No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 396ዐ8 የካቲት 11 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አስቴር አርአያ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
ወ/ሮ አምሳለ በላይ - ጠበቃ ተሾመ ገ/እግዚአብሓር ቀረቡ።
ወ/ሮ ጥበበ ተገኔ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የንግድ ማኀበር ሥራ አስኪያጆች ለማያደርሱት ጥፊት ለአባላቱ ያለባቸውን ኃላፉነት የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የጀመረው በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት ከሳሾች የነበሩ ሲሆን ክስ ያቀረቡት በአሁኗ አመልካችና ዶ/ር አለኸኝ መኮንን በተባለት ግለሰብ ላይ ነው።
በክሳቸውም ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው ብር 15ዐ,ዐዐዐ /አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ/ የሚያወጡ እጣዎችን ለመግዛት ተስማምተው በተለያዩ ጊዜ ለተከሣሾቹ በቀጥታና በላልች ሰዎች አማካኝነት የአሜሪካን ድላር እንደከፈለ፣ እንዱሁም ለጋዜጣ ማውጫና ለኮምፒውተር መግዣ ለተከሳሾቹ ገንዘብ መክፈላቸውን፣ ዶ/ር አለኸኝ መኮንን የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በዚህ መዝገብ አመልካች የሆኑት ደግሞ ከታህሣሥ 24 ቀን 1999 ዓ.ም. ከሥራ አስኪያጁ በተቀበለት ውክልና መሰረት ማኀበሩን በሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ እንደነበረ፣ ተከሣሾቹ ማኀበሩን አቋቁመናል ከሚለ በቀር እንዲችም እንቅስቃሴ እንዲላደረጉ፣ የማኀበሩ ካፒታል ነው የተባለው አንድ ነጥብ አንድ ሚሉዮን ብር (1,100,000)የማኀበሩ ደረሰኝ እንዱቆረጥለት ተጠይቀው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን፣ በዚህ ምክንያት ማኀበሩ ስለከሰረ እንዱፈርስ መወሰኑን፣ ተከሣሾቹ ማኀበሩን ያቋቋሙት በቅን ልቦና ነግድ ለማትረፍ ሳይሆን የንግድ ስሙን ሽፊን በማድረግ ከላልች ሰዎች ላይ ገንዘብ ለመውሰድ መሆኑን በመግለጽ ተከሣሾቹ የወሰደትን ገንዘብ በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ ወለድን ጨምሮ ብር 912,733(ዘጠኝ መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ስላሳ ሶስት) እንዱከፍለ ጠይቀዋል። የሥር አንደኛ ተከሣሽ የነበሩት ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ ተጠሪዎች አዋጣን የሚለት ገንዘብ ከ1ዐ ዓመት በፉት ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ነው፤ ገንዘቡን አዋጣን የሚለትም ለማኀበሩ ስለሆነ ማኀበሩን ከሚጠይቁ በስተቀር አንደኛ ተከሣሽን መጠየቅ አይችለም፣ አንደኛ ተከሣሽ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከተጠሪዎች ገንዘብ አልተቀበለም፣ ስለሆነም የአንድነት ኃላፉነት የለባቸውም፣ አንደኛ ተከሣሽ ሥራ አስኪያጅ የነበሩ ቢሆን ሥራውን የካሂደ የነበሩት ሥር ሁለተኛ ተከሣሽ /በዚህ መዝገብ አመልካች/ ስለሆኑ ስለ ሂሣቡ ሉጠየቁ የሚችለት እሳቸው ናቸው በማለት ክርክር አቅርበዋል። አመልካች በበኩላቸው ተከፈለ የተባለውን ገንዘብ ተከሣሽ አንድ ላይ የተቀበልነው ስላልሆነ ተጣምረን ልንከሰስ አይገባም፤ ተጣምረን ባንከሰስ ኖሮ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አይኖረውም፤ ገንዘቡ ተሰጠ ከተባለ 1ዐ ዓመት ስለሚያልፈው ይርጋ ያግደዋል፤ ክሱ ላቀርብ ይገባ የነበረው ማኀበሩ እንዱፈርስ በተጠየቀበት መዝገብ ስለነበር