No summary available.
ታህሳስ 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነገረ ፈጅ ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ ሐሰን ኢብራሂም - ጠበቃ ስለሺ ዘዬሐንስ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የብድር ውልን የተመለከተ ሲሆን ጉዲዩ የተጀመረው የአሁን አመልካች የአሁን ተጠሪ በ05/08/87 ዓ.ም በተፈረመ ውል ብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ) ተበድረው በየወሩ ብር 18,000(አስራ ስምንት ሺህ) እየከፈለ ከሚያዝያ ወር 1988 ዓ.ም የተስማሙ ቢሆንም ብድሩን በውለ መሰረት አልከፈለም። በመሆኑም በመያዣነት ለአመልካች ከሰጧቸውና አመልካች የመድን ሽፊን ከገዛላቸው ተሽከርካሪዎቻቸው ውስጥ ሁለቱን ያስረከቡ ቢሆንም በሉብሬያቸው ላይ የተጭበረበረና የተምታታ ነገር በመኖሩ ሉሸጡ አልቻለም። ስለዚህ ተጠሪ በዓመት 14% ወለድና 3% የወለድ መቀጫ ለመክፈል በተስማሙት መሰረት የሚፈለግባቸውን ብር 396,904.52(ሦስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አራት ብር ከሃምሳ ሁለት ማንቲም) እና ላልች ወጪዎችን እንዱከፍለ ይወሰንልን ሲል ባቀረበው ክስ ነው።
ተጠሪ በሰጡት መልስ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ተሽከርካሪዎቹ ለፍርክልዠር የሐራጅ ሽያጭ የቀረቡ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 244(2/ሐ) መሰረት አንደኛው የህግ እርምጃ እየተካሄደ ሳለ በተደራቢነት ክስ ሉመሰረትብኝ አይገባም በማለት ቅድመ መቃወሚያ አቅርበው በፍሬ ጉዲዩ መልስ ሰጥተዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም አመልካች ለተጠሪ ገንዘብ በብድር ሰጥቶ ለብድሩም መያዣዎችን ይዟል። ብድሩ ባልተከፈለው ጊዜ በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ወይም በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት የያዘውን ንብረት በሐራጅ በመሸጥ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል። ይህ ማለት ግን ሁለቱንም አማራጮች በአንድ ጊዜ በአንድ ላይ ይጠቀማል ማለት አይደለም። በተያዘው ጉዲይ ግን አመልካች ያበደረውን ገንዘብ ለማስመለስ በፍ/ቤት ክስ ያቀረበው በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት የያዘውን ንብረት ተረክቦ በሐራጅ ለመሸጥ በእንቅስቃሴ ላይ እያለ ነው። ስለሆነም ጉዲዩ በልላ በፍ/ቤት (በባንኩ በራሱ) ተይዞ እያለ እና ተሽከርካሪዎቹ ተሸጠው የሚያወጡት ገንዘብ ለብድሩ ወይም ለዕዲው በቂ መሆን አለመሆኑ ሳይረጋገጥ በዚህ ፍ/ቤት ክስ ማቅረቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 244(2/ሐ) መሰረት ተቀባይነት ስለላለው ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 245(2) መሰረት ተዘግቷል በማለት ወስኗል።
የአሁን አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ የካቲት 11 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት ብድሩን ሲወስደ ለመያዣነት ከአስያዟቸው መኪናዎች መካከል የሰላዲ ቁጥር 2-13518 አ.አ. በብር 17,500.00(አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ) የካቲት 29 ቀን 1998 ዓ.ም በወጣው ጨረታ የሰላዲ ቁጥሩ 3-26916 የሆነው ደግሞ ነሐሴ 24 ቀን 1998 ዓ.