No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ሣሙኤል ዓለሙ - ጠበቃ ፈቃደ አስፊው ቀረቡ መዝረቡን መርምረን ቀጥል የተመለከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ኩባንያ የመድን ሽፊን የገባሁለት የሰ.ቁ 3-34603 የሆነ መኪና በደረሰበት አደጋ ምክንያት ጉዲት ደርሶበታል። በመድን ውለ መሰረት ተከሳሽ ተገቢውን ካሣ እንዱከፍለኝ ብጠይቅም ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ ተከሳሽ ጉዲት የደረሰበትን መኪናዬን ሙለ ዋጋ ብር 235,000(ሁለት መቶ ሰላሣ አምስት ሺህ) እንደዚሁም መኪናው በጊዜው ባለመጠገኑ ወይንም ዋጋውን ባለመክፈለ ምክንያት በከሳሽ ላይ የደረሰውን የጥቅም መቋረጥ ብር 58,000(ሃምሣ ስምንት ሺህ) ጨምሮ ክሱ ካስከተለው ወጭና ኪሳራ ጋር እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሽ ክስና ማስረጃ ለተከሳሽ ደርሶ በሰጠው መልስ በከሳሽ መኪና ላይ ጉዲት የደረሰው ከመድን ውለ ውጭ ሁለት ሰዎችን ጭኖ ሲያጓጉዝ ሲሆን የመድን ሽፊን የተገባው ጭነት ጭኖ ሲጓጓዝ ለሚደርስ ጉዲት ነው።
ስለሆነም የከሳሽ መኪና ሰው ጭኖ ሲጓጓዝ ለደረሰው ጉዲት ከመድን ውለ አኳያ ተከሳሽ ካሣ ለመክፈል ግዳታ የለበትም። የክፍያ መጠኑን በተመለከተም ከሳሽ የደረሰበት መኪና ሉጠገን የማይችል ስለመሆኑ ባላስረደበት ሁኔታ ሙለ ዋጋ እንዱከፈላቸው መጠየቃቸው ተገቢነት የለውም። በመድን ውለ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠንም መኪናው የመድን ሽፊን በተሰጠው ጊዜ የተገመተ እንጂ አሁን ያለውን የመኪና ዋጋ ስለማያስረዲ በዚህ ልክ ካሣ ሉከፈል አይገባም። በመድን ውለ መሰረትም ተከሳሽ ለተቋረጠ ጥቅም ኃላፉነት የለበትም በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ ኃላፉነትን በተመለከተ ተከሳሽ በከሳሽ መኪና ላይ ጉዲት የደረሰው ሰው ጭኖ ሲጓዝ እንጂ ዕቃ ጭኖ ሲጓዝ ስላልሆነ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ቢከራከርም ሰው ጭኖ ጉዲት ስለመድረሱና የሰዎችን መጫን ከአደጋው ጋር ያለውን ግንኙነት አላስረዲም። ይልቁንም በማሰረጃነት የቀረበው የትራፉክ ፖሉስ ሪፖርት በከሳሽ መኪና ላይ ጉዲት የደረሰው መሐል መንገድ ላይ የገባን ሰው ለማዲን ሲሞክር መኪናው መንገደን ስቶ ከዛፍ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ስለሆነ ሰው ጭኖ መጓዙ የአደጋው መንስኤ ባለመሆኑ ተከሳሽ በመድን ውለ መሰረት በመኪናው ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የካሣ መጠኑን በተመለከተ ፍ/ቤቱ ጉዲት የደረሰበትን የከሳሽ መኪና በባለሙያ እንዱገመት አድርጎ ጉዲቱ በመቶኛ ሲሰላ 83.48% በገንዘብ ሲሰላ ደግሞ ብር 196,546.98(አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ከዘጠና ስምንት) አረጋግጦ ከ75% በላይ ጉዲት ከደረሰ እንደ ሙለ ውድመት /Total loss/ ስለሚቆጠር የመኪናውም ግምት ብር 235,000(ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ) እንደሆነ ግራ ቀኙ ባደረጉት የመድን ውል ላይ ስለተመለከተ ተከሳሽ ይህንኑ ገንዘብ ለከሳሽ እንዱከፍል የተቋረጠ ጥቅምን በተመለከተ ግን በመኪናው ላይ የደረሰው ሙለ ውድመት ስለሆነ ተከሳሽ ለመክፈል አይገድድም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ተከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ በተጠሪ መኪና ላይ በአደጋ ምክንያት ጉዲት በደረሰ ጊዜ 2 ሰው ጭኖ መገኘቱ ከመድን ውለ አኳያ አመልካች ኃላፉ ነው መባለ ተገቢነቱን ለማጣራት አቤቱታው ለሰበር እንዱቀርብ አድርጏ ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተጠቀሰው ሲሆን በበኩላችንም ጉዲዩን እንደሚከተው መርምረናል።
ምላሽ ማግኘት የሚገባውም የጉዲዩ ጭብጥ አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ ነው መባለ በአግባቡ ነው ወይንስ አይደለም? በአግባቡ ነው ከተባለስ የካሣ ክፍያው መጠን ተገቢነት አለው ወይንስ የለውም? የሚለት ናቸው።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካች ኃላፉ መባል የለብኝም በማለት አጥብቆ የሚከራከረው በተጠሪ መኪና ላይ ጉዲት ያደረሰው ሰው ጭኖ ሲጓዝ እንጂ ዕቃ ጭኖ ባለመሆኑ ከመድን ውለ አኳያ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ነው።
No topics extracted.
