No summary available.
ጥቅምት 03 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ነ/ፈጅ ጌታቸው ምንተስኖት - ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። አመልካች በስር ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት ለአንደኛ ተጠሪ በወር ብር 350.00(ሦስት መቶ ሃምሳ ብር) ያከራያቸው ሲሆን ተከራይዋ ቤቱን ለሁለተኛ ተጠሪ ያስተላለፈ በመሆኑ የሚፈለግባቸውን ውዝፍ የቤት ኪራይ፣ቅጣት፣የውሃ እንዱሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱከፍለ እና ቤቱን እንዱያስረክቡ፣በተጨማሪም ቤቱን እስኪያስረክቡ ላለው ጊዜ ኪራይ እንዱከፍለ በማለት ጠይቋል። አንደኛ ተጠሪ ተጠርተው ስላልቀረቡ ጉዲዩ በላለበት የታየ ሲሆን ሁለተኛ ተጠሪ ግን ቀርበው ለቀረበባቸው ክስ መልስ ሰጥተዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ እንዱከፈል ሳይጠየቅ 2 አመት ያለፈው የቤት ኪራይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2024(መ) መሰረት እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው፣ ቀሪውን ውዝፍ የቤት ኪራይ፣የውሃ ክፍያና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጠሪዎች ይክፈለ፣የኪራይ ውለ ተቋርጧል፣ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች ያስረክቡ፣ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ ያለውን የቤት ኪራይ ሁለተኛ ተጠሪ ይክፈለ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካችም አንደኛ ተጠሪ ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ በየወሩ የቤት ኪራይ እንዱከፍለ ቢወሰንም ከኪራዩ ጋር ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱከፍለ ውሳኔ ስላልተሰጠ ይኸው እንዱታረምለት ይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታም አመልካች ለንግድ አገልግልት ከሚያከራያቸው ቤቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የመሰብሰብ ግዳታ በአዋጅ የተጣለበት በመሆኑ ቤቱን እስኪረከብ ድረስ ተጠሪዎች ከውርሃዊ ኪራይ ጋር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሉከፍለ ይገባል የሚል ነው።
ይህ የሰበር ችልትም የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረጉ ሁለተኛ ተጠሪ ቀርበው መልስ የሰጡ ሲሆን አመልካችም የመልስ መልስ ሰጥቷል። አንደኛ ተጠሪ ግን ተጠርተው መልስ ያልሰጡ በመሆኑ ችልቱ መዝገቡን መርምሯል።
ይህ ችልት ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ ወርሃዊ ኪራይ እንዱከፍለ ሲወሰን ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱከፍለ ሳይወሰን መታለፈ አግባብ ነው? አይደለም? የሚለውን ነጥብ መርምሯል።
አመልካች ለንግድ ድርጅትነት የሚያከራያቸው ቤት ላይ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 መሰረት ታክስ የመሰብሰብ ግዳታ ያለበት ለመሆኑ ያቀረበውን ክርክር ሁለተኛ መልስ ሰጪ ክደው አልተከራከሩም። የሁለተኛ መልስ ሰጪ ክርክር ፍርድ ቤቱ የኪራይ ውለን ያፈረሰው በመሆኑ በላለ የኪራይ ውል የተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ አይችልም በማለት ነው። በአዋጅ ቁጥር 285/1994 መሰረት የንግድ ቤቶች የማከራየት የንግድ እንቅስቃሴ ከታክስ ነፃ ከሆኑት ግብይቶች ውስጥ እንደማይካተት የአዋጁ አንቀጽ 8 ያመለክታል። የስር ፍርድ ቤትም ቢሆን ይህንኑ የአመልካች ግዳታ ተገንዝቦ የኪራይ ውለ እስከተቋረጠበት እለት ድረስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተጠሪዎች እንዱከፍለ ወስኗል። በልላ በኩል አንደኛ ተጠሪ የኪራይ ገንዘቡን ባለመክፈላቸው የኪራይ ውለ የፈረሰ ቢሆንም ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ይዘው እየተገለገለበት በመሆኑ ላገኙት ግልጋልት የቤቱን ኪራይ በየወሩ እንዱከፍለ ተወስኖባቸዋል። በዚህ ውሳኔ ላይ ተጠሪው ያቀረቡት ቅሬታ የለም።
የንግድ ቤቱ ይዘው ስለሚገለገለበት የኪራይ ገንዘብ የሚከፍለ ከሆነ ደግሞ ኪራዩን ተከትል የሚመጣውን ተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዳታ ሉወጡ ይገባቸዋል። ይህ ግዳታ ደግሞ ከውል ሳይሆን ከሕግ የመነጨ ግዳታ ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የኪራዩ ገንዘብ እንዱከፈል ሲወስን የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዱከፈለው ሳይወሰን ማለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት መሆኑን ተገንዝበናል።
መ/ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 43032 ጥር 19 ቀን 2000 ዓ.ም ሰጠው ውሳኔና የፋ/ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 65580 ግንቦት 08 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሻሽለዋል።
ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ ከሚከፍለት የኪራይ ገንዘብ ጋር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሉከፍለ ይገባል ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.