No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አብደላ ሁሴን ከለር ላብራቶሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ አቶ ሣሙኤል ኤፍሬም - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን - ዓቃቤ ሕግ ግርማ ወልደማሪያም -ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ፣የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ አመልካች የፋዳራል አገር ውስጥ ገቢና ጉምሩክ ባለሥልጣን በሰጠው የገቢ ግብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ማስታወቂያ ባለመስማማት ይግባኝ ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ለማቅረብ በሕጉ መሰረት ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ በወቅቱ አስይዘዋል ወይስ አላስያዙም የሚለው ነጥብ ነው።
አመልካች የገቢ ግብር ማስታወቂያና የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ማስታወቂያ ከደረሳቸው በኋላ በሰላሣኛው ቀን ማለትም ሰኔ 8 ቀን 1999 ዓ.ም ለሁለቱም ግብሮች CPO በማሰራት ከተጠሪ ቢሮ ድረስ መሄዲቸው ለገቢ ግብር ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ 8/10/99 አስይዘው የጨረሱ መሆኑንና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ ሰኔ 8 ቀን 1999 ዓ.ም ለማስያዝ ከተጠሪ ቢሮ አስራ አንድ ሰዓት በኋላ ያቀረቡ ቢሆንም ሰራተኞችና የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፉዎች ወጥተው ስለነበር ሣያስይዙ ተመልሰው ተከታዮቹ ቀናት የቅዲሜና እሁድ ስለነበሩ 11/10/99 ገንዘቡን የማስያዝ ሂደቱን አጠናቅቀው ይግባኙ እንዱታይላቸው ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አቅርበዋል። የግብር ይግባኝ ሰሚ ይግባኙ የቀረበው በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 43 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት በሰላሣ ቀን ውስጥ መያዝ ያለበት ገንዘብ ተይዞ ባለመሆኑና ጊዜው ካለፈ በኋላ ያቀረበ በመሆኑ ይግባኙ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው አልፎል ወይስ አላለፈም የሚለው ክርክር የፍሬ ጉዲይ ክርክር እንጅ የሕግ ነጥብ ባመለሆኑ ይግባኙን አልተቀበልኩትም በማለት ይግባኙን ውድቅ አድርጏታል። አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልት ይግባኝ አቅርበው ይግባኝ ሰሚ ችልቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች የገቢ ግብር ማስታወቂያ ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ ያለብንን CPO እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ ያለብንን ገንዘብ በCPO አሰርተን ተጠሪ መሥሪያ ቤት የቀረብነው 8/10/99 ነው። የገቢ ግብሩን ተቀብል ደረሰኝ ሲሰጠን የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመክፈል ያቀረብነውን CPO በተመለከተ ኮንፒውተር ብለሽት አጋጥሞታል በሚልና በላልች ምክንያቶች ደረሰኝ ሣይሰጠን ተመልሰናል፣እለቱ አርብ ስለነበር ቅዲሜና እሁድ ቆይተን ሰኞ 11/10/99 ደረሰኝ ተቆርጦ የተሰጠን ሲሆን ለክፍያ ያቀረብነው 8/10/99 መሆኑን በደብዲቤ ገልፆ ጽፍልናል። የተጠሪ ምስክሮችም ይህንን አስረድተዋል። በግብር ተቀባዩ መሥሪያ ቤት (ተጠሪ)ለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ደረሰኝ ሣናገኝ 8/10/99 መመለሳችንና ደረሰኙ 11/10/99 ተቆርጦ የተሰጠን መሆኑ በእኛ ቸልተኝነት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው እንዲለፈ የሚያስቆጥር አይደለም።
ይህ የሕግ ትርጉም የሚጠይቅ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ እያለ የፍሬ ጉዲይ ክርክር ነው ተብል መታለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ ለተጨማሪ እሴት ታክሱ ደረሰኝ የተሰራላቸው 11/10/99 መሆኑን አመልካች አምነዋል። የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ጊዜው አልፎል ወይስ አላለፈም የሚለውን አጣርቶ መያዣው በወቅቱ ያልተከፈለ መሆኑን በማረጋገጥ መያዣቸው ጊዜው ካለፈ በኋላ የተከፈለ መሆኑን አረጋግጦ የሰጠው ውሣኔ የፍሬ ጉዲይ ክርክር እንጅ የሕግ ክርክር ባለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የፈጸሙት