በድጋሚ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም፣ ተጠሪዎች ለአመልካች በሁለት ቼክ ከፈልን ካለት በስተቀር ገንዘብ ስለመክፈላቸው የቀረበ ማስረጃ የለም፣ የተቀበልኩትንም ገንዘብ ለማኀበሩ ገቢ አደረኩ እንጂ በግላ አልበለፀኩም፣ ኃላፉነቱ የተወሰነ ማኀበርተኛ ካዋጣው መዋጮ በላይ ኃላፉ ላሆን የማይችልበት ነው፣ ማኀበሩ በመፍረሱ አመልካችም እንደ ላልቹ አባላት ጉዲት የደረሰብኝ በመሆኑ ሥራ አስኪያጅ ስለነበርኩ ብቻ በክስ ለተጠየቀው ገንዘብ ኃላፉ ልሆን አይገባም በማለት ክሱ እንዱሰረዝላቸው ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ መቃወሚያዎቹን ውድቅ ካደረገ በኋላ ተከሣሽ በሕግና በንግድ ልማድ አግባብ መሰረት የማኀበሩን ሂሣብ የመያዝና የሂሣብ መዛግብት ሪኮርድ የማስቀመጥ ግዳታ እንዲለባቸውና የሥራ አስኪያጅነት ኃላፉነታቸውን በትጋትና በጥንቃቄ መሥራት እንዲለባቸው በመመስረቻ ጽሁፈና በንግድ ሕጉ ላይ የተመለከተውን ግዳታቸውን ባለመወጣት የማኀበሩን ንብረት ለግል ጥቅማቸው አውለውም ሆነ በልላ መልኩ አለአግባብ እንዱበካክን አድርገዋል ስለዚህ በን/ሕ/ቁ 53ዐ መሰረት በአንድነትና በነጠላ ኃላፉ ናቸው በማለት ተከሣሾች ብር 3ዐዐ,ዐዐዐ /ሦስት መቶ ሺህ/ ገንዘብ ገቢ ተደርጓል ከተባለበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን የሥር አንደኛ ተከሣሽም በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ይግባኝ አቅርበዋል። ነገር ግን ፍ/ቤቱ በሁለቱም መዝገቦች የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቷል።
አመልካች ፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 319ዐ7 በሰጠው ውሣኔ በዚህ መዝገብ አንደኛ ተከሣሽ የነበሩት ደግሞ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በሰጠው ውሣኔ ላይ ቅር በመሰኘት በመ/ቁ 4ዐ866 የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ይህ የሰበር ችልትም በሁለቱም መዝገቦች አመልቾች ኃለፉ የመባላቸውንና ላልች ተያያዥ ነጥቦችን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። በዚሁ መሰረት በሁለቱም መዝገቦች ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። በሁለቱም መዝገቦች የቀረበው ጉዲይና ተከራካሪዎቹም ተመሣሣይ በመሆናቸው ችልቱ ሁለቱን መዝገቦች አጣምሮ መርምሯል።
No topics extracted.
ከፍ ሲል እንደተገለፀው ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት ከሥር ተከሣሽ ጋር በመሆን “ፈታሄ ቴክኒካል ኢንኮርፖሬትድ /ኢትዮጵያ/ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር” የተባለ የንግድ ድርጅት ለመመስረት በመስማማት እያንዲንዲቸው ብር 15ዐ,ዐዐዐ (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) የሚወጣ እጣ ለመግዛት ገንዘብ አዋጥተው የነበረ ቢሆንም የማኀበሩ ሥራ አስኪያጆች የተጣለባቸውን ኃላፉነት በአግባቡ ባለመወጣት ገንዘቡን ስላባከኑና ድርጅቱ ስለፈረሰ ገንዘቡን እንዱከፍለ ነው። ተጠሪዎች ድርሻቸውን ብር 3ዐዐ,ዐዐዐ(ሦስት መቶ ሺህ) ስለማዋጣታቸው በጋዜጣ ማስታወቂያ ከመገለጹም በተጨማሪ የሥር ፍ/ቤት የማኀበሩ ሂሣብ በባለሙያ ተጣርቶ ከቀረበው ሪፖርት ተጠሪዎች ገንዘብ ማዋጣታቸውን አረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ ከክርክሩ ሂደት የሥር አንደኛ ተከሣሽ የነበሩት የማኀበሩ ሥራ አስኪያጅ እንደነበሩና እሳቸውም በነበራቸው ስልጣን በዚህ መዝገብ አመልካች ለሆኑት ውክልና ሰጥተዋቸው አመልካችዋ በውክልና ማኀበሩን ሉያስተዲድሩ የነበሩ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም ሥራ አስኪያጆች ማኀበሩን ሲያስተዲድሩ በሰሩት ሥራ ኃላፉ የሚሆኑበትን የሕግ አግባብ መመልከት ተገቢ ይሆናል።
