No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሞያላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- አቶ ዛኪ ሰይድ - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በሕጉ በተሰጠው ስልጣን ተግባሩን በሚፈጽምበት ጊዜ ለሚደርሰው የገቢ መቋረጥና የንብረት ጉዲት ያለውን ኃላፉነት ስለሚገዛ የሕግ አግባብ የሚመለከት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበሩት ያሁኑ ተጠሪ ሲሆን ተከሣሽ የአሁኑ አመልካች ነበር። የተጠሪ ክስ ይዘት ባጭሩ፡ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነ ቁጥሩ 3-24ዐ62 ኢት መኪና አመልካች ከሕግ ውጪ በማቆሙ በፍርድ ቤት ውሣኔ የተሰጠ ቢሆንም መኪናው በቆመበት ጊዜ ተጠሪ በአጠቃላይ ብር 216,25ዐ.00 /ሁለት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ ብር/ ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑን ገልጸው ይህንኑ ገንዘብና መኪናውን እስኪረከቡ ድረስ ያለውን ገቢ ከመጠየቅ መብታቸው ጋር አመልካች እንዱከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል።
በመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያነት የቀረበው ክርክር ቀድሞ ተጠሪ ክስ አቅርበው ባለቀ ጉዲይ ላይ ድጋሚ ክስ ማቅረብ የማይችለ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ አመልካች መኪናውን ይዞ ሉያቆም የቻለው መኪናው ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ እቃ ጭኖ ወደ ውጪ ሉወጣ ሲል በመሆኑና ይህን ዓይነት ተግባር ደግሞ አመልካች ለመቆጣጠር ተገቢ ነው ያለውን እርምጃ ለመውሰድ በሕጉ ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ ኃላፉነት የለብኝም፣ መኪናው መጋቢት 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላም በዚሁ ጊዜ ለፍርድ ቤት ያሳወቀ በመሆኑ ጥፊት የለብኝም ብል መከራከሩን የሚገልጽ ነው። የሥር ፍርድ ቤትም አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበውን ክርክር የተጠሪ የቀድሞ ክስና የበኋለኛው ክስ ፍሬ ነገር ተመሣሣይ ባለመሆኑ ጉዲዩ በፍርድ ያለቀ ነው ለማለት አይቻልም በሚል ምክንያት ውድቅ አድርጎ የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር አመልካች የተጠሪ መኪናውን ያላግባብ በማቆም ገቢ እንዱያጡ አድርጓል፤ በመኪናው ሸራ እና ባትሪ ላይም ጉዲት ማድረሱን አላስተባበለም በማለት ብር 52,ዐ19.40 /ሃምሳ ሁለት ሺህ አስራ ዘጠኝ ብር ከአርባ ሳንቲም/ አመልካች ለተጠሪ ይክፈለው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ጥቅምት 18 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ከአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 አንቀጽ 58/ለ/ አንፃር /በሰ/መ/ ከተሰጠው ትርጉም/ ሲታይ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ የካቲት ዐ4 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በተፃፈ ሦስት ገጽ ማመልከቻ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሣኔ ተገቢ ነው የሚለበትን ምክንያት ገልጸው ውሣኔው ሉጸና ይገባል ሲለ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባባነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ ማንም ሰው በራሱ ጥፊት ወይም በላልት ሰዎች ጥፊት የተነሳ በልላ ሰው ንብረት ላይ ጉዲት ካደረሰ ከውል ውጪ ኃላፉነት የሚከተልበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ27/1/ እና /3/ ድንጋጌዎች ያሳያለ።