ም በወጣው ጨረታ በብር 152,000.00(አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ) መሸጣቸው እና ላላው መኪናም ሉገኝ አለመቻለ ተገልጾ እያለ፤ አዋጅ ቁጥር 97/90 ባንክን ክስ ከመመስረት የሚከለክለው ባለመሆኑ የብድር እዲ እንዱመልሱ በተጠሪ ላይ የቀረበው ክስ የፍርክልዠር ሥርዓቱን ሳይጨርስ መቅረብ የለበትም ተብል ውድቅ መደረጉ የአዋጁን መንፈስ ያላገናዘበ ስለሆነ ሉሻር ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ክሱ ከቀጠለ በኋላ አመልካች በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች ሽጧል መባለ በክርክሩ ሂደት የሚቀር ዕዲ መኖሩንና አለመኖሩን አረጋግጦ ክስ እንዱቀጥል ወይም እንዱቋረጥ በማድረግ ፊንታ በመያዣ የተያዙ ንብረቶች መሸጫውን ብቻ መነሻ በማድረግ ክርክሩን የሚያቋርጥ ነው ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ የግራ ቀኙ ክርክር ሐምል 08 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ሉመረመር ይገባዋል ተብል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ከአመልካች የወሰደትን ገንዘብ በወቅቱ ባለመመለሳቸው አመልካች በመያዣነት ከያዛቸው ተሽከርካሪዎች መካከል በሕጉ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ራሱ ለመሸጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበት ጊዜ በፍ/ቤት ተጠሪ ብር 396,904.52(ሦስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አራት ብር ከሃምሳ ሁለት ሳንቲም) ከወለድና ከላልች ወጪዎች ጋር እንዱከፍለ ይወሰንለት ዘንድ በተጠሪ ላይ ክስ በመመስረቱ ፍርድ ቤቱ አመልካች የፍርክልዠር ሥልጣኑን ሳይጨርስ በፍ/ቤት ክስ መመስረትን ስነሥርዓቱ አይፈቅድም በማለት ክሱን ለጊዜው የዘጋው መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች የፍርድ ሂደትን ማለፍ ሳያስፈልግ በሐራጅ የመሸጥ ሕጋዊ መብት ያለው መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 98/90 እና 216/92 ድንጋጌዎች መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በእነዚህ ህጎች በተሰጠው ሥልጣን ባንኩ ሲጠቀም ሉከተለው የሚገባው ሥነ-ሥርዓትም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 394 እስከ 449 ድረስ ያለትን ድንጋጌዎች ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 6 ድንጋጌ በግልፅ አስቀምጧል። እነዚህ ድንጋጌዎች የሚገኙት ደግሞ ስለፍርድ አፈፃፀም በሚገዛው የተጠቃሽ ሥነሥርዓት ሰባተኛ መፅሐፍ ስር ነው። ይህም የሚያሳየው የባንኩ ስራ ተበዲሪውን በመወከል የመያዣ ንብረቱን ሽጦ ለብድሩ ዕዲ እንዱውል ማድረግ ሲሆን ይሕም በይዘቱ የአፈፃፀም አካል ልባል የሚችል ነው። ከላይ የተጠቀሱት አዋጆች ባንኮች በራሳቸው ምርጫ በብድር የሰጡትን ገንዘብ የመሰብሰብ ተግባር እንዱከተለ አስገዲጅ መንገድ ስለመሆኑ የሚያሳይ ድንጋጌ አልያዙም። በልላ አገላለፅ ባንኮች ብድራቸውን ለማስመለስ በፍርድ ቤት በኩል ክስ ሲመሰርቱ ጉዲዩ በአዋጅ መሰረት ሉፈፀም ይገባል ልባል የማይችል ሲሆን መያዣ ንብረቶች ላይ ከአዋጁ ባገኙት መብት መሰረት እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመራቸው በሁለት መንገድ ክስ ቀርቧል ልባል የሚችል አይደለም።
ባንኮች በራሳቸው ምርጫ በብድር የሰጡትን ገንዘብ የመሰብሰብ ተግባር ሳይፈፅሙ በፍርድ ቤት ክስ ቢመሰርቱ ወይም በመረጡት መንገድ የመሄድ ሁኔታ አዋጁ ከወጣበት ዓላማ ጋር ሉፃረር ይችላል ተብል የሚታሰብ አይደለም። የአዋጁ አይነተኛ ዓላማ ባንኮች በተቻለ ፍጥነት በብድር የሰጡትን ገንዘብ በመሰብሰብ እንደገና መዋዕለ ንዋዩን ለኢንቨስትመንት ስራ እንዱውል በማድረግ በአገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና መጫወት ነው።