በተያዘው ጉዲይ ተከሾች ሲያስተዲድሩት የነበረው ማኀበር ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ሲሆን የዚህ ማኀበር ሥራ አስኪያጆች ያለባቸው ኃላፉነትም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 53ዐ ሥር ተመልክቷል። በዚህ መሰረት በንግድ ሕጉ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ወይም የማኀበሩን የመተዲደሪያ ደንብ በመጣስም ቢሆን በሥራ አስኪያጅነታቸው በሰሯቸው ጥፊቶችም ስህተቶችም ቢሆን በማኀበሩና በ3ኛ ወገኖች ፉት በየራሳቸው ወይም በአንድነት ሳይከፊፈል እንደ ነገሩ ሁኔታ ኃላፉዎች እንደሆኑ ያመለክታል በተያዘው ጉዲይ የሥር ተከሣሾች ማኀበሩን በሥራ አስኪያጅነት በጋራ ሲመሩ እንደነበር ተረጋግጧል። በልላ በኩል ደግሞ የማኀበሩን ሂሣብ የሰሩት የሂሣብ ባለሙያዎች የማኀበር ሂሣብ መርምረው ማኀበሩ የገቢና ወጪ ሰነድ እንደላለው፣ ኦዱት ተደርጎ እንደማያውቅ፣ ማኀበሩ ገንዘብ የሚያስቀምጥበት የባንክ ሂሣብ እንደላለው አወጣሁ ለሚላቸው ወጪዎችም በሕግ አግባብ የወጪ ሰነድች እንደላለት፣ ማኀበሩ ምንም ሥራ ያልጀመረ ቢሆንም ለደመወዝ፣ለቤት ኪራይና ለአበል የካፒታለን 88.38% ወጪ ማድረጉንና በአጠቃላይ የማኀበሩ አሰራር ትክክል እንዲልነበረ አብራርቷል። ተጠሪዎች በሥራ አስኪያጅነታቸው የማኀበሩን ሥራ አካሄድ፣ የማኀበሩን የሂሣብ አሰራር እና አያያዝ ላልችንም የማኀበሩን ሥራዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ በትጋትና በቅን ልቦና መስራት በሕግም በመተዲደሪያ ደንባቸውም የተጣለባቸው ኃላፉነት ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ግን ሥራ አስኪያጆቹ ማኀበሩ ሥራ ሳይጀምር የካፒታለን 88.38% ለቤት ኪራይ፣ ለደመወዝና ለአበል ወጪ በማድረግ፣ በአጠቃላይ የማኀበሩ አሰራር ኃላፉነት በጎደለውና በማንኛውም መለኪያ ትክክል ባልሆነ መንገድ ሲሰሩ እንደነበር ተረጋግጧል። በመሆኑም የሥር ተከሳሽ ሥራ አስኪያጆች ሆነው ሲሰሩ በሰሩት ጥፊትም ሆነ ስህተት በግል ሆነ በአንድነት ተጠያቂ ሉሆኑ እንደሚችለ የንግድ ሕጉ ቁጥር 58ዐ ስለሚያስረዲ የሥር ፍ/ቤት በዚህ መዝገብና በመ/ቁ. 4ዐ866 አመልካቾች ኃላፉነት አለባቸው በማለት ውሣኔ መስጠቱ በአግባቡ ነው። በልላ በኩል ተጠሪዎች ለአመልካቾች ከድርሻቸው መጠን ካዋጡት ገንዘብ ላላ ተጨማሪ ገንዘብ ለሁለቱ አመልካቾች መስጠታቸውን በመግለጽ ገንዘቡ እንዱከፈላቸው የጠየቁ ቢሆንም ለዚህ ያቀረቡ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ አመልካቾቹ ማዋጣታቸው የተረጋገጠው ብር 3ዐዐ,ዐዐዐ /ሶስት መቶ ሺህ/ ብቻ ገንዘቡ ከተዋጣበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር እንዱከፍለ መወሰኑ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል። በአጠቃላይ የሥር ፍ/ቤት በሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 4425ዐ ግንቦት 27 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ አና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 319ዐ7 ሐምል 9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
የዚህ ውሣኔ ግልባጭ ከመ/ቁጥር 4ዐ866 ጋር ይያያዝ
በዚህ መዝገብ ጥር 7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ትዕዛዙ ለሚመለከተው ክፍል ይተላለፍ።