No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አንዲርጌ ታደሰ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነ/ፈጅ - ቀረቡ
ጉዲዩን የጀመረው በባላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። አመልካች ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር በመኪናቸው ላይ ለሚደርስ አደጋ ለአስራ ሁለት አመታት የቆየ የመድን ውል ግንኙነት የነበራቸው መሆኑን ገልፀው በመኪናቸው ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ መኪናው ከጥቅም ውጪ በመሆኑ ተጠሪ ብር 400,000(አራት መቶ ሺህ) እንዱከፍላቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ የመድን ውለ የተቋረጠው ኀዲር 7 ቀን 2000 ሆኖ አደጋው የደረሰው ኀዲር 26 ቀን 2000 ዓ.ም በመሆኑ አመልካች ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቦ በአማራጭም ላልች ክርክሮች አቅርቧል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ አመልካች ታህሳስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ለተጠሪ ባቀረቡት ማመልከቻ ለአስራ ሁለት አመት በነበራቸው ውል ምንም አደጋ ባለመድረሱ ውለ ሳይታደስ ጊዜው ቢያልፍም ኀዲር 26 ቀን 2000 ዓ.ም ለደረሰው አደጋ ድርጅቱ አስተያየት አድርጏ ብር 100,000(መቶ ሺህ) እንዱከፍላቸው መጠየቃቸውን፣እንዱሁም የአመልካች ምስክር አመልካች ውለን ሉያድሱ ተጠሪ ዘንድ ሂደው መኪናው ላይ አደጋ በመድረሱ ክፍያ አንቀበልም ማለቱን መመስከራቸውን ገልፆ በአመልካችና በተጠሪ መሃከል ያለው የውል ግንኙነት በመቋረጡ አመልካች ክሱን ለማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ሰርዞታል።
የአሁኑ ሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በአቤቱታቸው የውለ ዘመን ከማለቁ በፉት ባለት ጥቂት ቀናት ውለን እንዲድስ ጠይቆኝ ስምምነቴን ስለገለጸኩ አረቦን ባለመክፈላ ብቻ ውለ ሉቋረጥ እንደማይችል የን/ህ/ቁ. 666/2//3/ አይችልም፣የሚል ነው። ይህ ችልትም የአመልካች ጥያቄ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ከን/ህ/ቁ. 666 አኳያ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪም ቀርቦ በሰጠው መልስ የን/ህ/ቁ. 666 ተፈፃሚነት የሚኖረው ውለ ፀንቶ ባለበት ጊዜ መሆኑንና የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉፀና ይገባል የሚልባቸውን ላልች ክርክሮች አቅርቧል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው አመልካች በባላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ የመሰረቱት ተጠሪ ለመኪናቸው የመድን ሽፊን ለመስጠት በገባው ውል መሰረት መኪናቸው ላይ አደጋ በመድረሱ የመድን ዋስትና እንዱከፍላቸው ነው። ተጠሪ በበኩለ አደጋው በደረሰበት እለት በአመልካችና በተጠሪ መሃከል የነበረው የመድን ውል ተቋርጦ ስለነበር አመልካች ክስ ለማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ክሱን ተቃውሟል። በመሰረቱ ማንኛውም ሰው ክስ ለማቅረብ የሚፈቀድለት ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ክሱ በተመሰረተበት ሃብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ሲኖረው እንደሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/ ድንጋጌ መረዲት የሚቻል ነው። አመልካችም ግራ ቀኙ ካደረጉት የመድን ውል የሚመነጭ መብት ያላቸው መሆኑን በማመን ነው ክስ የመሰረቱት። ነገር ግን በግራ ቀኙ መሃከል የተደረገው የመድን ውል ኀዲር 7 ቀን 2000 ዓ.ም ማብቃቱን ከመዝገቡ ተመልከተናል አመልካች ይህንን አላስተባበለም። ክርክራቸው ውለ ሉያበቃ ጥቂት ቀናት እንደቀሩት ተጠሪ ውለ እንዱታደስ ጠይቆኝ ፈቃደኛነቴን የገለጽኩ ስለሆነ አረቦን ክፍያ ባለመክፈላ ብቻ ውለ ሉቋረጥ አይችልም በማለት ነው።፡ ነገር ግን አመልካች በመኪናቸው ላይ አደጋ የደረሰው ውለ ከመታደሱ በፉት በመሆኑና ቀደም ሲል በነበረው የ12 አመታት የመድን ውል ግንኙነት በመኪናቸው ላይ አደጋ ባለመድረሱ ድርጅቱ አስተያየት አድርጏ ብር 100,000(መቶ ሺህ) እንዱከፈላቸው ማመልከታቸውን የስር ፍ/ቤት አረጋግጧል። ይህንም በአመልካችና በተጠሪ መሃከል የነበረው የመድን ውል ከተቋረጠ በኋላ አደጋው መድረሱን አመልካች ራሳቸው አምነው የተቀበለት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። በልላ በኩል ውለ እንደታደሰ የሚቆጠረው ተጠሪ ውለ እንዱታደስ አመልካችን ስለጠየቀ ብቻ ሳይሆን አመልካች ውለን ለማደስ ፈቃደኛ ሆነው በሕጉ አግባብ ውለን ሲያደርጉ ነው። ይህን ስለማድረጋቸው አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ የለም። በአጠቃላይ በአመልካችና በተጠሪ መሃከል የተደረገው የመድን ውል ኀዲር 7 ቀን 2000 ዓ.ም ካበቃ በኋላ ውለ ስላልታደሰ የውል ግንኙነታቸው ተቋርጧል። አመልካች የጠቀሱት የንግድ ሕጉ ቁጥር 666 ስንመለከተውም ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት የለውም። ምክንያቱም ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚ ላሆን የሚችለው በመድን ሰጪውና በመድን ገቢው መሃከል የፀና ውል ኖሮ መድን ገቢው በውለ በተመለከተው መሰረት የአረቦን ክፍያ መክፈል ሲያቋርጥ እንጅ የመድን ውል በላለበት ሁኔታ አይደለም። በተያዘው ጉዲይ ግን በአመልካችና በተጠሪ መሃል የነበረው ውል ጊዜው አብቅቶ ተቋርጧል። ስለሆነም አመልካች ይህንን ድንጋጌ መሰረት አድርገው ያቀረቡት ክርክር የድንጋጌውን መንፈስ ያላገናዘበ ነው። በልላ በኩል የመድን ዋስትና እንዱከፈለው የተጠየቀበት መኪና አደጋ የደረሰበት ኀዲር 26 ቀን 2000 ዓ.ም ስለመሆኑ በግራ ቀኙ የታመነ ጉዲይ ነው።
No topics extracted.
በመሆኑም አደጋው የደረሰው በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መሃከል የነበረው የውል ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ በመሆኑ አመልካች የመድን ዋስትና እንዱከፈላቸው ለመጠየቅ የሚያስችል መብት የላቸውም። በዚህም ምክንያት የስር ፍ/ቤቶች አመልካች ክስ ለማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለው ለማለት የሚቻል አይደለም።
ው ሣ ኔ
የባላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 06284 ጥቅምት 10 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ብይን እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 77050 ኀዲር 16 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።