No summary available.
ሀምላ 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ፍፁም በርታ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው። የክርክሩ መነሻ አባቴ አቶ በርታ ሰይድ ሀምላ 24 ቀን 1995 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሟች አባቴ በውልና ማስረጃ መጋቢት 5 ቀን 1985 ዓ.ም ኑዛዜ ያደረጉ ስለሆነ ኑዛዜው ፀድቆ የኑዛዜ ወራሽነቴ ተረጋግጦ ማስረጃ ይሰጠኝ በማለት ለአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረበው ማመልከቻ ነው። ተጠሪዎች በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት አመልክተው በክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ከተፈቀደላቸው በኋላ ተጠሪዎች በሸሪዓ ፍርድ ቤት የሟች ወራሽ መሆናቸውን ለማረጋገጥ አቤቱታ አቅርበው አመልካቹ በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እየተከራከረ ስለሆነ ጉዲዩ በአንድ ጊዜ በሁለት ፍርድ ቤቶች መታየት የለበትም የሚል መቃወሚያና በአማራጭ ላልች መከራከሪያዎችን አቅርበዋል። አመልካችና ተጠሪዎች በዚህ መዝገብ በተያዘው ጉዲይ ላይ በመከራከር እያለ የአሁን ተጠሪዎች አመልካች የአሁን አመልካች ጣልቃገብ ተከራካሪ የሆኑበት በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተያዘው መዝገብ መስከረም 25 ቀን 1997 ዓ.ም ውሣኔ አግኝቷል።
የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተወሰነ መሆኑን በመግለፅና አመልካች ያቀረበው አቤቱታ ላይ ማከራከር የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 8(1)”ን” የሚጥስ መሆኑን በመግለፅ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎበታል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙን አልተቀበለውም። አመልካች ለአዱስ አበባ አስተዲደር የሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ የሰበር አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች ለዚህ ችልት ግንቦት 6 ቀን 2001 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ እኔ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ተከራካሪ ሆኜ የገባሁት ወላጅ አባቴ በፍትሐብሕር ህጉ መሰረት ያደረገው ኑዛዜ ስላለ ውርሱ መታየት የሚገባው በመደበኛው ፍርድ ቤትና በፍትሐብሕር ህጉ መሰረት መሆን አለበት የሚለውን መቃወሚያ ለማቅረብ ነው። እኔ በአዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 3 መሰረት መጥሪያ ተልኮልኝ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፈቃደኛ መሆኔን በመግለፅ ፍርም ሞልቼ ያላቀረብኩ በመሆኑ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ሙለ ፈቃድን አልሰጠሁትም። መቃወሚያ ለማቅረብ ጣልቃ መግባቴ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፈቃድ ሰጥቷል ተብል የተሰጠው የህግ ትርጉም አባቴን የመውረስ መብቴን የሚያሣጣና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው እኛ የአንደኛ ተጠሪ የሟች ሚስትና ወራሽ ከሁለተኛ ተራ ቁጥር እስከ አራተኛው ተራ ቁጥር ስማችን የተገለፀው ተጠሪዎች የሟች ልጆችና ወራሾች መሆናችንን በሸሪዓ ፍርድ ቤት በሸሪዓ ህግ መሰረት ለማረጋገጥ ባቀረብነው ማመልከቻ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ እያለ አመልካች ነሐሴ 27 ቀን 1995 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት አመልክቷል። አመልካች ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ከተፈቀደለት በኋላ አንደኛ ተጠሪ የሟች ሚስት አይደለችም ሟች በህይወት በነበሩበት ጊዜ ያደረጉት ኑዛዜ ስላለ ኑዛዜው ይፅደቅልኝ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ስለጉዲዩ በሽማግላዎች እንዱጣራ በማድረግ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎበታል። አመልካች በሙለ ፈቃደ በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ ኑዛዜው