ተጠሪ በበኩለ በመኪናው ላይ 2 ሰዎች ተጭነው እንደነበረ አምኖ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች የተጫኑት የመኪናውን አገልግልት ከዕቃ መጫን ሰው ወደመጫን አገልግልት በመቀየር ሳይሆን በወቅቱ ተጭኖ የነበረው የመብራት ኃይል መ/ቤት ምሶሶዎችን ለመደገፍ፣ ለመጫንና ለማውረድ ተብል የጭነት ሥራ ለመሥራት ነው በማለት መከራከሩን ተገንዝበናል።
አመልካች በመድን ውለ መሰረት ካሣ ለመክፈል የምንገደደው መኪናው ዕቃ ጭኖ ሲጓዝ ለሚደርስበት ጉዲት እንጂ ሰው ጭኖ በሚጓዝበት ጊዜ አይደለም የሚል ክርክር ቢኖረውም የተጠሪ መኪና ሁለቱን ሰዎች የጫነው ከጭነት ሥራ ጋር በተያያዘ ያልተጫኑ ስለመሆኑና ሰዎችን ለማጓጓዝ ታስቦ የተጫኑ ስለመሆናቸው ማስረዲት የሚጠበቅበት ከመሆኑም በላይ ሰው የመጫኑም ሁኔታ ለአደጋው መንስኤ /Risk Possibility/ መሆኑንም ጭምር ማስረዲት ይጠበቅበታል ሆኖም ግን አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበው ማስረጃ ካለመኖሩም በላይ ይልቁንም ጉዲት የደረሰው በጉዞ ላይ መሐል መንገድ ላይ የገባን ሰው ለማዲን ሹፋሩ ጥረት ሲያደርግ መንገደን ስቶ በመውጣት ከዛፍ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት እንደሆነ በትራፉክ ፖሉስ ሪፖርት ላይ የተገለፀ ስለሆነ በተጠሪ መኪና ላይ የተጫኑት ሰዎች ኃላፉነቱን ከሚያስከትለው ሁኔታ ጋርም ሆነ ከካሣ ክፍያው ጋር ምንም የሚያገናኛቸው ስለላለ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
የካሣ ክፍያ መጠኑን በተመለከተ የተጠሪ መኪና ከአደጋው በኋላ ተገጭቶ ጉዲቱ በድምሩ ብር 196‚546.98(መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ስድስት ብር ከዘጠና ስምንት ሣንቲም) መሆኑ ተረጋግጧል የሥር ፍ/ቤቶች ለተጠሪ ካሣ እንዱከፈላቸው ውሣኔ የሰጡት የመኪናው ዋጋ ብር 235‚000(ሁለት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ) እንደሆነ በመድን ውለ ላይ ስለተመለከተ ይህንኑ አመልካች ለተጠሪ መክፈል አለበት በማለት ነው።
ሆኖም ግን ለአንድ ንብረት ወይም ዕቃ መድን የገባ ሰው ካሣ ሉከፈለው የሚችለው ጉዲት በደረሰ ጊዜ ዕቃው ከሚያወጣው ዋጋ ሳይበልጥ እንደሆነ በንግድ ሕግ ቁጥር 678 የተመለከተ ሲሆን የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤትም ጉዲት የደረሰበት የተጠሪ መኪና በባለሙያ እንዱገመት ትዕዛዝ ከሰጠ በኃላ ግምቱ ሲቀርብ በዚሁ ግምት መሰረት ካሣ እንዱከፈል መወሰን ሲገባው ከግምት በኋላ ተመልሶ በመድን ውለ ላይ የተቀመጠው የመኪናው ግምት እንዱከፈል መወሰኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ. በ12/2/2001 ዓ.ም. የሰጠው የኃላፉነት ውሣኔ እንደዚሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ሐምል 28 ቀን 2001 ዓ.ም. ይህንኑ የኃላፉነት ውሣኔ በማጽናት የሰጠውን ትዕዛዝ አጽንተናል። በልላ በኩልም የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከላይ በተጠቀሰው የመ/ቁጥር በ28/7/2001 ዓ.ም. አመልካች ብር 235.00 ካሣ ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ ከንግድ ሕግ ቁጥር 678 ጋር ያልተገናዘበ ስለሆነ በፍብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 348/1/ መሰረት አሻሽለን የተጠሪ መኪና በጉዲቱ ጊዜ በተገመተው መሰረት ብር 196,546.98/አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ብር አምስት መቶ አርባ ስድስት ከዘጠና ስምንት ሣንቲም/ ካሣ አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስነናል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።