ጥፊት ደግሞ ታስቦ ወይም በቸልተኝነት ሉፈፀም እንደሚችል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ28/1/ ድንጋጌ በግልጽ አስቀምጧል። የጥፊት ትርጉም ደግሞ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ28 እስከ 2ዐ37 ሥር የተመለከተ ሲሆን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ38 እስከ 2ዐ65 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች የተፈፀመው ተግባር ጥፊት መሆን አለመሆኑን የሚገዙ ናቸው። አመልካች ለተጠሪ ክስ ኃላፉነት አለበት የተባለው ከውል ውጪ ኃላፉነትን የሚገዙት የሕግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ያሳያል። አመልካች ይህንኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ተገቢነት የለውም በማለት የሚከራከረው በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 ከተሰጠው ኃላፉነት እና ተግባር አንፃር ነው። በዚህ አዋጅ አመልካች በጉምሩክ ወደቦች በወሰን አከባቢዎች እንዱሁም በላልች የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ማቋረጫ መስመሮች በኩል የሚገቡና የሚወጡ ዕቃዎችንና ማጓጓዣዎችን የመፈተሽ፣ የጉምሩክ ስነ ሥርዓት ተፈጽሞባቸው መግባታቸውንና መውታቸውን የማረጋገጥ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቷል።
በአዋጁ አንቀጽ 74 በተለይ ሲታይ አመልካች የሕገ ወጥ እቃዎችን ዝውውር የመቆጣጠር ኃላፉነትና ተግባር ተሰጥቶታል። በአዋጁ አንቀጽ 6/5/ እና 58 ስርም ይኸው ተግባር የአመልካች ሕጋዊ ግዳታ ስለመሆኑም የሚያስገነዝብ የሕጉ አቀራረጽ ይታያል። የአዋጁ አንቀጽ 25 ድንጋጌ ያሻሻለው የአዋጅ ቁጥር 368/1995 አንቀጽ 78 ድንጋጌም አመልካች ኮንትሮባንድ ወይንም ሕገ-ወጥ እቃ ጭኗል ብል ያመነበትን ተሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደሚቻል በግልጽ ተመልክቷል። ይሁን እንጂ አመልካች ይህንኑ በሕጉ ተለይቶ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በተገቢው መንገድና በተገቢው ጊዜ ያከናውናል ተብል ይታሰባል። አመልካች ይህንኑ ስልጣንና ተግባሩን በተገቢው ጊዜና ሁኔታ ባለማከናወን በልላ ሰው ንብረት ላይ በሚያደርሰው ጉዲት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ27/1/ እና /3/ ድንጋጌዎችና አግባብነት ባላቸው ድንጋጌዎች የማይጠየቅበት ወይም ኃላፉ የማይሆንበት ምክንያት የለም።
በመሆኑም አመልካች በሕጉ ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፉነትና ተግባር ያላግባብ ባለመወጣቱ በሰው ንብረት ላይ ጉዲት ማድረሱ ከተረጋገጠ ካሳ የማይከፍልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በዚህም መሰረት በአመልካች ተገቢ ያልሆነ ተግባር ጉዲት ደርሶብኛል የሚል ሰው የአመልካች ተግባር በሕጉ ከተሰጠው ኃላፉነትና ተግባር የሚፃረር ወይም በምክንያታዊ መንገድ ተቀባይነት የላለው መሆኑን ማስረዲት ከቻለ በአመልካች ሉካስ የሚገባው መሆኑን ይህ ችልት ያምናል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች የተጠረጠረውን ማንኛውንም ዕቃ ይዞ የመፈተሽና እቃውን የጫነውን ተሽከርካሪም ይዞ የማቆየት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶችም የተቀበለት ጉዲይ ሲሆን ፍርድ ቤቶቹ የአመልካችን ተግባር ኃላፉነትን የሚያስከትል ነው ለማለት የቻለት የተጠረጠረውን መኪና ለአንድ መቶ አስራ ሰባት ቀናት ያሕል መያዙ ተገቢነት የለውም በማለት ነው። ይሁን እንጂ አመልካች ይህን የሚያሕል ጊዜ መኪናው ተይዞ እንዱቆይ ያደረገው የወንጀለ ጉዲይ በፍርድ ቤት ተይዞ እየታየ ባለበት ጊዜ ሲሆን በፍርድ ቤት ውሣኔም መኪናውን እንዱለቅ መወሰኑ የክርክሩ ሂደት ያስገነዝባል። አመልካች ከዚህ ጊዜ ውጪ መኪናው ያላግባብ የተያዘ ስለመሆኑ ለማስረዲት ያቀረቡት ማስረጃ የለም። የወንጀል ጉዲይ ሲታይ በነበረበት ጊዜ ደግሞ ጉዲዩ የኮንትሮባንድ አይደለም ተብል ስለተወሰነ ብቻ በአመልካች ላይ የፍትሐብሕር ተጠያቂነት ሙለ በሙለ ያስከትላል ብል ለመደምደም የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት የለም። አመልካች በሕጉ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ባግባቡ ለመወጣት እንዱቻል መኪናውን ይዞ ማቆሙ ተገቢ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለታጣ ገቢ ደግሞ የሚጠየቅበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ይህ ሰበር ችልት በመ/ በቀረበው