የሕግ ስህተት የለም በማለት መልስ ሰጥቷል አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ ያለባቸውን ገንዘብ ያስያዙት መቼ ነው? ይግባኝ ለማቅረብ መያዝ የሚገባው ገንዘብ ጊዜው ከማለፈ በፉት በማስያዝ አመልካች ይግባኝ አቅርቧል ወይስ አላቀረበም የሚለው ነጥብ የሕግ ትርጉም የሚያስፈልገው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። አመልካች ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ በCPO ለማሰራት ከተጠሪ ቢሮ ሰላሣ ቀን ከማለፈ በፉት ቀርበው የገበሩ መሆኑና ተጠሪ የገቢ ግብር ይግባኝ ለማቅረብ በCPO ያቀረቡትን መያዣ ደረሰኝ ቆርጦ 8/10/99 ዓ.ም የሰጠ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ በመያዣነት ያቀረቡትን CPO 8/10/99 ከተቀበለ በኋላ በተለያየ ምክንያት ደረሰኝ ቀርቦ መስጠት እንዲልቻለና ደረሰኙን 11/10/99 ዓ.ም ቆርጦ የሰጠ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው።
እዚህ ላይ የሚነሣው ጥያቄ አመልካች ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ መያዣው በሚፈፀምበት ሥርአት በCPO አሰርተው ለተጠሪ ጊዜው ከማለፈ በፉት ማቅረባቸው ከተረጋገጠ CPO ለክፍያ ያቀረበውን ገንዘብ አወራርድ ደረሰኝ ለመስጠት ተጠሪ በአጋጠመው የአሰራር ወይም ላላ ችግር ምክንያት ቀናት ወይም ወራት ቢወሰድበት ይግባኝ ባዩ ይግባኝ ለማለት መክፈል ያለበትን ገንዘብ በጊዜው አልከፈለም ልባል ይገባዋል ወይ? የሚለው ነው። ይህ ጥያቄ ከሕጉ አጠቃላይ መንፈስና ዓላማና ሕግ አውጭ ሉያሣካው ከሚፈልገው ግብ አንፃር መመርመርና ውሣኔ ማግኘት አለበት። ሕግ አውጭው የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ የደረሳቸው ሰዎች የውሣኔ ማስታወቂያ በደረሳቸው በሰላሣ ቀን ውስጥ ማስያዝ የሚገባቸውን ገንዘብ 50% ለግብር ሰብባቢው መሥሪያ ቤት በማስያዝ ይግባኝ ማቅረብ እንዲለባቸው በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 43/1/ ሲደነግግ ግብር ከፊዩ ለግብር አስገቢው መሥሪያ ቤት ገንዘቡን ገቢ እንዱያደርግ ለማስገደድ እንጅ ገንዘቡ ገቢ ሆኖ ግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ደረሰኝ ሣይሰጥ ቢቆይ ለመሥሪያ ቤቱ የአሰራር ድክመትና ችግር ምክንያት ግብር ከፊይ ይግባኝ የማቅረብ መብቱ እንዱጣበብ በማሰብ አይደለም። ስለዚህ አመልካች ተጠሪ ክፍያ በሚቀበልበት ሥርአት በማሟላት ማለትም በCPO መክፈል አለብህ ተብል የተወሰነበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ 50% የግብር ውሣኔ ማስታወቂያ በደረሰው በሰላሣኛው ቀን ማለትም 8/10/99 ለተጠሪ ገቢ አድርጓል። የህም አመልካች ከላይ ከተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ የተወሰነው ጊዜ ከማለፈ በፉት ለተጠሪ ገቢ አድርገዋል። ተጠሪ ሰላሣ ቀኑ ከማለፈ በፉት በCPO ገቢ ለሆነለት ገንዘብ ደረሰኝ ቆርጦ ያሰጠው ከሶስት ቀን በኋላ ማለትም 11/10/99 መሆኑ ይግባኝ ለማቅረብ ማስያዝ ያለበትን ገንዘብ አመልካች ከሰላሣ ቀን በኋላ ነው ገቢ ያደረገው ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። በግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት በኩል ያለ የአሰራር ችግሮችና ጉድለቶች መሰረታዊ የሆነውን የአመልካችን ይግባኝ የማቅረብ መብት በማያጣብብ ሁኔታ በመተርጏም የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጠው ውሣኔ የሕጉን ድንጋጌ አተረጋጏምና ተፈፃሚነት የሚመለከት እንጅ የፍሬ ጉዲይ ክርክር አይደለም።
በመሆኑም የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት ጉዲዩ የፍሬ ጉዲይ ክርክር ነው በማለት ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ለአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 43 ንኡስ አንቀጽ 1 የሰጠውን የተዛባ ውሣኔ ሣያርሙ ማለፊቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ከማለፈ በፉት የመያዣነት መከፈል የሚገባውን ገንዘብ ለተጠሪ ያስያዙ በመሆኑ የቀረበለትን ይግባኝ በመመርመርና የግራ ቀኙን ክርክር በማስማት ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን ለግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 341 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት መልስን ልከንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.