No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት - ጠበቃ አርአያ ጌታሁን - ቀረቡ ተጠሪ፡- ዶ/ር ጌታሁን ሽብሩ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁ. 410/96 በተመተላለፍ የመብት ጥሰት ተፈጽሞአል በሚል የቀረበውን የካሣ ጥያቄ መነሻ በማድረግ የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ከሣስሽ የነበረው ተጠሪ ነው። ክሱም እንዲየነው ርቱዐ ኢምላክ በሚል የብዕር ስም “የተሰበሩ ክንፍች” በሚል ርዕስ ትርጉም መጽሐፍ አዘጋጅቶ መስከረም 24 ቀን 1999 ዓ.ም በተደረገ ውል ተከሣሽ(የአሁኑ አመልካች) 5000(አምስት ሺህ) ኮፒ እንዱያትምለት መስጠቱን፣ተከሣሽም በስምምነቱ መሰረት የህትመቱን ጠቅላላ ዋጋ ግማሽ ብር 14,929.50(አስራ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ዘጠኝ ብር ከሃምሣ ሣንቲም) ተቀብል ህትመቱን በሦስት የስራ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ ግዳታ መግባቱን፣ነገር ግን ስራው ተጠናቆ ተጠሪ ከመረከቡ በፉት “የተሰበሩ ክንፍች” በሚል ስያሜ የታተመው መጽሐፍ ቅጂዎች በላልች ሰዎች (ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሣሽ ተብለው በክሱ ተመዝግበው በነበሩት) አማካይነት በገበያ ውስጥ ሲሸጥ መገኘቱን ይገልፃል። በመጨረሻም ቁሳዊ እና የሞራል ጉዲት ደርሶብኛል በማለት በጠቅላላው ብር 160,079.50 (መቶ ስልሳ ሺህ ሰባ ዘጠኝ ብር ከአምሳ ሳንቲም)እንዱከፈል እንዱወሰን ይጠይቃል።
አመልካች እና ተጣምረው የተከሰሱት ሰዎችም የየበኩላቸውን የመከራከሪያ ነጥቦች በማንሳት ከክሱ በነጻ ይሰናበቱ ዘንድ የተከራከሩ ሲሆን፣ፍ/ቤቱም ክርክሩንና ክርክሩን ለመደገፍ የቀረቡትን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ፣መጽሐፈን ሲሸጡ ተገኝተዋል የተባለትን ተከሣሾች በነፃ በመልቀቅ አመልካች ላይ ለደረሰው የመብት ጥሰት ተጠያቂ ነው ብልአል። በዚህ መሰረትም ተጠሪ በቁሳዊ እና በሞራል ረገድ ለደረሰበት ጉዲት ካሣ እንዱከፈለው ወስኖአል። ይህን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም የአመልካችን ክርክር ባለመቀበል ውሳኔውን አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁ.
410/96 አንቀጽ 8 መሰረት የሞራል ካሣ የማግኘት መብት ተፈፃሚ የሚሆነው ለስራው ተርጓሚ ጭምር ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው።
ተጠሪ መጽሐፈን ተርጉሞ እንዱታተምለት ለአመልካች በውል ስለመስጠቱ አከራካሪ አይደለም። መጽሐፈ ታትሞ ለተጠሪ ከመድረሱ በፉት በገበያ ሲሸጥ ስለመገኘቱም በስር ፍ/ቤቶች በማስረጃ ተረጋግጦአል። በሰበር ችልቱ ከቀረበው አቤቱታ ዋነኛ መሰረት ሆኖ በአመልካች የተጠቀሰው የመከራከሪያ ነጥብ ተጠሪ የመጽሐፈ ደራሲ ሳይሆን፣ተርጓሚ በመሆኑ እንደ ድርሰቱ አመንጪ ተቆጥሮ የሞራልና የቁሳዊ ጉዲት ካሣ ሉወሰንለት አይችልም የሚል ነው። ተጠሪ ደግሞ የቅጅ መብትም እንደድርሰት መብት እውቅና ያገኘና ጥበቃ የተደረገለት በመሆኑ የሞራልም ሆነ የቁሳዊ ጉዲት ካሣ እንዲገኝ መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት የመከላከያ ክርክሩን አሰምቶአል።
ለክርክሩ አወሳሰን ተገቢነት ያለው ሕግ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁ.410/96 ነው። ይህን አዋጅ ማውጣት ያስፈለገው የአንድን ሃገር ባህላዊ፣ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ሳይንሳዊና ቴክኖልጂያዊ ልማትን በማፊጠን ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወቱት የስነ ጽሁፍ፣የኪነጥበብ እና ተመሣሣይ የፈጠራ ስራዎች የሚበረታቱበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚያስችል በመታመኑ እንደሆነ ከአዋጁ መግቢያ አጠቃላይ መንፈስ መገንዘብ ይቻላል። በዚህ አዋጅ የሕግ እውቅና ሉሰጣቸውና ጥበቃ ላደረግላቸው ይገባል ከተባለት የፈጠራ ስራዎች አንደ የስነ ጽሐፍ ስራ ሲሆን፣ይህም ከድርሰት ስራዎች ጋር የሚያያዝ ነው። በያዝነው ጉዲይ አከራካሪ ሆኖ የቀረበው ነጥብም ድርሰትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በተጠሪ የተሰራው የትርጉም ስራ በሕጉ እውቅና የተሰጠውና ጥበቃ የሚደረግለት ስለመሆን አለመሆኑ በተመለከተ መልስ ሉገኝ የሚችለው የአዋጁን ዝርዝር ድንጋጌዎች በመመልከት ነው።
