No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሸረፈዱን አብደላ - ጠበቃ አብድ መሐመድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ማርታ አሰፊ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በሐዋላ የተላከውን ገንዘብ መሰረት ያደረገ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ሲሆን ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች ናቸው። ተከሳሽ ደግሞ የአሁኑ ተጠሪ ነው። የአመልካች የስር ክስ ይዘት ባጭሩ፡- አቶ አህመድ ኢሳ ኪይሮ የተባለ ግለሰብ በተጠሪ ባንክ ሚዛን ተፈሪ ቅርንጫፍ ታህሣሥ 16 ቀን 1999 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. በ25/12/2006) በመቅረብ ብር 145,860.00(አንድ መቶ አርባ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ብር) ለአመልካች ገቢ በማድረግ ማስተላለፊቸውን፣አመልካች ይሕንን ገንዘብ ለማውጣት ገንዘቡን እንዱከፍል ለታዘዘው አየር ጤና ቅርንጫፍ ቢሄደ ገንዘቡን ለላላ ግለሰብ እንደከፈለ በመግለጽ ክፍያው ለአመልካች ሉፈፀምላቸው የማይችል መሆኑን የገለፀ መሆኑን በመግለጽ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ክፍያው ይፈፀም ይችል ከነበረበት ከጥር 01 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድና ከተለያዩ ወጪዎች እና ኪሳራዎች ጋር ተጠሪ እንዱከፍል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም አመልካች በገንዘቡ ላይ መብት ወይም ጥቅም ስለላላቸው ክስ ለመመስረት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት አለመኖሩን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስቶ የተከራከረ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ክፍያው ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና የተለመደውን አሰራር በመከተል የፈፀሙ መሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ክፍያውን የፈፀመው ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና የተለመደውን አሰራር በመከተል በመሆኑ ለክሱ ኃላፉነት የለበትም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ነሐሴ 12 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡ተጠሪ ክፍያውን የፈፀመው ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና የተለመደውን አሰራር በመከተል ነው ተብል ገንዘብ ላኪው ግለሰብ እንኳ ቀርቦ እንዱመሰክር ሳይደረግ ውሳኔ መሰጠቱ ያላግባብ ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ ተጠሪ ገንዘቡን እንዱከፍላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ተገቢውን ጥንቃቄ ወስድ በሐዋላ የተላከውን ገንዘብ በመክፈለ ኃላፉነት የለበትም ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች መወሰኑ ባግባቡ መሆኑ ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏ የተጠሪ ነገረ ፈጅ ጥር 07 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ ማመልከቻ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አመልካችም በ11/06/2002 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ ማመልከቻ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀ ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ለክሱ መሰረት ያደረጉት ምክንያት ገንዘቡ በስህተትና በሐሰት ለላላ ሰው ተከፍልብኛል የሚለውን መሆኑን፣ተጠሪም ገንዘቡ በላኪው ግለሰብ በተላለፈው መሰረት ገንዘቡ ለተላከለት ሰው ከፍያለሁ ብል የሚከራከር መሆኑን፣የስር ፍርድ ቤትም በተጠሪ በኩል የቀረቡትን ማስረጃዎችን በመመርመር ተጠሪ ገንዘቡን ለተላከለት ሰው ከፍያለሁ የሚለው ከአመልካች ጋር ተመሳሳይ ስም ላለው ሰው ተገቢውን ጥንቃቄ እና የተለመደውን አሰራር በመከተል ስለመሆኑ መረጋገጡን በምክንያትነት በመያዝ ተጠሪን ከክሱ ኃላፉነት ነፃ ማድረጉን ነው።
በመሰረቱ ባንክ በሐዋላ የተላከውን ገንዘብ ለተላከለት ሰው በትክክል የማድረስ ኃላፉነት ያለበት መሆኑ ይታመናል። ባንኩ በሐዋላ ለማድረስ የተቀበለውን ገንዘብ ለተገቢው ሰው ካላደረሰ ኃላፉነት የሚኖርበት ሲሆን ኃላፉነቱ የሚከተለው ግን ተገቢውን ጥንቃቄ እና የተለመደውን አሰራር ሳይከተል መቅረቱ ወይም ራሱ ባንኩ መጭበርበሩ ሲረጋገጥ ነው። በተያዘው ጉዲይ ግን ባንክ ተገቢውን ጥንቃቄ እና የተለመደውን አሰራር መከተለን የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው ጉዲይ ሲሆን አመልካች ገንዘቡን ከባንኩ የወሰደት ግለሰብ ባንኩን ያጭበረበሩት ስለመሆናቸውን በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ማስረጃ የለም። ገንዘቡን ለአመልካች ላኩ የተባለት ሰው ለማስረጃነት አመልካች የቆጠሯቸው ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የማያሳይ በመሆኑ አመልካች የስር ፍርድ ቤት እኚህን ግለሰብ ሳይሰማ ማለፈ ያላግባብ ነው በማለት ያቀረቡት ቅሬታ ስለማስረጃ አቀራረብና አቀባበል የተደነገጉትን የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ በመሆኑ ይህ ችልት የሚቀበለው ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የማስረጃው አቀባበልና አመዛዘኑ ባግባቡ ሆኖ አግኝተናል። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕግ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 እና 22 ድንጋጌዎች ስር የተመለከተው ይዘትና መንፈስ እንደሚያስገነዝበው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ጉዲይ ሳይሆን የማስረጃ ምዘና ጉዲይ ሆኖ ስለአገኘን የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉፀና የሚገባው ነው። በዚህ መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 100405 ግንቦት 04 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 69684 ግንቦት 14 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.