No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ አብደራሂም አህመድ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢት/መድን ድርጅት - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ብሬ ሙሲሳ - በላለበት
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። አመልካች ለፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ለደንበኛው ለኢትዮጵያ ነዲጅ ድርጅት ናፍጣና ቤንዚን የጉዞ መድን ሽፊን የሰጠ ሲሆን ከነዲጁ ውስጥ 31,513 ሉትር የስር ተከሳሾች በሆኑት መኪና ሲጓጓዝ መኪናው ተገልብጦ 18,153 ሉትር የፈሰሰ በመሆኑና የነዲጁን ዋጋ ብር 45,927.09(አርባ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሰባት ብር ከዘጠኝ ሣንቲም) ለደንበኛው ስለከፈለ ይህንኑ ገንዘብ ከተከሳሾች መኃከል ኃላፉነት ያለበት ተለይቶ እንዱከፍለ እንዱወሰንለት አመልክቷል። የስር ሁለተኛ ተከሳሽ ከክሱ ወጪ የሆኑ ሲሆን ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ ጉዲዩ በእርቅ ማለቅ ያለበት ስለሆነ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ መቃወሚያውን ውድቅ አድርጓል። ተጠሪ በዋናው ጉዲይ ላይም በሰጡት መልስ ነዲጁን የጫነው መኪና ባለቤት ስላልሆኑ ኃላፉነት እንደላለባቸው ከነዲጁ ባለቤት ጋር ያደረጉት የማጓጓዝ ውል አለመኖሩን እንዱሁም ተዋዋይ ወገኖቹ የኢት/ነዲጅ ድርጅትና የጣና ፈሳሽ ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር ወደ ክርክሩ እንዱገቡ ጠይቀዋል። ሦስተኛ ተከሳሽ የነበረው ወይራ ትራንስፖርት ድርጅት ክስ የተመሰረተበትን ነዲጅ የጫነው ተሳቢ ነዲጁ ፈሰሰ ከተባለበት ቀን በፉት ለስር ሁለተኛ ተከሳሽ ያስተላለፈ በመሆኑ ኃላፉነት የላለበት ስለመሆኑ ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ የተጠሪ ጭነት መኪና ወደኋላ ተንሸራቶ እየተገለገለበት ያለውን ነዲጅ የጫነውን ተሳቢ እንዱገለበጥ በማድረጉ ተጠሪ ለጉዲቱ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2081(1) እና (2) መሰረት ኃላፉ ናቸው ሦስተኛ ተከሳሽ የነበረው ተሳቢውን አደጋው ከመድረሱ በፉት ለስር ሁለተኛ ተከሳሽ ያስተላለፈ በመሆኑ ኃላፉነት የለበት በማለት ተጠሪ በክስ የተጠቀሰውን ገንዘብ ለአመልካች እንዱከፍለ ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ከተመለከተ በኋላ በኢት/ነዲጅ ድርጅትና በጣና ፈሳሽ መጓጓ ዣ ባለንብረቶች ማህበር መኃከል በተደረገው ውል አንቀጽ 18 መሰረት ከውለ ትርጉምና አፈፃፀም ጋር ግንኙነት ባላቸው ምክንያቶች የሚነሳ አለመግባባት ሁለቱ በመረጧቸው ገላጋይ ዳኞች አማካኝነት እንደሚታይ ስምምነት ተደርጓል። አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው በን/ህ/ቁ 683 ባገኘው የመዲረግ መብት በመሆኑና ይህ የመዲረግ መብት ደንበኛው ባለው መብት ልክ ስለሆነ በአመልካችና በተጠሪ መሃከል የሚነሳው ክርክር በስምምነት ማለቅ ስላለበት ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የይግባኝ ሰሚውን ፍ/ቤት ውሳኔ አፅንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታው በአመልካች ደንበኛና በጣና ፈሳሽ ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር መሃከል የተደረገው ውል ተፈፃሚነት የሚኖረው በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መሃከል ለሚነሳ ክርክር እንጂ ለተያዘው ጉዲይ አይደለም። በተጠሪ ላይ ክስ የቀረበው የተረከቡት ነዲጅ ላይ ጉዲት በመድረሱ የአጓጓዥ ኃላፉነት ስላለባቸው በመሆኑ ከጉዲዩ ጋር ግንኙነት የላለውን ውል መሰረት በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚል ነው። ችልቱም የአመልካች ደንበኛ ከጣና ፈሳሽ መጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር ጋር ጉዲዩን በእርቅ ለመጨረስ ስለተስማማ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ በፍ/ቤት ላታይ አይገባም በሚል የተሰጠው ውሳኔን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪ በህይወት ስለላለ ወራሾቻቸው እንዱቀርቡ በጋዜጣ ጥሪ ቢደረግም ስላልቀረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ የመሰረተው በተጠሪ የጭነት መኪና እየተሳበ በነበረው ተሳቢ ላይ ተጭኖ የነበረው ነዲጅ ተሳቢው በመገልበጡ ምክንያት ፈሶ ስለባከነ ለደንበኛው የከፈለው ገንዘብ ተጠሪ እንዱተኩ ነው።
ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የአመልካች ክስ በፍ/ቤት ቀርቦ ላታይ አይገባም በማለት የወሰነው የአመልካች ደንበኛ ከጣና ፈሳሽ ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር ጋር ባደረገው ውል በሁለቱ መሃከል የሚነሳ ማንኛውም አለማግባባት በእርቅ ለመጨረስ ያደረገው ስምምነትን መሰረት በማድረግ ነው። በመሆኑም ይህ ውል በአመልካችና በተጠሪ መሃከል ላለው ክርክር ተፈፃሚነት አለው? የለውም? የሚለውን ጭብጥ ችልቱ መርምሯል።
No topics extracted.
