No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአረቦን ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ ኀዲር 01 ቀን 2000 ዓ.ም በአሁኑ አመልካች እና በአቶ አህመድ ማሞ ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ተጠሪ የሰላዲ ቁጥር 3-33558 ሆኖ ንብረትነቱ የአቶ አህመድ ማሞ ለሆነው ተሽከርካሪ አመልካች ጋር በጠየቁት መሰረት የመድን ውል ማድረጉን፣ከእ.ኤ.አ ከ18/08 እስከ 18/08/2004 ድረስ ከሚፈለግባቸውን የአረቦን መድን ክፍያ ውስጥ ብር 24,472.89(ሃያ አራት ሺህ አራት መቶ ሰባ ሁለት ብር ከሰማንያ ዘጠኝ ሳንቲም) ያልከፈለ መሆኑን ገልፆ ይህንኑ ገንዘብ ከነ ሕጋዊ ወለድና ከልዩ ልዩ ወጪዎች ጋር አመልካችና አቶ አህመድ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰነለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካችም በተከሳሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መከላከያ መልስ፤የተጠሪ ጥያቄ በይርጋ የታገደ መሆኑን፣የመድን ውለ ተዋዋይ ባለመሆኑ ክስ ላቀርብበት እንደማይገባ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስቶ የተከራከረ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም የተጠየቀው የአረቦን ገንዘብ ክፍያ ጥያቄ የውል ዘመኑ አልፍ ውለ ከተፈፀመ በኋላ የቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት እንደላለው፣ውለ በሁለት ምስክሮች ፉት ያልተደረገ በመሆኑ በሕግ ፉት የሚፀና አለመሆኑን፣የአረቦን ክፍያ አልከፈለም ከተባለ ተጠሪ ውለን ከማቋረጥ ውጪ አረቦን ይከፈለኝ በማለት ክስ ማቅረብ እንደማይችል ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የአሁኑን አመልካች መከራከሪያ ነጥቦችን ውድቅ በማድረግ ለክሱ ገንዘብ ኃላፉ አድርጏ ብር 24,472.89(ሃያ አራት ሺህ አራት መቶ ሰባ ሁለት ብር ከሰማንያ ዘጠኝ ሳንቲም) ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ 9%(ዘጠኝ ከመቶ) ወለድና ከልዩ ልዩ ወጪዎች ጋር ከአቶ አህመድ ማሞ ጋር በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍል ሲል ወስኖበታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ድርጅት ነገረ ፈጅ ግንቦት 24 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡-ጉዲዩ በሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ የሚታገድ ሆኖ እያለና ውለም መሰረትም የተፈፀመ ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የን/ሕ/ቁ. 666 እና 674 እንዱሁም ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያደረገው የመድን አረቦን ውል ሳይኖር የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1731 እና 1952 ድንጋጌዎችን ባላገናዘበ መልኩ አመልካችን ለአረቦን ገንዘብ ክፍያ ጥያቄ ኃላፉ ማድረጋቸው ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት የተከራከረው ክርክር መታለፈ ከን/ሕ/ቁ. 674 ድንጋጌ አንፃር አግባብ መሆን ያለመሆኑን ለመመረመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏ የተጠሪ ነገረ ፈጅ ኀዲር 10 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የጽሐፍ መልስ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አግባብነት ይደግፊለ ያሎቸውን ምክንያቶች በመዘርዘር ውሳኔው ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች አቶ አህመድ ማሞ ከተባለ ግለሰብ ጋር በመሆን የመድን አረቦን ገብቶ የተዋዋለ መሆኑን፣የመድን ውልም እንዱታደስ ጥያቄ አቅርቦ በጥያቄው መሰረት ተጠሪ ማደሱን፣ግራ ቀኙን የሚያከራክረው የአረቦን ገንዘብ ክፍያ መከፈል በነበረት ጊዜ ባለመከፈለ ተጠሪ የይከፈለኝ ጥያቄ ማቅረቡ በይርጋ የታገደ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው የሕግ ጥያቄ ነው።
በመሰረቱ አመልካች ለክርክሩ መሰረት ያደረገው የን/ሕ/ቁ.674/1/ ሲሆን የድንጋጌው ሙለ ይዘትም፡በኢንሹራንስ ውል ምክንያት የሚቀርብ ማንኛውም ክስ የሚታገደው ለክሱ ምክንያት የሆነው ጉዲት ከተደረገበት ወይም በጉዲዩ ላይ ጥቅም ያላቸው ወገኖች ጉዲቱን ካወቁበት ቀን ጀምሮ ከሁለት አመት በኋላ ነው የሚል ሲሆን የእንግሉዝኛው ትርጉምም፡- Any claim arising out of a contract of insurance shall be barred after two years from the occurrence giving rise to the claim or from the day when the parties knew of the occurrence.
በሚል ተቀምጧል።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት በኢንሹራንስ ውል ላይ ተመስርቶ የሚቀርብ ማንኛውም ክስ ጥያቄውን ለማቅረብ የሚያስችለው ምክንያት በተከሰተ ወይም ጥቅም ያላቸው ወገኖች ጉዲዩን ካወቁበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ እንዲለበት መገንዘብ አያዲግትም።
በተያዘው ጉዲይ የመድን አረቦን መከፈል የነበረበት ጊዜ ሁለት ዓመት ያለፈው ስለመሆኑ ተጠሪም የማይክደው ፍሬ ጉዲይ ሲሆን ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረው ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ድንጋጌ በንግድ ሕጉ የተመለከተው ሳይሆን በፍ/ብ/ሕጉ አንቀጽ 1845 ስር የተመለከተው ነው በማለት ነው። ሆኖም ጉዲዩ የኢንሹራንስ ውልን መሰረት ያደረገ እንደመሆኑ መጠን በንግድ ሕጉ የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የማይኖርበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን ከላይ የተመለከተው ድንጋጌ ግልጽ ከመሆኑ አንፃር የምንገነዘበው ነጥብ ነው። በመሆኑም ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 754/1/ ስር የተመለከተው ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1677 እና 1845 መሰረት በማድረግ አመልካች ያቀረበውን የይርጋ ክርክር ውድቅ ያደረገው ያላግባብ ስለሆነ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 102951 ጥቅምት 05 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 72894 ግንቦት 03 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ የጠየቀው የመድን አረቦን ይከፈለኝ ጥያቄ በሁለት አመት ይርጋ ጊዜ የታገደ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.