አመልካች የተጠሪ ስራ በሕጉ ጥበቃ የተደረገለት አይደለም በማለት የተከራከረው ተጠሪው በእንግሉዝኛ ቋንቋ የተሰራውን የድርሰት ስራ ወደ አማርኛ ቋንቋ መለስ(ተረጏመ) እንጂ ስራውን (ድርሰቱን) አላመነጨም ከሚል መነሻ ነው። በመሆኑም አንድ ሰው የአንድ ስራ አመንጪ ወይም የፈጠራ ባለቤት ነው ልባል የሚችለው ምን አይነት ስራ ሰርቶ ሲገኝ ነው? የሚለው ነጥብ አግባብነት ካለው የአዋጁ ድንጋጌ ጋር አገናዝቦ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። “የሥራ አመንጪ” የሚለው ሐረግ በአዋጁ አንቀጽ 2/2/ ትርጉም ተሰጥቶታል። በዚህ ትርጓሜ መሰረት የስራ አመንጪ የሚባለው የአንድን የአእምሮ ውጤት የሆነን ስራ የፈጠረ ማንኛውም ግለሰብ ነው።
እዚህ ላይ ግልጽ ሆኖ የሚታየው ስራው የአእምሮ ውጤት መሆን እንዲለበትና ይህ ሁኔታ መሟላቱ ሲረጋገጥም በሕግ እውቅና የሚያገኝና ጥበቃም የሚደረግለት እንደሆነ ነው። ጥበቃ ለማግኘት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎችም በአዋጁ አንቀጽ 6 የተቀመጡ ሲሆን፣ለያዝነው ጉዲይ አግባብነት ያለው ንኡስ አንቀጽ/1/ ማንኛውም የስራ አመንጪ የስራው አላማና የጥራት ደረጃ ግምት ውስጥ ሳይገባ ስራውን በማውጣቱ ምክንያት ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥበቃ እንደሚያገኝ ያመለክታል። በእርግጥ ስራው ጥበቃ ያገኝ ዘንድ ወጥ(ኦርጂናል) ላሆን ይገባል። እንደዚሁም የተቀረጸ ወይም ግዙፍነት ያገኘ መሆን ይኖርበታል። በማለትም ሕጉ ደንግጓል።
ተጠሪ በእንግሉዝኛ ቋንቋ የተሰራውን ድርሰት(መጽሐፍ) ወደ አማርኛ ቋንቋ ለመተርጏም ሲነሳ ዓላማ ያደረገው መጽሐፈ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በሆነ ህብረተሰብ ዘንድ እንዱታወቅና እንዱነበብለት እንደሆነ መገመቱ አይከብድም። ቋንቋ የተናጋሪውን ህብረተሰብ ባህልና ወግ መሰረት ያደረገ ወይም ከእነዚህ ጋር ከፍተኛ ትስስር ያለው በመሆኑ በአንድ ቋንቋ የተፃፈን መጽሐፍ(ድርሰት) ወደ ላላ ቋንቋ ሲተረጏም ባህልና ወጉም ግምት ውስጥ እየገባ እንደሆነ ወይም ላሆን እንደሚገባም መገመት ይቻላል። ተጠሪ የሰራው ስራ መታየት ያለበትም ከዚህ አንፃር ነው። በእንግሉዝኛ ቋንቋ የተፃፈውን መጽሐፍ ወደ አማርኛ ቋንቋ ሲመልስ(ሲተረጉም) የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው (አንባቢው) የድርሰቱን ባህርይ በትክክል እንዱገባውና ከራሱ ባህልና ወጉ ጋር አገናዝቦ እንዱያጣጥመው በሚያስችለው ሁኔታ አመቻችቶ እንደሚያዘጋጀው ይታወቃል። ይህን ስራ የሚሰራው አእምሮው በፈቀደለት መጠን እውቀቱን በመጠቀም ነው። በአጭሩ የትርጉም ስራው የአእምሮው ጭማቂ ወይም ውጤት የታከለበት ነው ማለት ይቻላል። በዚህ መልክ ያለው ስራም በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈ(ከእንግሉዝኛው የተለየ) መጽሐፍ በመሆኑ በአንቀጽ 6/1/ እንደተደነገገው ወጥ(ኦርጅናል) የሆነና ግዙፍነትም ያገኘ ስራ ነው። በመሆኑም ተጠሪ የስራው አመንጪ አይደለምና ጥበቃ አይደረግለትም በማለት አመልካች ያቀረበው የመከራከሪያ ነጥብ የሕግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። ሕጉን መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ ስንመለከትም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል ለማለት አልቻልንም።
348/1/ መሰረት ጸንተዋል።
አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ተጠሪ የሞራልና የቁሳዊ ጉዲት ካሣ ሉያገኝ ይገባል መባለ ተገቢ ነው ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪራሣቸውን ይቻቻለ።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.