እንዱፀድቅለትና አንደኛ ተጠሪ የሟች ሚስት አይደለም ተብል እንዱወሰንለት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አመልክቶ ውድቅ ከተደረገበት በኋላ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ስምምነት አልሰጠሁም በማለት ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም በማለት በፅሐፍ መልስ ሰጥተዋል። አመልካች ሟች አባቴ ኑዛዜ ያደረጉ በመሆኑ በሸሪዓ ህግ መሰረት የሟች ውርስ መታየት የለበትም የሚል መቃወሚያ ለማቅረብ በክርክሩ ጣልቃ መግባቴ በሸሪዓ ህግ መሰረት በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፈቃድ እንደሰጠሁ ሉቆጠር አይገባውም። ከዚህ በተጨማሪ ኑዛዜው በሸሪዓ ፍርድ ቤት ታይቶ ውሣኔ አልተሰጠበትም የሚል ይዘት ያለው የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ በፅሐፍ ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች በሸሪዓ ህግ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፈቃደን ሰጥቷል ወይስ አልሰጠም? የሸሪዓ ፍርድ ቤት ሟች አድርገውታል የተባለውን ኑዛዜ አይቶ ውሣኔ ሰጥቶበታል ወይስ አልሰጠበትም? የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ማመልከቻ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለት ጭብጦች መታየት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
አመልካች በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 41 መሰረት ተጠሪዎችን ወራሽነት ጥያቄና ክርክር ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር ሲጠይቅ በክርክሩ ሑደት በአዋጅ ቁጥር 188/1992 አንቀፅ 6(1) መሰረት የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ለውሣኔአቸው መሰረት ሉያደርጉት በሚገባው በሸሪዓ ህግ መሰረት ለመዲኘት ፍላጎትና ፈቃድ ያለው መሆኑን የሚያመለክት ነው። ምክንያቱም የክርክሩን የአመራር ሥርዓት ካልሆነ በስተቀር የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች በሥረ-ነገር ሥልጣናቸው ሥር የሆኑ ጉዲዮች የሚቀርብላቸውን አቤቱታና ክርክር የሚወስኑት የሸሪዓ ህግን መሰረት በማድረግ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 188/92 በአንቀፅ 6(1) በግልፅ የተደነገገ በመሆኑ አንድ ሰው ለሸሪዓ ፍርድ ቤት ክስ ወይም አቤቱታ ሲያቀርብ ሥነ ሥርዓታዊ ከሆነው ጭብጥና ጥያቄ ውጭ የሆኑት ጉዲዮች በሸሪዓ ህግ ለመዲኘትና ፈቃድ የሰጠ መሆኑን የሚያሣይ በመሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በሸሪዓ ህግ መሰረት በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፈቃደን የሰጠ መሆኑን ወይም አለመሆኑን አመልካች በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ከፈቀደለት በኋላ ያቀረበውን ክርክር ይዘትና የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዲኝነት በማየት እንዱወሰንለት ያቀረበውን ጭብጥ በመመርመር ውሣኔ መስጠት ግድ ይላል።
አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ከፈቀደለት በኋላ ሁለት መሰረታዊ ጭብጦች ፍርድ ቤቱ አይቶ ውሣኔ እንዱሰጥለት ጠይቋል። የመጀመሪያው አንደኛ ተጠሪ የሟች አባቴ አቶ በርታ ሰይድ ሚስት አይደለም። ስለሆነም አንደኛ ተጠሪ የሟች ሚስትና ወራሽ ነኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ይደረግልኝ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ሟች አባቴ በህይወት እያለ ያደረገው የኑዛዜ ሰነድ ስላለ የሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ያፅድቅልኝ የሚል መሆኑን በመዝገብ ቁጥር 7/96 የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም አመልካች የሸሪዓ ፍርድ ቤት ጣልቃገብ ተከራካሪ እንዱሆን የጠየቅሁት ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በሸሪዓ ህግ መሰረት ጉዲዩን እንዲይወስን ተቃውሞ ለማቅረብ ነው በማለት በሰበር አቤቱታው ያቀረበው መከራከሪያ ተገቢነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች ለፋዳራል የሸሪዓ ፍርድ ቤት በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ ክርክሩን እንዱያሰማ ያቀረበው ማመልከቻና አመልካች በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ከተፈቀደለት በኋላ የሸሪዓ ፍርድ ቤቱ የጠየቀው ዲኝነትና ያቀረበው ክርክር በአንድነት ሲታዩ አመልካች በሸሪዓ ህግ መሰረት በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ሙለ ፈቃድን የሰጠ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው።
