No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሃብቱ ወልደ - ጠ/አማረ ተሻለ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በመቐለ መካከለኛ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በስር ፍ/ቤት ከሳሽ የነበሩት አመልካች ሲሆኑ በክሳቸው በመቀላ ከተማ ቀበላ 1ይ ወያን የሚገኝ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ የሚገኘውን በቁጥር ሐ/116 በስማቸው የተመዘገበውን ቤት አንደኛ ተጠሪ እንዱያስተዲድሩ፣ እንዱቆጣጠሩ፣ እንዱሸጡና እንዱለውጡ ውክልና ሰጥተዋቸው የነበረ ቢሆንም ከውክልናቸው ውጪ እናታቸው ለሆኑት ለሁለተኛ ተጠሪ በስጦታ በመስጠት ስሙን ያዛወሩ በመሆኑ የስጦታው ውለ ፈርሶ የማህበሩ ቤት ከሁለተኛ ተጠሪ ወደ ስማቸው እንዱዞርላቸው ጠይቀዋል። አንደኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ በተሰጣቸው ውክልና መሰረት ቤቱን ለሁለተኛ ተጠሪ ከመሸጥ በቀር በስጦታ እንዲልሰጡ፣ ሽያጩ ሉከናወን የሚገባውም በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ እና በንግድ ህጉ እንጂ በፍ/ህጉ አለመሆኑንና በተሰጣቸው ውክልና መሰረት በህጉ አግባብ ያደረጉ ሽያጭ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቀዋል። ሁለተኛ ተጠሪም አመልካች በቤቱ ላይ የባለቤትነት ማረጋገጫ ስለላላቸው የመክሰስ መብት የላቸውም፣ አንደኛ ተጠሪ በተሰጣቸው ውክልና መሰረት በሽያጭ እንጂ በስጦታ አልተላለፈም፣ ቤቱም ሉሸጥ የሚችለው በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብና በንግድ ህግ እንጂ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 መሰረት አይደለም፣ ቤቱ በስማቸው ስለተመዘገበ ሽያጩ ሉፈርስ አይገባም፣ ይፈርሳል የሚባል ከሆነ መቀጫ ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ሉከፍለ ይገባል በማለት ተከራክረዋል። በስር ሦስተኛ ተከሳሽ የነበረው 1ይ ወያነ ቤት ስራ ህብረት ስራ ማህበር የተደረገ የስጦታም ሆነ የሽያጭ ውል የለም፣ አንደኛ ተጠሪ በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የተቀመጠ ውሳኔና በመሸጫ አሰራር ከትዲር ነፃ መሆናቸውን በማምጣት ስም ማዛወሪያ ሞልተው ወደ ሁለተኛ ተጠሪ አዘዋውረዋል በማለት መልስ ሰጥተዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ አንደኛ ተጠሪ ለእናታቸው ለሁለተኛ ተጠሪ ሸጫለሁ ያለት በተዘዋዋሪ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ስለሆነ የጥቅም ግጭት አለ፣ የተሸጠውም ቤትና ቦታ በመሆኑ ሽያጩ ለማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጫ የሚመለከተውን የህጉን ድንጋጌ አያሟላም፣ በመሆኑም ውለ ሉፈርስ ይገባል በማለት ቤቱ ከሁለተኛ ተጠሪ ወደ አመልካች ስም እንዱዛወር ወስኗል። ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ላይ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞታል። ተጠሪዎች በመቀጠል ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች ክስ የመሰረቱት አንደኛ ተጠሪ ከተሰጣቸው ውክልና ውጪ ቤታቸውን በስጦታ ለሁለተኛ ተጠሪ ስለሰጡ የስጦታ ውለ እንዱፈርስ ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቶቹ ከክሱ ውጪ በመውጣት የሽያጭ ውለ ይፍረስ ብል መወሰኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 182(2) ውጪ ነው በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመሻር የሽያጩ ውል የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው አንደኛ ተጠሪ ከአመልካች በተሰጣቸው ውክልና ስልጣን ለወላጅ እናታቸው ያደረጉት የሽያጭ ውል የጥቅም ግጭት ያለበት ነው፣ በምንም አይነት ውል የጥቅም ግጭት ካለ ለውጥ ስለማያመጣ የሰበር ችልቱ የጥቅም ግጭት መኖር አለመኖሩን መመርመር ሲገባው ወደ ውለ አይነት ገብቶ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉሻር ይገባዋል ብለዋል። ይህ ችልትም የጥቅም ግጭት መኖር አለመኖሩን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ላቀርብ ይገባል በማለቱ ተጠሪዎች መልሳቸውን በፅሁፍ አቅርበዋል። በመልሳቸውም ቤቱን አንደኛ ተጠሪ በተሰጣቸው ውክልና መሰረት አትርፈው የሸጡት እንጂ በስጦታ ያስተላለፈ ባለመሆኑ የጥቅም ግጭት አለ ልባል አይችልም፣ አመልካች በተደረገው ሽያጭ ውል መሰረት የደረሰባቸው ጉዲት ስለመኖሩ በማስረጃ አስደግፈው አላረጋገጡም በማለት ተከራክረዋል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተመለከትነው አመልካች ክስ የመሰረቱት አንደኛ ተጠሪ እንዱያስተዲድሩላቸው፣ እንዱቆጣጠሩላቸው፣ እንዱሸጡላቸውና እንዱለውጡላቸው ውክልና የሰጧቸውን ቤት ከውክልናቸው ውጪ በስጦታ ለሁለተኛ ተጠሪ ስላስተላለፈ ውለ እንዱፈርስላቸው ነው። ተጠሪዎቹ በሰጡት መልስ ቤቱን ለሁለተኛ ተጠሪ የተላለፈው በሽያጭ እንጂ በስጦታ አለመሆኑ ተከራክረዋል። አመልካችም በስር ፍ/ቤት በተደረገው የቃል ክርክር የሽያጭ ውልም ቢሆን አንደኛ ተጠሪ ውለን ያደረጉት ከእናታቸው ጋር በመሆኑ የጥቅም ግጭት አለ በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤት ቤቱ የተላለፈው በሽያጭ መሆኑን ተቀብል ነገር ግን አንደኛ ተጠሪ ከእናታቸው ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል የጥቅም ግጭት ያለበት በመሆኑ ውለ ሉፈርስ ይገባል የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል። የሰበር ችልቱ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ የሻረው ክሱ የስጦታ ውል ይፍረስልኝ ሆኖ ሳለ የሽያጭ ውል እንዱፈርስ መደረጉ በክሱ ከተጠየቀው ዲኝነት ውጪ ነው በማለት ነው። በእርግጥ አመልካች ቤታቸው ለሁለተኛ ተጠሪ የተላለፈው በስጦታ ነው በሚል ክስ ቢመሰርቱም ዋናው ጥያቄአቸው ቤቱ ወደ ሁለተኛ ተጠሪ የተላለፈበት ውል እንዱፈርስ ነው። በቃል ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜም አመልካች ቤቱ በሽያጭ መተላለፈን ሲረደ የሽያጩም ውል ቢሆን የጥቅም ግጭት ያለበት ነው በማለት ይኸው ነጥብ ክርክር ተደርጎበታል።
በመሆኑም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ባልተነሳ ጉዲይ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል በማለት የደረሰበት መደምደሚያ የተሳሳተ ነው።
በልላ በኩል ይህ ችልት አንደኛ ተጠሪ ለሁለተኛ ተጠሪ ያደረጉት የሽያጭ ውል የጥቅም ግጭት አለበት ወይ? የሚለውን ነጥብ ተመልክቷል። ተወካዩ በፈፀመው ውል ምክንያት የወካዩና የወኪለ ጥቅሞች የሚቃወሙ የሆኑ እንደሆነ ይህን ውል የፈረመው 3ኛ ወገን ሁኔታውን ያወቀና ሉያውቀው የሚገባ የሆነ እንደሆነ ወካዩ በሚያቀርበው ጥያቄ መሰረት ውለ ሉፈርስ እንደሚችል የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2187(1) ያስረዲል። በተያዘው ጉዲይ አንደኛ ተጠሪ የአመልካች ወኪል ሲሆኑ በተሰጣቸው ውክልና መሰረት የአመልካችን ቤት ለእናታቸው ሸጠዋል። ውክልና ተወካዩ ለወካዩ እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በወካዩ ስም ለማከናወን የሚደረግ ስምምነት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2198 ያመለክታል። ይህም ስምምነት ወካዩ የውክልናው ስራ በሚፈፅምበት ጊዜ የወካዩን ህጋዊ ሁኔታዎች የመለወጥ ስልጣን የሚሰጠው በመሆኑ ተወካዩ የውክልናውን ስልጣን ተጠቅሞ ሲሰራ ለወካዩ ፍፁም ታማኝ እና በስራው ሁለ የወካዩን ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ግዳታ አለበት። ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ይህንን ለወካዩ ፍፁም የሆነ ታማኝነቱንና ሙለ ለሙለ የወካዩን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚከለክለው ፍላጎት ወይም ታማኝነቱን የሚከፊፍል ሁኔታ የሚያስከትል የጥቅም ግጭት ሲፈጠር ተወካዩ በስራው አፈፃፀም ጥንቃቄ ሉያደርግ ይገባል። እነዚህም ግዳታዎች በፍ/ብ//ህ/ቁ. 2208 እና 2209 ስር ተመልክተው የምናገኛቸው ናቸው።
