No summary available.
ታህሳስ 06 ቀን 2002 ዓ.ም.
ዳኞች፡ መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን - ነ/ፈጅ ወንደ ለማ ቀረቡ ተጠሪ፡
ይህ ጉዲይ ከጉምሩክ ቀረጥ አከፊፈል ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ በቀረበው ክሰ አንደኛ ተጠሪ የተለያዩ ኤላትሮኒክስ ዕቃዎችን በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ አስገብተው በወኪል ደንበኛቸው ሁለተኛ ተከሣሽ አማካይነት ዱክለራሲዮን በመሙላት ቀረጥና ታክስ ለመክፈል ከሚያስፈልጉ ሰነድች ጋር በማቅረብ የዕቃዎቹ ዝርዝር ዋጋቸው በዲታ ቤዝ ሲፈለግ 23 የሚሆኑት ዕቃዎች ዋጋቸው ባለመገኘቱ ትክክለኛ ዋጋቸው ከዋናው መ/ቤት እስከሚላክልን ድረስ ዕቃው እንዲይቆይ ዋጋው በኘሮፖርሽን ተሰልቶ ብር 285,259.85(ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ብር ከሰማንያ አምስት ሣንቲም) ከፍለው ንብረቱን ተረክበው ወስደዋል።
ሆኖም የእነዚህ 23 ዕቃዎች ዋጋቸው ከዋናው መ/ቤት ተገልጾልን በዚሁ መሰረት ቀረጥና ታክስ ሲሰራ መክፈል የነበረበት ብር 47,638.34 ሳይከፈል የቀረ መሆኑ ተረጋግጧል። ቀረጥና ታክስ በማንኛውም ምክንያት ከዋጋቸው በታች የተከፈለ መሆኑ በምርመራ የተደረሰበት ከሆነ ያልተከፈለውን ቀሪ ቀረጥ ወይም ታክስ የማስከፈል ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 60/89 በአንቀጽ 57/1/ መሰረት ለከሣሽ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ በዚሁ መሰረት ተከሣሾች በቀሪነት የሚፈለገውን ክስ የቀረበበትን ብር 47,638.34(አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሣ ስምንት ብር ከሰላሳ አራት ሣንቲም) ከነወለድ እንዱከፍለ እንዱወሰንባቸው በማለት ጠይቀዋል።
አንደኛ ተጠሪም ቀርበው በሰጡት መልስ ተከሣሸ አሟልቶ ማቅረብ የሚገባውን ሰነድች በሙለ ለከሣሽ አቅርቦ ከሣሽም ሂሳቡን አሰልቶ የሸቀጡን ዋጋ ትክክለኛነት አረጋግጦ ቀረጡን የተቀበለ ሰለሆነ በቀረጥ ሰብሳቢው ታምኖበት ቀረጥ ተከፍል ዕቃው ከወጣ በኋላ ቀሪ ሂሳብ ለመጠየቅ ከሣሸ መብት የለውም። ከሣሽ በክሱ ኘሮፖርሽን ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ በምን ሂሳብ ስላት እንደተሰላ እና የዕቃዎቹን ዋጋ ግኝት ምንጩን በመጥቀስ በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 48 መሰረት ወደ አገር ስለሚገባ ዕቃ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ በዝርዝር አላስረዲም። ስለሆነም ከሣሽ በክሱ በሕጉ መሰረት እንዳት ተመርምሮ ቀሪ ሂሳብ እንደተገኘ በአዋጅ መሰረት ያላስረዲ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ሁለተኛ ተከሣሽም የቀረበልኝ ድክመንት ትክክል መሆኑን አረጋግጪ ለከሣሸ መ/ቤት በማቅረብ በየደረጃው ያለ የጉምሩክ ሰራተኞች አይተው የዋጋ ማስተካከያ ካደረጉ በኋላ የቀረጡን ትክክለኛነት አምነውበት በፊርማቸው ካረጋገጡ በኃላ ክፍያው የተፈጸመ ስለሆነ ክሱ ያላአግባብ የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ጉዲዮን ከሣሽ ቀሪ የቀረጥ ክፍያ ጥያቄው እንዳት እንደተገኘ እንዱያስረዲ በታዘዘው መሰረት የከሣሸ መ/ቤት የታሪፍና ትመና መምሪያ ክፍል ሰራተኛ ቀርበው ሲያስረደ አንደኛ ተከሣሸ ያስገቡት ዕቃ የዋጋ ስጋት ካለባቸው አገር የመጡ በመሆኑ በጉምሩክ መመሪያ ቁጥር 3/1996 አንቀጽ 8 ከተራ ቁጥር 1-3 በተመለከተው መሰረት ቀረጡ በኘሮፖርሽን የተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ሆኖም ግን ፍ/ቤቱ የተባለውን መመሪያ አስቀርቦ እንደተመለከተው መመሪያው የወጣው ከቀረጥ ነፃ የገቡ ዕቃዎች ለላላ ወገን በሚተላለፊበት ጊዜ የእርጅና ቅናሽ ስለሚታሰብበት ሁኔታ ሲሆን የመመሪያው አንቀጽ 8 ቀረጥ በኘሮፖርሽን እንደሚለካ የማይደነግግ በመሆኑ የከሣሽ ክርክርም ሆነ የምስክርነት ቃለ ተቀባይነት የለውም ካለ በኃላ በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 48/1/ መሰረት ወደ አገር ውስጥ የሚገባ ዕቃ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ሆኖ የሚወሰደው ለዕቃው መግዣ፣ዕቃውን እስከ ኢትዮጰያ የመጀመሪያ የጉምሩክ ወደብ ድረስ ለማጓጓዝ እንደዚሁም ለመድን ዋስትና አረቦን የወጣው ወጭ ድምር እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን ነገር ግን እነዚህ በአስመጪው በኩል የሚቀርቡት ሰነድች ተቀባይነት የላቸውም ተብል በጉምሩክ ባለሥልጣን ከተወሰነ ቀረጡ ሉለካ የሚገባው በአንቀጽ 48/3/ እስከ 10 ድረስ በተመለከተው አኳኃን መሆን እንዲለበት ተመልክቶአል። ሆኖም አንደኛ ተከሣሽ ከውጭ አገር ያስገባው ዕቃ ዋጋ ተቀባይነት የለውም። ተብል ቀሪ ቀረጥ እንዱከፍል የተጠየቀበት አግባብ በአንቀጽ 48 ላይ በዝርዝር በተደነገገው መሰረት ስለመሆኑ የባለሙያ ማስረጃ በማቅረብ ከሣሸ ያላስረደ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ከሣሽ በውሣኔው ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ ተጠሪዎች ተጨማሪ ቀረጡን ሉከፍለ አይገባም ተብል ውሣኔ መሰጠቱ ከሕጉ አኳያ ተገቢነቱ ተመርምሮ ሉወሰን እንደሚገባው በመታመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የአመልካች የቀሪ የቀረጥ ክፍያ ጥያቄ አግባብነት ከሕጉ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ወደ አገር የሚገባ ዕቃ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ምን ያህል እንደሆነና እንዳት እንደሚሰራ በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 48 ሥር ተዘርዝሯል። በልላ በኩልም ወደ ሃገር በገባ ወይም ከሀገር በወጣ ዕቃ ላይ የተከፈለው ቀረጥ በማናቸውም ምክንያት ሉከፈል ከሚገባው ቀረጥ ያነሰ መሆኑ በምርመራ የተደረሰበት እንደሆነ ባለሥልጣኑ የዕቃውን ባለቤት ወይም ወኪለን በልዩነት ያልተከፈለውን ቀረጥ ማስከፈል እንደሚችል በአንቀጽ 57/1/ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶታል።
