No summary available.
የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ብርሃን ፀጋዬ - አልቀረቡም ከተባለ በኋላ ጠበቃ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. አቶ ሚካኤል ፍስሐ - ቀረቡ 2ኛ. ናሰው ኮንስትራክሽን - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የሽርክና ውል የሚመለከት ነው። ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው ክስ የተመሰረተው በአመልካች አማካይነት ነው። የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ከአንደኛ ተጠሪ ጋር ያቋቋሙት የሽርክና ውል ፈርሶ የተገዛው ንብረት ተሸጦ እንዱከፊፈለ እንዱወሰን የሚል ነበር። አንደኛ ተጠሪ የሽርክና ውል የለንም በማለት ክድ ተከራክሯል። የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትን ኤክስካቫተር ማሽን ባለቤት መሆኑን በመጥቀስ በክርክሩ ገብቶ ለመከላከል ጣልቃገብ ሆኖ አቤቱታ አቅርቧል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል የተፈረመው ውል የሽርክና ውል እንጂ የአሽሙር ማህበር አይደለም በማለት የሽርክና ውለ ደግሞ በንግድ ሕግ አንቀጽ 219 /ሐ/ መሰረት አልተመዘገበም በሚል ምክንያት ክሱን ውድቅ አድርጓል።
ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛው ፍ/ቤትም ይህንኑ አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ በአመልካች እና በአንደኛ ተጠሪ መካከል መጋቢት 4/1994 ዓ.ም የተፈረመው ውል “የአሽሙር ሽርክና ማህበር” መሆኑን አጥብቀው በመከራከር የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ተሽሮ እንደክሱ የዲኝነት ጥያቄ እንዱወሰን አመልክቷል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ውል በሕግ ረገድ የሚኖረው ውጤት ምንድነው? የሚለውን ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል። የአንደኛ ተጠሪ ወኪል ታህሣሥ 30/2002 ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት መልስ የሥር ፍ/ቤት ክርክርን አጠናክረው አቅርበዋል።
እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል። አመልካች ከአንደኛ ተጠሪ ጋር የሽርክና ማህበር ያቋቋሙ ስለመሆኑ ለማስረዲት መጋቢት 3 ቀን 1994 ዓ.ም የተፃፈ ውል አቅርበዋል። አንደኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር የሽርክና ውል የለኝም ይበል እንጂ የቀረበውን ሰነድ ለማስተባበል በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ ስለመኖር የሥር መዝገብ አያስረዲም። የሥር ፍ/ቤት የቀረበውን ሰነድ ውድቅ ያደረገው ሰነደ የእሽሙር ማህበር ስለመኖሩ አያስረዲም በሚል ነው።
ከቀረበው ሰነድ መረዲት የተቻለው አመልካችና አንደኛ ተጠሪ የሽርክና ማህበር ለማቋቋም ውል ማድረጋቸውን ነው የውል ሰነድ “የሽርክና ውል ስምምነት” ከሚል በስተቀር ምን ዓይነት የሽርክና ማህበር እንደሆነ አያመለክትም። ከንግድ ሕግ አንቀጽ 211 መረዲት የሚቻለው የሽርክና ማህበር ጠቅላላ ስያሜ እንጂ የማህበሩን ዓይነት ለይቶ የሚያመለክት አለመሆኑን ነው። የማህበሮቹ ስያሜ እና ዓይነታቸውን በተመለከተ የንግድ ሕጉ ድንጋጌ ቁጥር 212 በዝርዝር አመልክቷል።
በግራ ቀኙ መካከል አለ የተባለው የሽርክና ማህበር ስያሜው ተለይቶ አልተመለከተም። ከዚህ መነሻ ሲታይ የሽርክና ውለ አልተመዘገበም የሚለው የሥር ፍ/ቤት አቋም ምን ዓይነት የሽርክና ውል የሚለውን አልለየም። ምክንያቱም ምዝገባ የሚያስፈልገው እና ምዝገባ የማያስፈልገው የሽርክና ማህበር በንግድ ሕጉ ተለይቷል።
በግራ ቀኙ ክርክር ይዘት ከመዝገቡም መረዲት እንደተቻለው የአመልካች ክርክር የሽርክና ማህበሩ የእሽሙር የሽርክና ማህበር ስለሆነ ምዝገባ አያስፈልገውም ሕጉ አያስገድድም የሚል ነው። በአንደኛ ተጠሪ በኩል ያቀረበው ዋነኛ ክርክር እስከነጭራሹም የሽርክና ውል የለም የሚል ነው። በዚህ ረገድ በአመልካች በኩል የቀረበው ሰነድ የሽርክና ውል ስለመኖሩ የሚያስረዲ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤትም ተቀባይነት ያገኘ ፍሬ ነገር ነው። የሽርክና ውለ የእሽሙር ሽርክና ማህበር ወይንስ ላላ አይነት ማህበር አቋቁሟል? የሚለውን ለመለየት የሥር ፍ/ቤት በውሳኔው በዝርዝር አላመላከተም።
በሕጉ አገላለጽ ላልች የሽርክና ማህበራት ምዝገባ የሚያስፈልግ ሲሆን የእሽሙር ሽርክና ማህበር ግን ምዝገባ አያስፈልገውም። የንግድ ሕጉ አንቀጽ 219 ይመለከቷል።
አመልካች ያቀረቡት ሰነድ የሽርክና ማህበር መመሥረቱን የሚያመላክት ሲሆን ባለመመዝገቡ የእሽሙር ሽርክና ማህበር ነው ተብል በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር አንደኛ ተጠሪ በማስተባበል ያቀረበው ክርክር የለም።
ስለሆነም በስምምነት የተቋቋመው ማህበር የእሽሙር ሽርክና ማህበር ስለመሆኑ ከቀረበው ሰነድ ለመረዲት ችለናል። ስለሆነም የሽርክና ውለ አልተመዘገበም በሚል ምክንያት የሥር ፍ/ቤት የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሳኔ ሆኖ አግኝተናል።
No topics extracted.
ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
61426 የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።