አመልካች በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፈቃደኛ መሆኔን በአዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀፅ 5(1) እና ከአዋጁ ጋር በተያያዘው አባሪ(ፍርም) በመሙላት አልሰጠሁም በማለት ክርክር አቅርቧል። ሆኖም ከአዋጁ ጋር የተያያዘውን ፍርም በመሙላት በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፈቃደኛ መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን ከቀጠሮ ቀን በፉት ለሬጅስትራር እንዱገልፅ የሚገደደት በጉዲዩ ተከሳሽ ወይም በተጠሪነት ቀርበው መልስ የመስጠት ግዳታ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀፅ 5(1) በግልፅ ተደንግጓል። አስፈላጊ የሆነ ሥነ ሥርዓቶችና ፍርማሉቲዎች በማሟላት ለሸሪዓ ፍርድ ቤት ክስ ወይም አቤቱታ ያቀረበ ከሳሽ ወይም አቤቱታ አቅራቢ ክሱን ወይም አቤቱታውን ለሸሪዓ ፍርድ ቤት አንዱታይ ፈቃደኛ መሆኑን ፍርም በመሙላት መግለፅ አያስፈልገውም። ስለሆነም አመልካች የሸሪዓ ፍርድ ቤት አቤቱታውን አይቶና በአቤቱታው ዲኝነት የጠየቀባቸውን ጉዲዮች አጣርቶ እንዱወሰንለት ግልፅ ጥያቄ አቅርቦና ተከራክሮ ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘትና ጉዲዩ በሸሪዓ ህግ መሰረት እንዱወሰን ፈቃደን አልሰጠሁም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የአዋጁን አንቀፅ 5(1) ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ሟች አቶ በርታ ሰይድ ያደረጉት ኑዛዜ የሸሪዓ ህግ የሚጠይቀውን መሥፈርት ያሟላና ህጋዊ ውጤት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ሲወስን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አግባብነት ያላቸውን የሸሪዓ ህግ ድንጋጌዎች አልጠቀሰም ወይም የሸሪዓ ህግ ድንጋጌ ሲተረጉም ሥህተት ሰርቷል የሚል ሀሳብ ካላቸው አመልካች ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ የማረም ሥልጣን ላለው የፋዳራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ነበረባቸው። አመልካች ይህንን በማድረግ ፊንታ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በጭብጥነት በመያዝ ግልፅ ውሣኔ የሰጠበት የሟች ኑዛዜ እንደተጠቃሚ መሆናቸውን እንዱረጋገጥላቸው ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የሰበር ችልት አመልካች ሟች አባቴ ያደረጉት ኑዛዜ ተጠቃሚ መሆኔ ተረጋግጦ ማስረጃ ይሰጠኝ በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢና የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት አፅንተነዋል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት፣ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማ ነክ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
ራ/ታ
ሐምል 07 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ የኮንስትራክሽን ስራዎችና ቡና ቴክኖልጂ ማስፊፉያ ድርጅት መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር - ወኪል አህመድ በዲኔ ቀረቡተጠሪ፣ የኮንሽትራክሽን ስራዎችና ቡና ቴክኖልጂ ማስፊፉያ ድርጅት - ጠበቃ መንበረስላሴ በዛብህ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት ያደረገ የቦነስና የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚህ አካል ክሱን ያቀረበው የአሁኑ አመልካች ሲሆን ተጠሪ ከሣሽ ነበር የአመልካች የክሱ ይዘት ተጠሪ ድርጅት በ1999 ዓ.