አመልካች በቀሪነት የሚፈለግ የቀረጥ ክፍያ ስላለ ተጠሪዎች ይህንኑ ቀሪ ክፍያ ሉከፍለ ይገባል በማለት ክሱ የተመሰረተው ተጠሪዎች ያስገቡት ዕቃ ኢንቮይሳቸው ዋጋው በመ/ቤቱ ከሚገኘው ዲታ ቤዛችን ጋር ሲወዲደር አንሶ በመገኘቱ ውድቅ ተደርጎ በዲታ ቤዙ መሰረት ዋጋ ሲፈለግ የተወሰኑት ዕቃዎች ዋጋቸው ስላልተገኘ በተገኙትና ባልተገኙት መካከል ያለውን ልዩነት የመ/ቤቱ መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት በኘሮፖርሽን ተሰርቶ ቀረጡን እንዱከፍለ ከተደረገ በኃላ ዝራዝራቸው በዲታ ቤዝ ያልተገኙ ዕቃዎች ዋጋቸው ከዋናው መ/ቤት ሲላክልን በልዩነት የሚፈለግ ቀሪ የቀረጥ ክፍያ መኖሩን አረጋግጠናል በሚል ነው።
ተጠሪዎችም አመልካች በኘሮፖርሽን ቀረጥ ለማስከፈል የሚያሰችል የሕግ ድጋፍ የለውም ተገቢ ሰነድችንም አቅርበን ቀረጡ የተከፈለ ስለሆነ ቀሪ ክፍያ አለ ተብል የቀረበው ክስ የሕግ መሰረት የለውም በማለት ክርክር አቅርበዋል።
ሆኖም ግን የአመልካች መ/ቤት የዋጋ ዝርዝራቸውን በዲታ ቤዝ በተገኘውና ባልተገኘው መካከል ልዩነቱን በኘሮፖርሽን ስላት መሰረት እንደሚያስከፍል ለተጠሪዎች ሲገልጽ ተጠሪዎች ተቀብለው ቀረጡን ከፍለዋል።
አመልካች ቀረጡን የማስከፍላችሁ በኘሮፖርሸን ስላት ነው ካለ በልላ አገላለጽ የተጠሪዎችን ኢንቮይስ ውድቅ ማደረጉን የሚያመለክት ስለሆነ በአዋጁ አንቀጽ 53/1/ በተቀመጠው አግባብ መሰረት ተቃውሟቸውን አስመዝግበው የጉምሩክ ሹሙ በሚወሰነው መሰረት ቀረጥ መክፈል ይገባቸው የነበረ ሲሆን በዚህ መልኩ ተቃውሞ ካላደረጉ በኘሮፖርሽን ስላት የተጠየቀውን የቀሪ ቀረጥ ክፍያ ጥያቄ እንደተቀበለት የሚቆጠር ነው።
ስለሆነም አመልካች ክሰ የመሰረተበትን የቀረጥ ክፍያ ጥያቄ በተጠሪዎች በኩል በሕጉ አንቀጽ 53 አግባብ ተቃውሞ ያልቀረበበት እንደመሆኑ መጠን የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪዎች ተቃውሞ ባላቀረቡበት ሁኔታ አመልካች በኘሮፖርሽን ቀረጥ ለማስከፈል የሚችልበትን አግባብ አላስረዲም በማለት የክፍያ ጥያቄውን ሳይቀበለው መቅረቱ ከአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 57 እና 53/1/ አኳያ ተገቢነት የላለውና የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ ሕዲር 19 ቀን 2000 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እንደዚሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 2 ቀን 2001 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተሽሯል።
ተጠሪዎች አመልካች ክሰ ያቀረበበትን ብር 47,638.24/አርባ ሰባት ሺ ስድስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሀያ አራት / ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ተከፍል እስካለቀ ድረስ ከሚታሰብ 9 /ዘጠኝ በመቶ/ ወለድ ጋር እንዱከፍለ ተወስኗል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.