ውል ተዋዋዮች የገቡቧቸው ግዳታዎች በመሃከላቸው አስገዲጅ እንዱሆኑ ወደውና ፈቅደው የሚመሰርቱ በመሆኑ ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዳታቸውን በፈቃዲቸው ወስነው ያቋቋሙት ውል ላላ ሦስተኛ ወገንን ሉያስገድድ የሚችልበት ሁኔታ የለም። በዚህም ምክንያት ነው ውልች ተፈፃሚነታቸውና አስገዲጅነታቸው ውለን ባቋቋሙ ተዋዋይ ወገኖች መሃከል ብቻ መሆኑ ፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731 ስር ተደንግጎ የምናገኘው።
በተያዘው ጉዲይ የአመልካች ደንበኛና ጣና ፈሳሽ ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር ባደረጉት ውል በሁለቱ መሃከል የሚነሳ ማንኛውም አለመግባባት በእርቅ ለመጨረስ ተስማምተዋል። የዚህ ውል ተዋዋዮች ሁለቱ ብቻ ሲሆኑ ተጠሪ ተዋዋይ ወገን አልነበሩም። ስለሆነም ይህ ውል ተፈፃሚነቱ ወይም አስገዲጅነቱ ውለን ባቋቋሙት ተዋዋይ ወገኖች ላይ ብቻ ነው። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይህ ውል በአመልካችና በተጠሪ መሃከል ተፈፃሚነት አለው የሚለው መደምደሚያ ላይ የደረሰው አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ ለማቅረብ የቻለው በደንበኛው መብት ተደርጎ ስለሆነ የሚኖረው ደንበኛው ያለው መብት ነው በማለት ነው። በእርግጥ በን/ህ/ቁ 683(1) መድን ወጪው ለደንበኛው በከፈለው የካሳ መጠን ልክ ለጉዲቱ ኃላፉ የሆነውን ሰው የሚጠይቀው በደንበኛው መብት ተደርጎ ነው። ይህ ድንጋጌ ግን መድን ሰጪው የከፈለውን የካሳ መጠን በሚመለከት ብቻ እንጂ የደንበኛው ላልች መብቶችና ግዳታዎችን ሁለ የሚመለከት ስላልሆነ በተያዘው ጉዲይ የአመልካች ደንበኛ ከጣና ፈሳሽ ማጓጓዣ ጋር ያደረገው ውል አመልካች በተጠሪ ላይ ለመሰረተው ክስ ተፈፃሚነት ሉኖረው አይችልም። ተጠሪ በዚህ ውል ተዋዋይ ወገን አልነበሩም። ምንም እንኳን አመልካች በከፈለው የካሳ መጠን ልክ የደንበኛውን መብት ተደርጎ የቀረበ ቢሆንም የአመልካች ደንበኛ ከተጠሪ ጋር የሚነሳ አለመግባባትን በእርቅ ለመጨረስ የተስማማበት ውል የለም። በመሆኑም የአመለካች ደንበኛ ከላላ 3ኛ ወገን ጋር የተደረገው ውል ከተያዘው ጉዲይ ጋር ግንኙነት ስለላለው አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ በእርቅ ሉያልቅ የሚገባው ስለሆነ ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላቸውም መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋ/መ/ደረጃ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 4 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 27 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ስላለው ይግባኝ ሰሚው የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን ይግባኝ ተቀብል ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።