ም የበጀት ዓመት ተጠሪ ካገኘው ትርፍ በሕብረት ስምምነቱ አንቀጽ 24/1/ መሰረት የደመወዝ ጭማሪና የቦነስ ክፍያ ተጠሪ እንዱከፍል ይወሰንልን የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበው ክርክር የደመወዝና የቦነስ ጭማሪ ጉዲይ ለማየት ፍርድ ቤቱም ሆነ ቋሚ ቦርደ ሥልጣን የለውም የሚል ነው። ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በአዋጁ አንቀጽ 138 መሰረት ስልጣን የላለው መሆኑን በመግለጽ ክሱን ዘግቶታል። ይህ ብይን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ቀርቦም ፀድቋል። ከዚህ በፉትም ጉዲዩ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ቀርቦ ቦርድም የአዋጁን አንቀጽ 147፣ 142/1/ሀ/2/3// እና 136/2/ ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ቦርደ ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለውም በማለት ክሱን ዘግቶታል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራቀኙ ከተከራከሩ በኃላ የቦርደ ውሣኔ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ በታየው ጉዲይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ነው።
የአመልካች ነገረፈጅ መስከረም 07 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡- ጥያቄው የጋራ ጥቅምን የሚነካ የወል የስራ ክርክር ነው ተብል ተወስኖ ሆኖ እያለ ጥያቄው በፍርድ ቤቱም ሆነ በቦርደ የሚታይ አይደለም ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ጉዲዩ በቋሚ ቦርድ ቀርቦ ላታይ በሚችል አኳኋን ሕጉ ሉተረጎም ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጥያቄ ለማየት እንዱቻል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ በጠበቃው አማካኝነት ህዲር 02 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል። የመልሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ጉዲዩ ከአዋጅ ቁጥር 136/2/ እና 147/1 ሀ/፣ 147/2/ አንፃር ሲታይ በሁለቱም አካላት የሚታይ ባለመሆኑ አመልካች ያለው መብት በአዋጁ አንቀጽ 157 መሰረት መብቱን ማስከበር ነው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአመልካች ማህበር የዲኝነት ጥያቄ መሰረት ያደረገው ከተጠሪ ጋር ያለውን የሕብረት ስምምነት መሆኑን ጥያቄውም በ2000 ዓ.ም የበጀት ዓመት ተጠሪ ድርጅት ከብር 78,000,000 (ሰባ ስምንት ሚሉዮን) በላይ ማትረፈን በግልፅ በማረጋገጡ በህብረት ስምምነቱ መሰረት ለሁለም ሰራተኛ የደመወዝ ጭማሪና ቦነስ የመስጠት ግዳታ ያለበት መሆኑን አመልካች ጠቅሶ የሚከራከር መሆኑና ተጠሪ እንደዚህ አይነት ጥያቄ በቋሚ ቦርድ ላታይ አይገባም በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 138፣142 እና 147 ድንጋጌዎች መሰረት የስራ ክርክር ጉዲዩች የሚታዩበትን ስርዓት ሲዘረጋ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባው የወልና የግል የስራ ክርክሮች በሚል ነው።
የስራተኞችን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም አወሳሰን በሚመለከት የሚነሳውን የወል የስራ ክርክር በቋሚው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ላታይ እንደማይችል በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 147/1/1ሀ/ በግልፅ ተመልክቷል። በአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ የደመወዝ ጭማሪና የቦነስ ጥያቄን ማስተናገድ የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 142/3/ በተጠቀሰው መሰረት በአዋጅ አንቀጽ 136/2/ ስር እጅግ አስፈላጊ የሕዝብ አገልግልት ሰጪ ድርጅቶች ተብለው የተጠቀሱትን ድርጅቶች የሚመለከት ሲሆን ብቻ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ሕግ አውጪው ድርጅቶችን ሙለ በሙለ ለይቶ ዘርዝሮ አስቀምጧል። ተጠሪ ደግሞ ከእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የሚካተት አይደለም። በአዋጅ አንቀጽ 136 ስር ከተዘረዘሩት እጅግ አስፈላጊ የሆነ የሕዝብ ግልጋልት ሰጭ ድርጅቶች ውጪ ያለትን ድርጅቶች ጋር ሰራተኛው የሚያነሳውን የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጉዲይ ቋሚ ቦርደ ጉዲዩን ለማየት ግልፅ የሆነ የሕግ አውጪ ክልከላ ከላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ሲሆን የእነዚህ ድርጅቶ ጉዲይ በየትኛው አካል ላታይ አንደሚገባ ሕጉ ያስቀመጠው ስርዓት መኖሩንና አስፈላጊነቱ ምን እንደነበር መመለከቱ የግድ ይላል።