ስለሆነም ባንኮች በአዋጁ የተሰጣቸውን ሥልጣን በመተው ወይም እንቅስቃሴውን ጀምረው እያለም ቢሆን በፍርድ ቤት ክስ ቢመሰርቱ ተቀባይነት የለውም ወይም በቅድሚያ የተጀመረው እንቅስቃሴ ሉያልቅ ይገባል የሚባልበት ሕጋዊ መሰረት ያለው ምክንያት የለም። የስር ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244(2/ሐ) ድንጋጌም በአንድ ፍርድ ቤት የቀረበ ክስ በልላ ፍርድ ቤት እየታየ ከሆነ የሚከለክል እንጂ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ላለው አይነት ክርክር አግባብነት ያለው አይደለም።
አመልካች በአዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት እንቀስቃሴን ቀጥል በፍርድ ቤት ክስ ከመሰረተ በኋላ መያዣ ንብረቶችን ለመሸጥ እንቅቃሴ እያደረገ በፍርድ ቤት ክስ ቢመሰርት ወይም የመያዣ ንብረቶችን ክሱ እየቀጠለ ባለበት ሁኔታ መሸጡ ቢረጋገጥ ሉኖረው የሚችለው ውጤት የሚቀር እዲ መኖሩንና አለመኖሩን አረጋግጦ ክስ እንዱቀጥል ከማድረግ ወጪ ክሱን ለማቋረጥ የሚያስችል አይደለም። ንብረቶቹ የሚሸጡበት ዋጋ በአፈጻጸም ጊዜ የሂሳብ መተሳሰብ ተሰርቶበት ሉቀናነስ የሚችል ከመሆኑ ውጪ የአመልካችን በፍ/ቤት ክስ ከመቀጠል የሚያግደው አይደለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ባንክ ሉከተለው የሚገባው መንገድ አንድ ብቻ ነው ተብል ባልተደነገገበት ሁኔታ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244(2/ሐ) ድንጋጌን ያለቦታው በመጥቀስ በአመልካች ባንክ የተፈፀመ ድርጊት የተጠሪን የሂሳብ እንተሳሰብ ጥያቄ በአፈፃፀም ከማንሳት የማይከለክልባቸው ሆኖ እያለ የአመልካችን ክስ ማቋረጡ ሕጋዊ ባለመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በልላ በኩል ተጠሪ ከአመልካች ባንክ የወሰደት የገንዘብ ብድር አለመከፈለን ሳይክደ አጥብቀው የሚከራከሩት በመያዣ የተያዙ ንብረቶች በሒራጅ መሸጣቸውን በመግለፅ በመሆኑና ይህ ደግሞ በኃላፉነታቸው መጠን ካልሆነ በልላው ላይ የተለየ ውጤት ሉያስከትል የማይችል በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዲዩ ላይ ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን እንደገና መመለሱ የፍትሃ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረታዊ ዓላማ ክርክሮች በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጪ እልባት እንዱያገኙ ማስቻል ከመሆኑ አንፃር ሲታይ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም። ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊያን ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 02 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ሚያዝያ 05 ቀን 1987 ዓ.ም በተፈረመ የብድር ውል ከአመልካች ለወሰደት ገንዘብ የከፈለት ማንኛውም ገንዘብ እና የመያዣ ንብረቶች ሽያጭ ዋጋን በአፈፃፀም ወቅት ከአመልካች ጋር የመተሳሰብ መብታቸው የተጠበቀ ሆኖ በስር ፍርድ ቤት ክስ የቀረበበትን ብር 396,904.52(ሦስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አራት ብር ከሃምሳ ሁለት ሳንቲም) ወለድን በስምምነታቸው መሰረት ገንዘቡ ተከፍል እስከሚያልቅ፣ እንዱሁም የመድን አረቦኑን ለአመልካች እንዱከፍለ በማለት ወስነናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.