በመሆኑም ተወካዩ የራሱን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የቤተሰቡ፣ የጓደኛው ወይም ቅርብ ግንኙነት ያለው ሰው ጥቅምን በሚመለከት ጉዲይ ሲያጋጥመው ሁኔታውን ለወካዩ ሳያሳውቅና ሳይስማማ ስራውን እንዲይሰራ ይከለከላል። ይህም የሚሆነው የውክልና ስራውን በሚሰራበት ጊዜ የራሱን ወይም ከራሱ ጋር ቤተሰባዊ ወይም ላላ ጥብቅ ግንኙነትና ትስስር ያለው ሰውና የወካዩ ጥቅም በሚጋጭበት ጊዜ ከራሱ ወይም ከቤተሰቡ ጥቅም ይልቅ የወካዩን ጥቅም በማስቀደም ለወካዩ ጥቅም ብቻ ይሰራል ተብል ስለማይገመት ነው። በመሆኑም ወኪለ በፈፀመው ውል ምክንያት የወካዩ እና የተወካዩ ጥቅሞች የሚጋጩ ከሆነ ውለን የፈረመው 3ኛ ወገን ይህን ሁኔታ ያወቀውና ሉያውቀው የሚገባ የሆነ እንደሆነ በወካዩ ጥያቄ መሰረት ውለ ሉፈርስ እንደሚችል በህጉ ተካቷል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች አንደኛ ተጠሪን ክርክር ያስነሳውን ቤት እንዱያስተዲድሩ እንዱሸጡና እንዱለውጡ የውክልና ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። በመሆኑም አንደኛ ተጠሪ በወካያቸው ስም ሲዋዋለ ፍፁም ታማኝና ሙለ ለሙለ የወካያቸውን የአመልካችን ጥቅም በሚያስጠብቅ ሁኔታ ውለን የመፈፀም ግዳታ አለባቸው። አንደኛ ተጠሪ ከአመልካች በተሰጣቸው ውክልና መሰረት ቤቱን የሸጡ እናታቸው ለሆኑት ለሁለተኛ ተጠሪ ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ደግሞ አንደኛ ተጠሪ በውክልናቸው መሰረት ቤቱን የሸጡት የቤተሰባዊ ጥብቅ ትስስር ላላቸው እናታቸው በመሆኑ በወካያቸው ጥቅምና ውለን ባደረጉት እናታቸው ጥቅም መሃከል ግጭት መኖሩ የሚታመን ነው። ይህ በሆነ ጊዜ አንደኛ ተጠሪ ሁኔታውን ለአመልካች ሉያሳውቁና የአመልካችን ይሁንታ ሉያገኙ ይገባል። አንደኛ ተጠሪ ውለን ከመፈፀማቸው በፉት ለአመልካች ያሳወቁና ስምምነታቸውን ያገኙ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክርክር የለም። ወይም አንደኛ ተጠሪ ቤቱን የአመልካችን ጥቅም ብቻ በሚያስጠብቅ መልኩ ተገቢው ጥንቃቄ በማድረግ ቤቱ በተሸጠበት ጊዜ ሉያወጣ በሚችለው የገበያ ዋጋ ሽያጩን ያከናወኑ መሆኑና የአመልካች ጥቅም በምንም መልኩ ያልተጎዲ መሆኑን በስር ፍ/ቤት ሉያስረደ ይገባል። ይህ ለመሆኑ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ አቅርበው ያስረደት ነገር ስለመኖሩ መዝገቡ አያሳይም። በልላ በኩል አንደኛ ተጠሪ ቤቱን በውክልና ስልጣናቸው የሸጡላቸው በመሆኑ የጥቅም ግጭት እንደሚኖር ሁለተኛ ተጠሪ ያውቃለ ወይም ሉያውቁ ይገባል። አንደኛ ተጠሪ ከአመልካች በተሰጣቸው የውክልና ስልጣን መሰረት የአመልካችን ቤት ለእናታቸው ለሁለተኛ ተጠሪ መሸጣቸው የጥቅም ግጭት መኖሩን የሚያሳይ በመሆኑም አመልካች ውለ እንዱፈርስላቸው ሉጠይቁ ይችላለ።
በልላ በኩል አንደኛ ተጠሪ ከቤቱ ሽያጭ ያገኙትን ገንዘብ ለአመልካች የከፈለ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ባለመረጋገጡ የተከፈለ ገንዘብ ካለ አንደኛ ተጠሪ አመልካችን ከሰው የመጠየቅ መብታቸውን ፍ/ቤቱ ጠብቆላቸዋል። ሁለተኛ ተጠሪም ቤቱ ለመግዛት የከፈለትንና በቤቱ ላይ ተጨማሪ ወጪ አውጥቻለሁ የሚለ ከሆነ ያወጡትን ወጪ አንደኛ ተጠሪን ከሰው የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ ነው።
በአጠቃላይ የስር ፍ/ቤት የሽያጩ ውል ሉፈርስና በሁለተኛ ተጠሪ ስም የተመዘገበው የቤትና የቦታ እጣ በአመልካች ስም እንዱመዘገብ የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት የህግ መሰረት የለም።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት 17 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የመቐላ መሃከለኛ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 5 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 8 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.