No summary available.
ጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አሸናፉ አበበ - ጠበቃ ኒቆዱሞስ ጌታሁን ቀረበ ተጠሪ፡- የጉምሩክ ዓቃቤ ሕግ - ታደለ ተስፊዬ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የጉምሩክን ሕግ በመተላለፍ ወንጀል ፈጽሞአል በማለት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበውን ክስ መነሻ በማድረግ የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ተጠሪ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ አመልካች እና በወቅቱ ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረው ታደለ ገብሬ ኪዲኔ የተባለው ግለሰብ የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራርን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 228 እና 66/2/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የጉምሩክ ሥነ-ሥርአት ያልተፈጸመባቸውን አልባሳት ይዘው የማስተላለፍ ወንጀል ፈጽመዋልና ቅጣት ይወሰንባቸው በማለት ጠይቆአል።
ተከሣሾቹ ለክሱ በሰጡት መልስ በክሱ የተነገረውን ድርጊት አልፈጸምንም፤ ጥፊተኛም አይደለንም በማለት በመከራከራቸው ፍ/ቤቱ በዓቃቤ ሕጉ የቀረቡትን ማስረጃዎች ከሰማ በኋላ ተከሣሾች ሉከላከለ ይገባል በማለት ብይን ሰጥቶአል። በዚህ መሰረትም የመከላከያ ማስረጃዎች የሰማ ሲሆን፣በመጨረሻም ተከሣሾች እንደክሱ አቀራረብ ተመስክሮባቸዋል። ለማስተባበልም አልቻለም በማለት በተጠቀሰባቸው ሕግ መሰረት ጥፊተኞች ናቸው ብልአቸዋል። ሲያስተላልፈት የተገኘው አልባሳት እንዱወረስ፣ለአልባሳቱ ሉከፈል ይገባ የነበረው የቀረጥና ታክስ መጠን በሚያህል ገንዘብ ብር 10,520.33(አስር ሺህ አምስት መቶ ሃያ ብር ከሰላሣ ሦሥት ሣንቲም) ለመንግስት እንዱከፍለ እና በአስራ አምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ወስኖባቸዋል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን የሰማ ሲሆን፣በመቀጠልም ይግባኝ የተባለበትን ውሳኔ አጽንቶአል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች መጋቢት 28 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ለተፈጸመው ድርጊት በአቃቤ ሕግ የተጠቀሰው የአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 66/2/ አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ዓቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ የጠቀሰው ድንጋጌ አግባብነትን ለመመርመር የክስ ቻርጁን ይዘት ማየት አስፈላጊ በመሆኑ ተመልክተነዋል። በቻርጁ ላይ የተገለጸው አመልካች አልባሳቱ ተጭነው የተገኙበትን መኪና ሲያሽከረክር እንደነበር፣አብሮ የተከሰሰው ታደለ ገብሬ ኪዲኔ የተባለው ደግሞ አልባሳቱን ያስጫነ እንደሆነ፣ መኪናው የመጣው ከናዝሬት መስመር ወደ አዱስ አበባ ሲሆን፣አመልካች አቃቂ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ኬላ ላይ እንደደረሰ የጉምሩክ ሰራተኞች ለፍተሻ እንዱቆም ሲጠይቁት ኬላውን ጥሶ መሄደን፣በኋላም በተደረገው ክትትል በተለምድ ሃና ማሪያም አካባቢ ተይዞ ፍተሻ ሲደረግ አልባሳቱ መገኘታቸውን ነው። ዓቃቤ ሕግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች ልክ እንደ ክሱ እንዲስረዲ አቤቱታ በቀረበበት ውሳኔ ተመልክቶአል። በክሱ የተጠቀሰው የጉምሩክ አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 66/2/ የኮንትሮባንደ ድርጊት/ጥፊት/ የተፈጸመው ሃይል በመጠቀም ወይም ከላልች ጋር በማበር ሆኖ በተገኘ ጊዜ የሚጠቀስ እንደሆነም ከድንጋጌው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል። በመሆኑም መጠቀሱ በአግባቡ ነው ብለናል። አቤቱታ በቀረበበት ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 136351 ጥር 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 76902 መጋቢት 7 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕግ ሥ/ቁ. 195/2/ለ/2/ መሰረት ፀንተዋል።
አመልካች ያቀረበው የሰበር ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለናል።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.