ጉዲዩ የወል የስራ ክርክር መሆኑ ግልፅ ነው። ሆኖም የወል የስራ ክርክር ሆነውም በቦርደ በተለየ ሁኔታ የማይታዩት ጉዲዩች በሕጉ ተለይተው ተቀምጠዋል ወይስ አልተቀመጡም? የሚለው ጥያቄ መነሳት ያለበት ነው።
በዚህ ችልት እምነት ከላይ እንደተጠቀሰው ሕግ አውጪው ክርክሩ የወል የስራ ክርክር ቢሆንም በቋሚ ቦርደ ላታይ የማይገባበትን ሥርዓት ዘርግቷል።
የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 141 እና 142 ሲታዩ ይህንኑ የሚመልሱ ናቸው። በዚህም መሰረት በአዋጅ አንቀጽ 136/2/ ድንጋጌ ስር ከተዘረዘሩት ድርጅቶች ውጪ ያለ ድርጅቶች የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጉዲይ የአስማሚ ተግባርና ኃላፉነት ሆኖ ላታይ የሚገባው በአዋጁ ምዕራፍ ሶስት በፋዳራለ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስቴር በሚመድበው አስማሚ ነው። በአዋጅ አንቀጽ 142/1ሀ/ ከተጠቀሰው የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጉዲዩች ብቻ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ማቅረብ ይቻላል ይህንኑም ከተጠቀሰው አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ሶስት ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበው ነው። ጉዲዩ የሚታየው በአዋጁ ምዕራፍ ሶስት በሚቋቋም አስማሚ እንጂ በአዋጅ ምዕራፍ አራት ስር በሚቋቋም ቦርድ /ቋሚም ይሁን ጊዜያዊ/ አይደለም ይህ ስለመሆኑም አንዲንድ በዋቢነት የሚጠቀሱት ነገሮች አለ። ከእነዚህ መካከል አዋጅ ቁጥር 377/96 ማሻሻያ ላይ የቀረበው ውይይት አንደ ነው። ከአዋጁ ማሻሻያ ሐሳቦች አንደ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጉዲይ በአስማሚ ላታይ አይገባውም የሚል እንደነበር ይታወቃል ማሻሻያው ተቀባይነት ያለማግኘቱ የሚታወቅ ነው። የማሻሻያው ጥያቄ ውድቅ የተደረገበት አብይ ምክንያትም የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጉዲይ ከአለው እጅግ አስፈላጊና ወሳኝነት ባህርይው የተነሳ በተደጋጋሚ ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪና ጥቅማጥቅም በፈለጉ ቁጥር በአሰሪዎቻቸው ላይ የሚያነሷቸው የማያባሩ ጥያቄዎች ስለሆኑ ሁለቱም ወገኖች በፈቃዲቸው በመረጧቸው አስማሚዎች የሚስማሙባቸው ወይም የሚኒስትሩ መ/ቤት በሚመድበው አስማሚ እንዱያልቅ በማስፈለጉ መሆኑ ይታወቃል። እነዚህ ጥያቄዎች ለወሳኝ ቦርድ ይቅረቡ ቢባል ሰራተኞችና አሰሪዎች ጊዜያቸውን ከመስማማት ይልቅ በመካሰስ ያላግባብ እንዱያጠፈና በድርጅቶች ምርትና ምርታማነት ላይም አለታዊ ተጽእኖ ሉያሳድሩ ይችላለ ተብል ይታመናል። በአንፃሩ ደግሞ ለሕዝብ አገልግልት የሚሰጡ ድርጅቶች ግን ስምምነት ላይ ባይደርሱ ሰራተኞች የሚወስደት እርምጃ በአገልግልት ላይ ችግር ስለሚያስከትል የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጉዲይ ከመንግስት ፖሉሲ /Public polic/ አንጻር የእነዚህ ድርጅቶች ጉዲይ ብቻ በቦርድ እንዱታይ ሕግ አውጪው ያደረገው ሉፈጠር ከሚችለው ችግር አንጻር መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ሀተታ ዘምክንየት ያሳያል። የአዋጅ አንቀጽ 147/1/ ድንጋጌ ሲታይ ሥልጣንን በተመለከተ ቋሚው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ደመወዝና ላልች ጥቅማ ጥቅሞችን ከሚመለከቱት የስራ ክርክር ጉዲዩች ውጪ በአዋጁ በአንቀጽ 142 ንዐስ አንቀጽ አንድ ስር የተመለከቱትን ጉዲዮች ማየትና ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን እንዲለው ተመልክተዋል። የደመወዝ ጭማሪ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄን የሚመለከቱት የስራ ክርክሮችን ቋሚ ቦርደ የማየትም ሆነ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን እንዲይኖረው ማድረግ ያስፈለገውም