No summary available.
ሚያዝያ 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ/ማ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጫልቱ ሚደግሳ - በላለበት **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የመድን ሰጪ የኃላፉነት መጠን የሚመለከት ነው። የአሁን አመልካች የመድን ሽፊን የሰጠው የሰላዲ ቁ 3 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ ንብረትነቱ የአቶ ሐብታሙ አለነህ ሆኖ በአቶ ጌታነህ አለነህ ሲሽከረከር የሰላዲ ቁጥር 3 የሆነ መኪና ገጭቶ በመኪናው ውስጥ የነበሩ አቶ ተመስገን ሚደግሳ እና ወ/ሮ ስኳሬ ዱቲን የገደለ በመሆኑ የካሣ ጥያቄ ክስ በወራሾች ቀርቦ አመልካችም በመድን ውል መነሻ በክርክሩ እንዱገባ መደረጉን መዝገቡ ያስረዲል። የአሁን አመልካች ኃላፉነት እና የካሣ መጠንን አስመልክቶ ክርክር ያቀረበ ቢሆንም ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ሥልጣን የተመለከተው የኢለባቡር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሾች ለጉዲቱ ኃላፉ ናቸው ካለ በኋላ የካሣ መጠኑም ብር 106,400(አንድ መቶ ስድስት ሺህ አራት መቶ) ብር እንዱከፈል ወስኗል።
ይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የካሳ መጠኑን በማሻሻል ባጠቃላይ ብር 68,200(ስልሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ) እንዱከፈል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል ሲል ሰኔ 16/2001 ዓ.ም በጠበቃው አማካይነት ባቀረበው አቤቱታ የሟች ወራሾች በቀጥታ ክስ ማቅረብ እንደማይችለ፣ የካሳ መጠን አስመልክቶ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ስሕተት እንደሆነ እና ካሣ መከፈል አለበት ከተባለም የአመልካች የኃላፉነት ወሰን ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ለአንድ ሰው እንደመሆኑ በጠቅላላ ከስልሳ ሺህ(60,000) በላይ የሚከፍልበት አግባብ ባለመኖሩ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በዚህ ረገድ እንዱታረም ሲል አመልክቷል።
ይህ ሰበር ችልትም አቤቱታውን ከመረመረ በኋላ የአመልካች የኃላፉነት ወሰን ከብር 60,000(ስልሳ ሺህ) በላይ መወሰኑ በአግባቡ ስለመሆኑ ለመመርመር ተጠሪ እንዱቀርቡ አዝዟል። ተጠሪ ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት እንዱወሰን ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል።
የአመልካች ኃላፉነት የመነጨው ከመድን ውል ስለመሆኑ ከመዝገቡ ተረድተናል። አመልካች ለሥር ተከሳሽ የሰጠው የመድን ሽፊን የሦስተኛ ወገን ኃላፉነት ስለመሆኑ እና ለአንድ ሰው የሚከፈለው ካሣ መጠን ጣሪያው ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ስለመሆኑም አላከራከረም። አመልካች የመድን ሽፊን የሰጠው የሥር ተከሳሽ መኪና ጉዲት ያደረሰው በሁለት ሰዎች ላይ ስለመሆኑም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው።
ስለሆነም በውለ መሰረት የአመልካች ኃላፉነት ወሰን ብር 60,000(ስልሳ ሺህ) መሆኑ ታውቋል። በንግድ ሕግ አንቀጽ 665(2) መሰረት ደግሞ የመድን ሰጪው ኃላፉነት በመድን ውለ የተመለከተውን የገንዘብ ወሰን መሰረት ካሣ መክፈል ግዳታ አለበት። አመልካችም እየተከራከረ የነበረው የኃላፉነት መጠን በውል ከተወሰነው በላይ ላሆን እንደማይገባ ነው። ከዚህ አንፃር አመልካች በግልፅ ውለን እና ሕጉን መሰረት አድርጏ ክርክሩን አቅርቦ እያለ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንኑ ባለማገናዘብ አመልካች ከውል ግዳታው በላይ ብር 68,200(ስልሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ) እንዱከፍል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል ብለናል።
ስለሆነም በዚህ ረገድ የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማረም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
አመልካች በዋስትና ውል በተመለከተው መሰረት ለመክፈል የሚገደደው ብር ስልሳ ሺህ (60,000) ብቻ ነው ብለን የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት የመ/ መጋቢት 22/2002 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ወስነናል።
በኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት የተወሰነውን ቀሪ የካሣ ገንዘብ የሥር አንደኛ ተከሳሽ ሉከፍል ይገባል ብለናል።
በዚህ ፍ/ቤት ተሻሽል በተወሰነው መሰረት የኢሉባቡር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱያስፈጽም ታዟል።
ይፃፍ።
No topics extracted.