No summary available.
ሚያዝያ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ማሞ ገ/ማሪያም ተጠሪ፡- የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድና የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ችልት የሰጡት ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች በተከሰሰበት የወንጀል ክስ በቀነ ቀጠሮ እየቀረበ የሚከራከር ስለመሆኑ ዋስትና ይሆን ዘንድ በሞዳል 85 በደረሰኝ ያስያዘው ብር 200/ሁለት መቶ/ ብር ነው። አመልካች በተከሰሰበት ወንጀል ከፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሣሥ 9 ቀን 2002 ዓ.ም በነፃ የተሰናበት መሆኑን በመግለጽ ያስያዘው ገንዘብ እንዱመለስለት ሲጠይቅ ገንዘብ ያስያዝክበት ዋናውን ደረሰኝ ካላቀረብክ አይመለስልህም በማለት የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካችን ጥያቄ በድምጽ ብልጫ ውድቅ አድርጏታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለተጠሪ ያቀረበ ቢሆንም የሰበር ችልቱ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበለውም። አመልካች በተከሰስኩበት ወንጀል በነፃ የተለቀቅሁ መሆኑን በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ በማቅረብ አስረድቻለሁ። ገንዘብ ያስያዝኩበት ደረሰኝ ስለጠፊብኝ ኮፒውን ይዜ በመቅረብ እንዱከፈለኝ ያቀረብኩት ጥያቄ የበታች ፍርድ ቤቶች አለመቀበላቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር አመልካች ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ቀርቦበት የነበረውን የወንጀል ክስ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠውን ቀነ ቀጠሮ እያከበረ የሚቀርብና የሚከታተል ለመሆኑ ዋስትና ይሆን ዘንድ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በሞዳል ሰማኒያ አምስት እስይዞ ጉዲዩን ሲከታተል የነበረ መሆኑንና ከተከሰሰበትም ወንጀል በነፃ የተሰናበት መሆኑን የመንግስት ሰነድ የሆኑት የፍርድ ቤት መዝገቦችና በውሣኔው ግልባጭ በማየትና በማጣራት ለማረጋገጥ ይቻላል።
አመልካች ያስያዘው ገንዘብ አይመለስልህም የተባለው ገንዘቡን ገቢ ያደረገበት ዋናው ደረሰኝ ሣይሆን የዋናው ኮፒ ይዞ በመቅረቡ ነው። በአርግጥ በሰነድ የተገለፀን ፍሬ ጉዲይ ለማስረዲት ማቅረብ የሚገባው ዋናው ሰነድ መሆን እንዲለበት (Best evidence rule) መሰረታዊ መርህ ለመረዲት ይቻላል። ሆኖም ዋናው ሰነድ ሉገኝ በማይችልበት ሁኔታ የዋናው ሰነድ ኮፒ/Secondary evidence/ በማቅረብ ጉዲዩን ከማስረዲት የማይከለክል መሆኑን በስፊት ተቀባይነት ያላቸውን የማስረጃ ሕግ መርሆች በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ ገንዘቡን ያስያዘው አመልካች ስለመሆኑ አመልካች ይዞት በቀረበው የደረሰኝ ኮፒ ብቻ ሣይሆን በወንጀል ተከስሶ ጉዲዩ ከታየበት የጊዜ ቀጠሮ መዝገቦችና ክርክሩን ተከታትል በነፃ ከተለቀቀበት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል መዝገብ ጋር በአንድነት አጣምሮ በመመዘን ለማረጋገጥ ይቻላል። ስለሆነም አመልካች በአደራ በሞዳል 85 ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ያስያዘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አቅርቦ እያለ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ያቀረብከው ማስረጃ ዋናውን ደረሰኝ ሣይሆን ፍቶ ኮፒውን ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የሰበር ችልት የሰጡት ትእዛዝ ተሽሯል።
አመልካች በሞደል 85 በደረሰኝ ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ይመለስላቸው ብለናል።
ይኸ ፍርድ በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.