No summary available.
ጥቅምት 17 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - አቶ ናሆም ሸዋንግዛው ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ወ/ሮ ሀና አባይ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት የትሐታብሓር ይግባኝ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ሰኔ 9 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
የክርክሩ መነሻ የአሁን ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርቦ አቶ ሐጎስ ተድላ ከንፊስ ስልክ ቅርንጫፍ ለወሰደት ብር 75‚000 (ሰባ አምስት ሺ ብር) ንብረትነቱ የተበዲሪው የአቶ ሀሰን አብደላ የሆነ የሰላዲ ቁጥሩ 3-16015 እና የተሳቢው መለያ ቁጥር 3-03383 የሆነ መኪና በመያዣነት ይዘናል። ተጠሪ እና ተበዲሪው አቶ ሐጎስ ተድላ መያዣው የመድን ዋስትና እንደገባለት በተስማሙት መሰረት በመያዣነት የተያዘው መኪና በተከሳሽ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምስራቅ አብይ ቅርንጫፍ ብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) ተገምቶ ኢንሹራንስ መድን ተገብቶ የአረቦን ክፍያ ስንከፍል ቆይተናል። የመድን ውለ እየታደሰ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ህዲር 28 ቀን 1988 ዓ.ም መኪናው በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ከጥቅም ውጭ ስለሆነና ተከሳሽ (አመልካች) ከመያዣው ግምት ብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) እንዱከፍል ብንጠይቀው ፈቃደኛ ስላልሆነ እና ተበዲሪው ብድሩን ያልከፈለ በመሆኑ በመያዣነት የያዝነውን የመድን ዋስትና የገባለትን መኪና ዋጋ እንዱከፍለ ይወሰንልን በማለት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ከተጠሪ ጋር ቀጥተኛ የሆነ የውል ግንኙነት ስለላለኝ ክስ የማቅረብ ችልታ የለውም። መኪናው የተገለበጠው አሽከርካሪው መሪ እንቢ ብልኝ ነው በማለት ያቀረቡት መግለጫ በቴክኒክ ማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ ሀላፉነት የለብንም።
በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዲት በባለሙያ አልተረጋገጠም። መክፈልም ካለብን ሰባ አምስት ሺ ብር ነው የሚለ መከራከሪያዎችን አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት በአመልካች በኩል የቀረቡትን መከራከሪያዎች ውደቅ በማድረግ አመልካች ለተጠሪ መያዣው በአደጋ በመውደሙ ምክንያት የደረሰበትን ጠቅላላ ጉዲት ብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀሣሳ ሺ ብር) ከህዲር 8 ቀን 1988 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ይክፈል በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቦ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የጉዲቱ መጠን አልተረጋገጠም በሚልና በላልች ነጥቦች የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ በመሻር ጉዲዩ እንደገና ታይቶ እንዱወሰን ጭብጦችን በመለየት ለሥር ፍርድ ቤት መልሷል።
ተጠሪ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት አቅርቦ ችልቱ የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል።
አመልካች ይህንን ውሣኔ በመቃወም ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በተበዲሪው ብድሩ ያልተከፈለው መሆኑን ሣያረጋግጥ ክስ እንዱያቀርብና እንዱከራከር መደረጉ መሰረታዊ የሆኑ የኢንሹራንስ መርሆችና ዓላማ የሚቃረን ነው። ተጠሪ ተበዲሪው ከተበደረው ውስጥ የከፈለውን ያልከፈለውን ለይቶ አላቀረበም ተጠሪ ያበደረው 75‚000 (ሰባ አምስት ሺ ብር) ሆኖ እያለ ተገቢ ያልሆነ ክፍያ ጠይቋል ተጠሪ ብድሩ ባለመከፈለ የነበረውን ወለድ እና ትርፍ መጠየቁ ተገቢ አይደለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት አግባብነት ያላቸውን የፍትሐብሕር ህግ እና የንግድ ህግ በመተላለፍ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት በፅሐፍ ያመለከተ ሲሆን ይህንኑ የሚያጠናክር የቃል ክርክር አቅርቧል ተጠሪ በበኩለ ተበዲሪው እዲውን በወቅቱ ባለመክፈለ ምክንያት ወለደና ላልች በብድሩ አለመከፈል ምክንያት መከፈል ያለበት ገንዘብ ሲታሰብ ብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) ጉዲት የደረሰብን መሆኑን አስረድተናል። ተጠሪ የመድን ሽፊን ለማግኘት ከአመልካች ጋር የመድን ውል እንደገባ ያደረገውና የአረቦን ክፍያ ሲከፍል የኖረው ለተበዲሪው ለሰጠው ብር 75‚000 (ሰባ አምስት ሺ ብር) ሣይሆን ይህ ብድር በወቅቱ ባይከፈል ለብድሩ መያዣ ለሆነውና ዋጋው ብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) ለሆነው በመያዣነት ለያዝነው መኪና ነው። የጠየቅነው ገንዘብ በመድን ውለ ከተሰጠው ሽፊን የበለጠ አይደለም ስለዚህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል።
No topics extracted.