የደመወዝ ጭማሪ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጉዲይ የአሰሪውና የሰራተኛው ወገኖች በሚያደርጉት ድርድር አሉያም አንደ ወገን በልላው ላይ በሕጋዊ መንገድ ተጽእኖ በማሳደር ኢኪኖሚያዊ ጥቅሙን ለማግኘት ሉወሰድ በሚችል እርምጃ ሉፈታ የሚገባው እንጂ በቦርድ መወሰን የሚገባው ባለመሆኑ ስለመሆኑ የሕጉ ማሻሻያ ሀተታ ዘምክንያት ያሳያል። በአሰሪና ሰራተኛ ወገኖች መካከል በደመወዝና በጥቅማ ጥቅም ጉዲዩች ላይ አለመግባባትና ክርክር ሲፈጠር በዚህ አካል ጉዲዩ እንዱታይ ማድረግ የኢንደስትሪ እርምጃዎችን /ስራ ማቆም ሆነ ስራ መዝጋት/ መብቶች ይገደባል የሚል እሳቤ አለ። ስለሆነም የተከራካሪ ወገኖች ስምምነት በላለበት ሁኔታ ወይም ስራ ማቆምና ስራ መዝጋት መብቶች የላላቸው አካላት ካልሆነ በስተቀር ተከራካሪ ወገኖች በአስገዲጅ የግልግል ዲኝነት ስር እንዱወድቁ ማድረግ አግባብነት እንደላለው በመታመኑ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ እነዚህ ጉዲዩችን እንዲይመለከት መደረጉን ሐተታ ዘምክንያቱ ያሳያል። የስራ መቆምና የስራ መዝጋት መብቶች በአዋጅ አንቀጽ 157 እና ተከታዩቹ ጥበቃ ያገኙ ጉዲዩች ናቸው በዚህም መሰረት ሕግ አውጪው በአዋጅ አንቀጽ 147/2/ መሰረት እጅግ አስፈላጊ የሕዝብ አገልግልት ድርጅቶች የሚባለት ድርጅቶች ውስጥ ያለ የሰራተኞችም ሆኑ የአሰሪው ወገን በተጠቀሱት የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጉዲዩች ላይ የሚነሳን ክርክር በድርድር ለመፈታት ባይችለ እንደላልቹ የስራ ማቆም ወይም የስራ መዝጋት እርምጃ የመወስድ መብት የላላቸው በመሆኑ ሰራተኞቹም ሆነ አሰሪዎቹ ለጉዲዩ መፍትሄ እንዱያገኙ ክርክር በተፈጠረ ቁጥር በጊዜያዊነት ሉቋቋም ለሚችለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን መስጠቱ ታምኖት ግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል።
ስለሆነም የአዋጅ አንቀጽ 147/2/ ከአንቀጽ 142/3/ ጋር ተጣምሮ ሲነበብ ሉኖረው የሚገባው ትርጉም በአንቀጽ 136/2/ ስር እጅግ አስፈላጊ የሕዝብ አገልግልት ድርጅቶች ተብለው ከተዘረዘሩት ተቋማት ጋር ተያይዞ የሚቀርበውን የደመወዝ እና የላልች ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ ጋር ተያይዞ የሚነሳን የወል የስራ ክርክር ካልሆነ በስተቀር ከላልች ድርጅቶች የሚቀርበውን የደመወዝና የላልች ጥቅማ ጥቅሞችን የወል የስራ ክርክሮችን አይቶ የመወሰን የስረ ነገር የዲኝነት ሥልጣን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ አይደለም። በመሆኑም ምንም እንኳ የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ የወል የስራ ክርክር ነው ቢባልም ሕግ አውጪው በተለየ ሁኔታ በቋሚ ቦርደ ሉታዩ ይገባል ብል ከዘረዘራቸው ድርጅቶች ውጪ ያለ ድርጅቶችን በተመለከተ ቋሚ ቦርደ ሉመለከት አይገባም።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የሰጠውን ውሣኔ ለዚህ ጉዲይ ያለውን አግባብነት ስንመለከተውም በእነዚህ መዛግብት የተሰጠው ውሣኔ የወል የስራ ክርክር ብል ለመለየት የሚቻልባቸውን መንገድች ተንትኖ ውሣኔ የሰጠበት ሁኔታ እንጂ ያሁኑ አይነት ክርክር ቀርቦ በቦርደ ላታይ የሚገባው ነው በማለት ግልፅ የሕግ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ አይደለም። በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ጉዲዩ በቋሚ ቦርድ ላታይ የሚገባው አይደለም ከተባለ ላታይ የሚገባው በየትኛው አካል ነው የሚለው ጥያቄ መነሳቱ የግድ ነው። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሚገኘውም ከአዋጅ አንቀጽ 142/1ሀ/ ስር ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ስለደመወዝና ላልች ጥቅማ ጥቅሞች አወሳሰን በተመለከተ የሚቀርብ የወል የስራ ክርክር መታየት ያለበት ተከራካሪዎችን በማስማማት ለጉዲዩ እልባት በሚሰጠው በአዋጅ አንቀጽ 141/1/ መሰረት በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስቴር የሚሰየም አስማሚ ቦርድ ነው። አዋጅ ቁጥር 466/1997 አንቀጽ 2/2/ ሲታይም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ ቋሚ ቦርደም ሆነ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ በጉዲዩ ላይ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.