ተመሣሣይ ጉዲይ አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1989 ድንጋጌዎችን በመመርመር በአዋጅ ቁጥር 454/1997 መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። አመልካች መኪናውን ይዞ ጉዲዩ በወንጀል ችልት እየታየ መቆየቱን ከክርክሩ መገንዘብ የምንችለውና በዚህ ሂደት የባከነው ጊዜ ከነባራዊው ዓለም አንፃር ሲታይ ምክንያታዊ ነው ከሚባል በስተቀር ያላግባብ የዘገየ ነው ለማለት የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 69/1989 አንቀጽ 6/5/፣ 58፣ 74 ድንጋጌዎች እና ከአዋጅ ቁጥር 368/1995 አንቀጽ 78 ድንጋጌ አንፃር ሲታይ መኪናውን ማቆሙ በሕጉ መሰረት የተሰጠውን ስልጣን በሕጉ አግባብ ለመወጣት እንዱያስችለው የወሰደው እርምጃ ያላግባብ ያልተከናወነ እና በተገቢው ጊዜ ውስጥ የተፈጸመ ነው ከሚባል በስተቀር በውለ ውጪ ኃላፉነትን የሚያስከትል ሆኖ አላገኘነውም። በዚህም ምክንያት በዚህ ረገድ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።
ላላው በታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ አመልካች በተጠሪ መኪና ባትሪና ሸራ ላይ ጉዲት አድርሷል ተብል ግምቱን እንዱከፍል ነው። አመልካች በዚህ ረገድ የተሰጠውን የበታች ፍርድ ቤቶችን ሕጋዊ መሰረት የለም በማለት በዚህ ችልት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በግልጽ ያልተከራከረበት ሲሆን በሥር ፍርድ ቤት በቀረበው ክርክርም ቢሆን በመኪናው ባትሪና ሸራ ላይ መኪናው በአመልካች ቁጥጥር ሥር ውጪ በነበረበት የደረሰ ወይም በራሱ ቁጥጥር ሥር ውስጥ እያለ በልላ ምክንያት የደረሰ ነው የሚል ክርክርም አላቀረበም። በመሆኑም በእነዚህ ንብረቶች ጉዲት የደረሰ ስለመሆኑ ማስረጃን የማጣራትና የመመዘን ስልጣን ያላቸው የሥር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይ ሲሆን አመልካች ጉዲቱ በልላ ምክንያት የደረሰ ስለመሆኑ የሚያሳይ ክርክርና ማስረጃ አላቀረቡም። በመሆኑም አመልካች በኮንትሮባንድ ድርጊት /ሥራ/ ተሰማርቶ የተገኘን ተሽከርካሪ ለጊዜው ማቆም የሚችል መሆኑን ሕጉ ስልጣን ቢሰጠውም ንብረቱን ግን ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ የመያዝ ግዳታ አለበት።
መኪናው በራሱ ቁጥጥር ስር በነበረበት ጊዜ ለሚደርሰው የመኪናው አካል ጉድለት ጉድለቱ በልላ ሕጋዊ ምክንያት የደረሰ ስለመሆኑ እስካላስረዲ ድረስ ኃላፉነቱ የአመልካች የማይሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በአጠቃላይ ከፍ ብለው በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ሉሻሻል የሚገባው በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ዐ4134 ሐምል 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ተሰጥቶ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ነሐሴ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የተጠረጠረውን ዕቃ ይዞ የመቆየት ሥልጣንና ተግባር በአዋጅ ቁጥር 69/1989 አንቀጽ 6/5/፣ 58/1/ለ/ እና 74 እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 368/1995 አንቀጽ 78 መሰረት ያለው በመሆኑና ጊዜውም ምክንያታዊነት የላለው ነው ለማለት የሚቻል ባለመሆኑ መኪናው በቆመበት ጊዜ ለታጣ ገቢ ኃላፉነት የለበትም ብለናል።
አመልካች መኪናውን ይዞ ባለበት ጊዜ ለደረሰው የመኪና ባትሪ እና ሸራ ጉዲት ኃላፉነት ያለበት በመሆኑ የሁለት ባትሪ ዋጋ ብር 4,5ዐዐ.00 /አራት ሺህ አምስት መቶ/ እና የሸራ ዋጋ ብር 7ዐዐዐ.00 /ሰባት ሺህ/ በድምሩ ብር 11,5ዐዐ.00 /አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለተጠሪ እንዱከፍል ብለናል። በዚህ መሰረት ያስፈጽም ዘንድ የዚህ ችልት ውሣኔ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ ብለናል።
ለክርክሩ የወጣን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት ጥቅምት 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል፤ ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.