No summary available.
ጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ነኢማ አወል ተጠሪ፡- የገቢዎች እና ጉምሩክ ዓቃቤ ሕግ ኃ/ስላሴ ገ/መድህን ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መሰረት የሆነው ጉዲይ የጉምሩክ አዋጅ በመተላለፍ ወንጀል ፈጽማለች በማለት ተጠሪ በአመልካች ላይ የመሰረተውን የወንጀል ክስ የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው አመልካች የተከሰሰችው በጉምሩክ አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 66/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ከደባይ ወደ ኢትዮጵያ በቦላ አለም አቀፍ አየር ማረፉያ ስትገባ የጉምሩክ ሥነ-ሥርአት ያልተፈጸመባቸው የተለያዩ የሞባይል መለዋወጫዎችን እና የተዘጋጁ አልባሳቶችን ይዛ ተገኝታለች ተብላ ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠችው መልስ በአቃቤ ሕግ ክስ የተነገረውን ወንጀል አልፈጸምኩም በማለት በመከራከርዋ ክሱ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረቡትን ማስረጃዎች ሰምቶአል። ከዚህ በኋላም አመልካች ልትከላከል ይገባል በማለት ብይን በመስጠት የመከላከያ ማስረጃዋን ሰምቶአል። በመጨረሻም አመልካች ጥፊተኛ መሆንዋን በማረጋገጡ ይዛው የተገኘችው እቃ እንዱወረስ፣በእቃው ላይ ሉከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ በሚያህል የገንዘብ መቀጮ ብር 114,076.46(አንድ መቶ አስራ አራት ሺህ ሰባ ስድስት ብር ከአርባ ስድስት ሳንቲም) እንድትከፍል እና በሁለት ዓመት እስራት እንድትቀጣ ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔውን አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች የተከሰሰችበት የወንጀል ድርጊት መታየት ያለበት በአዱሱ የወንጀል ሕግ መሰረት ነው ወይንስ በጉምሩክ አዋጅ ቁ.
60/89? የሚለውን ጭብጥ ለመመርመር ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ፣እንደዚሁም የሰበር ችልቱ በሰበር መ/ቁ. 42753 ከሰጣቸው ውሳኔዎች ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ከላይ እንዲመለከትነው የሥር ፍ/ቤቶች ክርክሩን የሰሙትና በመጨረሻም ውሳኔ የሰጡት የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 60/89 በተቀመጡት ድንጋጌዎች መሰረት ነው። የሰበር ችልቱ ከፍ ሲል በተጠቀሱት መዝገቦች ተመሣሣይ አቤቱታ ቀርቦለት በእርግጥም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የጉምሩክ አዋጅ አንደሆነ በመግለጽ ውሳኔ ሰጥቶአል። በዚህም ለጉዲዩ አወሳሰን ተገቢነት ያለው አዱሱ የወንጀል ሕግ ነው በሚል የቀረበውን ክርክር ውድቅ አድርጏአል። በያዝነው ጉዲይም ይኸው ቀደም ሲል የተሰጠው የሕግ ትርጉም አስገዲጅነት ያለው ስለሆነ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልቻልንም።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 139937 መጋቢት 21 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 79028 ነሐሴ 2 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕግ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 195/2/ለ(2) መሰረት ፀንተዋል።
አመልካች ያቀረበችው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.