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለው ክርክር ተጠሪ ላበደረው ብድር በመያዣነት የያዘው መኪና ለሚደርሰው ጉዲት እስከ ብር 350‚000 አመልካች የመድን ሽፊን ላሰጥ፣ መኪናውን ያስያዘው ሰው ወይም ተጠሪ በየጊዜው መክፈል የሚገባውን አረቦን ሲከፍለ ነው። ተጠሪ የመድን ሽፊን ለተገባለት ንብረት መከፈል የሚገባውን አረቦን ያለ ማቋረጥ የከፈለ መሆኑንና በዚህ ሑደት መኪናው አደጋ የደረሰበት መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።
አመልካች መኪናው ሙለ በሙለ ከጥቅም ውጭ አልሆነም የሚል መከራከሪያ ያቀረበ ቢሆንም ተጠሪ ካቀረበው ማስረጃ የተሻለ ማስረጃ በማቅረብ ክርክሩን ያላስረዲ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ስለዚህ በዚህ በኩል አመልካች የሚያቀርበው ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ተጠሪ የመኪናው ባለቤት ለሆኑት ተበዲሪ ብር 75‚000 (ሰባ አምስት ሺ ብር) ሲያበድሩ ለብድሩ አከፊፈል ዋስትና ይሆነው ዘንድ ግምቱ 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) የሆነ መኪና በመያዣነት ይዟል። አመልካች ላበደረው ብድር አከፊፈል ዋስትና እንዱሆነው በመያዣነት በያዘው ንብረት ላይ ያለው መብት ብድሩ ባለመከፈለ ቀሪ የሆነ ዋናው ገንዘብ፣ ይህ ብድር በብድር ውለ መሰረት ባለመከፈለ የሚወልደው ወለድ፣ የወለድ ወለድ መቀጫና ላልች ወጭዎችን ሁለ ባለመከፈላቸው መያዣውን ሽጦ ገቢ የማድረግ መብቱን የሚያጠቃልል መሆኑና ጠቅላላ ጣሪያው በመያዣ ውለ የተገለፀው የገንዘብ መጠን እንደሆነ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2858 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል።
ተጠሪ ተበዲሪው ብድሩን ባለመክፈለ ምክንያት ብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) ዋናው ብድር ወለድና ላልች ክፍያዎች ከተበዲሪው እንደሚፈልግ በሥር ፍርድ ቤት አስረድቷል። ተጠሪ ለዚህ ገንዘብ አከፊፈል ይረዲው ዘንድ በመያዣነት የያዘው ንብረት የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ በመያዣነት የያዘው ንብረት በባህሪው ተንቀሣቃሽና ለአደጋ ተጋላጭ መሆኑን በመረዲት በመያዣነት የያዘውን ንብረት በብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) የመድን ሽፊን እንዱገባለት አድርጓል። ይህንንም ያደረገው ተጠሪ ያበደረውን ገንዘብ፣ ወለድና ላልች ክፍያዎች የማስመለስ እድለን ለማስፊት እና እርግጠኛ ለመሆን ነው። ስለሆነም ተጠሪ አመልካች እንድከፍለው የጠየቀውና የሥር ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ለተጠሪ ብር 350‚000 (ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ብር) ከህዲር 8 ቀን 1988 ዓ.ም ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍል የወሰኑት የንግድ ህግ ቁጥር 678 ድንጋጌ መሰረት በማድረግና የኢንሹራንስ ውለን መሰረት በማድረግ በመሆኑ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላላገኘነው በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት አፅንተነዋል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ችልትና በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።