No summary available.
ሚያዝያ 26 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገብረሥላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ መስፍን ሽፈራው ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎች ባለሥልጣን - ገብረእግዚአብሓር ሙናቸው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት መጋቢት 13 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። ተጠሪ አመልካች የዘሽ ትሬዱንግ ሥራ አስኪያጅ መሆናቸውን ገልፆ ድርጅቱ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም ከቀኑ አራት ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ፈፅሟል። ስለዚህ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) መሰረት የወንጀል ተጠያቂነት አለበት በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክረዋል ድርጅቱ ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱን ዐቃቤ ህግ ገልጿል። አመልካች በበኩላቸው ሥራውን በውክልና ለወ/ሮ ድርሻዬ ከበደ ለተባለች ሰራተኛ በውክልና ሰጥቻለሁ የሚል ክርክር ያቀረቡ ሲሆን የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመዘነ በኋላ አመልካች ለሥራው ሙለ ውክልና አልሰጠም። የቃል ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ውጭ የዘረጋው ሥርዓት የለም በማለት በክሱ በተጠቀሰው የህግ ድንጋጌ ጥፊተኛ ብል በአንድ ዓመት ከስድስት ወር እሥራትና በብር 20,000(ሀያ ሺህ ብር) እንዱቀጣ ወስኗል።
አመልካች በውሣኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ትክክለኛ ፍትህ ይረዲለ የተባለ የማጣሪያ ምስክሮች በመስማት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ አፅንቶታል። አመልካች የሥር ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የድርጅቱ ሰራተኛ ወ/ሮ ድርሻዬ ከበደ ሥራውን ወክያት እየሰራች የነበረ ሲሆን በዚሁ ጉዲይ ጥፊተኛ ተብላ ተቀጥታለች፣ ወንጀለ ሲፈፀም እኔ በቦታው አልነበርኩም፣ ግብይቱ የተፈፀመው ያለ እኔ ፈቃድና ስምምነት ነው፣ ከድርጅቱ ሰራተኞች ያለቫት ደረሰኝ ግብይት እንዲይፈፅሙ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ። የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 34 እና የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) የማይጣጣሙ በመሆኑ ተከሳሹን በሚጠቅም መንገድ መተርጎም አለባቸው። ቅጣቱ ውሣኔም ተገቢ አይደለም መገደብ ነበረበት በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ አመልካች የሚመራው ድርጅት በወንጀል ጥፊተኛ ተብል ተቀጥቷል ስለዚህ አመልካችን ተጠያቂ ለማድረግ ላላ ማስረጃ የማቅረብ ግዳታ የለብንም አመልካች ጥፊተኛ የተባለት ተገቢውን ቁጥጥር ባለማድረግና ሥርዓት ባለመዘርጋታቸው ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች ተገቢውን ማጣራት አድርጎ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) እና በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 34 ንዐስ አንቀፅ 3 መካከል የሀሳብ አለመጣጣም አለ በማለት ያቀረበው ክርክር በወንጀል ህጉ አንቀፅ 3 የተደነገገውን ከግንዛቤ የማያስገባና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም። አመልካች በሥራ አስኪያጅነት የሚመሩት የንግድ ድርጅት የአመልካች ሰራተኛ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት በመፈፀም ወንጀል ጥፊተኛ የተባለ በመሆኑ በመርህ ደረጃ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) ጥፊተኛ የሚባለ መሆኑ በህጉ ተደንግጓል። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56 ንዐስ አንቀፅ 3 የተመለከቱትን ልዩ ሁኔታዎች በማስረዲት ከተጠያቂነት ነፃ ለመሆን የመከላከያ ማስረጃ አቅርበዋል። ሆኖም አመልካች ለድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ያልቀጠሩና ያልወከለ መሆኑና የአስተዲደር ሥራዎን ብቻ ለወ/ሮ ድርሻዬ ከበደ የወከለ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ለሰራተኞቹ የቃል ማስጠንቀቂያ የሰጠ መሆኑን ያስመሰከረ ቢሆንም አመልካች የቃል ማስጠንቀቂያ በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56 ንዐስ አንቀፅ 3(ለ) በተደነገገው መሰረት ማንኛውም በጎ አሳቢ ሰው ሉያደርገው የሚችለውን ጥንቃቄ ያደረገና ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ድርጅቱን በመምራት ኃላፉነቱን የተወጣ መሆኑን የሚያረጋግጥ አይደለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላላገኘነው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀፅ 2(ለ)(2) መሰረት አፅንተነዋል።
ው ሣ ኔ
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.