሪያው የወንጀል ድንጋጌ የለውምና ተፈጻሚነት የለውም በማለት የመ/ደረጃ ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽረዋል። በዚህ መሰረት በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ምክንያት አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 39/2/ እና ተያያዥ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መመርመር ተገቢ ነው። በተያዘው ጉዲይ ባንኩ ተጠቃሹን መመሪያ ያወጣው በአዋጁ አንቀጽ 39/2/ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ስለመሆኑ የመመሪያው መግቢያ ዐረፍተነገር ያመለክታል። በአዋጁ አንቀጽ 39/2/ የተመለከተው ድንጋጌ የሚያስገነዝበን ስለወርቅና ስለውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ባንኩ መመሪያ ማውጣት ስለመቻለ ነው። ከዚህ ድንጋጌ እና ከአዋጅ አጠቃላይ መንፈስ መረዲት የሚቻለው የገንዘብ እና የወርቅ ሥራ እንቅስቃሴ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን አለታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት በመመልከት በተለየ ሁኔታ ሥርዓት እንዱበጅለት እና ቁጥጥር እንዱደረግበት የታሰበ ስለመሆኑ ነው። ይህንንም ለማሳለጥ ይቻል ዘንድ በአዋጁ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች በተጨማሪ ባንኩ በዝርዝር መመሪያ ሉወሰን እንዱችል ሥልጣን የተሰጠው መሆኑን ያመለክታል።
ስለሆነም መመሪያው በአንቀጽ 1 እና 2 ስለወርቅ ንግድና ዝውውር መያዝ ወይም ማኖር የባንኩ ፈቃድ አስፈላጊነት እና የመጠኑም ገደብ አስመልክቶ ድንጋጌ ይዟል። ይህ ድንጋጌ ሲጣስ በየትኛው ሕግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው ደግሞ ራሱ ዋናው አዋጅ ሆኖ እናገኛለን። ይህም አዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59(1)(ሸ) ላይ እንደተመለከተው አዋጁን ወይም አዋጁን ተከትል የወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን የተላለፈ ሰው የሚቀጣበትን አግባብ ደንግጓል። ስለሆነም የወንጀል ተጠያቂነትን አስመልክቶ የተደነገገው በአዋጁ መሰረት መሆኑን እንረዲለን። ከዚህ አንፃር በመመሪያው የተመለከተውን ገደብ በመተላለፍ ለተፈፀመ የወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት በአዋጁ በተመለከተው አግባብ የሚፈፀም በመሆኑ በተያዘው ጉዲይ ላይም መመሪያው ተፈጻሚነት አለው ብለናል።
መመሪያው ተፈጻሚነት አለው ካልን በኋላ በተጠሪ ተፈፀመ የተባለው ድርጊት በዚህ መመሪያ የሚሸፈን ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን እንደሚከተለው መርምረናል። በተጠሪ ላይ ሥር ፍ/ቤት በአማራጭ የቀረበው ክስ በባንኩ የወጣውን መመሪያ በመተላለፍ ያለባንኩ ፈቃድ ከአሥር(10) አውንስ በላይ ወርቅ ሲያዘዋውር ተገኝቷል የሚል ሲሆን ተጠሪም በክሱ የተጠቀሰውን 46.96 ኪ.ግ ወርቅ ይዞ መገኘቱን አልካደም። ይልቁንም ጎንደር ከተማ ለሚገኝ ደንበኛው የሸጠ መሆኑንና ወደዚያው እንዱጓጓዝ ማድረጉን የእምነት ቃለን ሰጥቷል።
ስለሆነም በፍሬ ነገር ረገድ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠው ባንኩ ካወጣው መመሪያ ውጭ ያለባንኩ ፈቃድ እውቅና ከፍተኛ ዋጋ ያለው የወርቅ መጠን ማዘዋወሩና ስለመያዙ ነው። ይህ ድርጊቱ በመመሪያው አንቀጽ 1 እና 2 የተመለከተውን ክልከላ የተላለፈ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬነገር ነው። ስለዚህም የተጠሪ ድርጊት በመመሪያው የሚሸፈንና የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ሆኖ አግኝተናል።
ተጠሪ የፈፀመው ድርጊት በአዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 39/2/ ለባንኩ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የወጣውን መመሪያ ቁጥር ሲቲጂ 001/97 አንቀጽ 1 እና 2 የተላለፈ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 59/1//ሸ/ መሰረት ጥፊተኛ የሚያሰኝና ቅጣት የሚያስከትል ሆኖ ተገኝቷል። የቅጣት አወሳሰን በተመለከተ በዐ/ህጉ በሥር ፍ/ቤት በቀረበው ክስ እና የመ/ደረጃ ፍ/ቤት ከወንጀለ አፈጻጸም ባህሪይ እና ከተፈፀመው ድርጊት ዓላማና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከደረሰ ጉዲት አንፃር በአዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59(2)(ለ) ሥር በተመለከተው አግባብ የተወሰነው ጥፊተኛነት እና ቅጣት ዓይነትና መጠን መሰረታዊ የሕግ ጉድለት አለው ለማለት የሚያስችል የሕግ ምክንያት ስላላገኘንበት ባለበት እንዱፀና ብለናል።
የተጠሪ ጥፊት እና የቅጣት አወሳሰን በአዋጅ ቁ.83/86 እና በመመሪያው የተሸፈነ መሆኑን ከፍሲል ስለተመለከትን ከወንጀለኛ መቅጫ ሕግ /የ1949 ዓ.ም ወ/መ/ሕግ/ አንቀጽ 357 እና 358 አንፃር ለመመርመር የተያዘው ጭብጥ መመርመር አስፈላጊ ስላልሆነ አልፈነዋል።
ሲጠቃለል ተጠሪ በአማራጭ በቀረበበት ክስ ጥፊተኛ አይደለም ሲለ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከፍሲል በዝርዝር በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል። በዚሁ መሰረት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይ/ወ/መ/ ሐምል 23 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/መ/ ህዲር 26 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2)ሀ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በወ/መ/ ግንቦት 24 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኛነት ውሳኔ እና ቅጣት ፀንቷል።
ተጠሪ ላይ የተሰጠው የእስራት ቅጣት በዚህ ወንጀል እስከ አሁን የታሰረው ታሳቢ ተደርጏ ቀሪው እንዱፈፀምበት ብለናል። የፋዳራል ፖሉስ ተጠሪን ይዞ ለማረሚያ ቤት እንዱያስረክብ እና ማረሚያ ቤቱም ይህንኑ እንዱያስፈጽም ታዟል። ይፃፍ።
የገንዘብ መቀጮ እና የሚወረሰውን ንብረት በተመለከተ አመልካች ተከታትል እንዱያስፈጽም ብለናል።
ይፃፍ
No topics extracted.