No summary available.
ሐምል 7 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ተከተል ዘካሪያስ - ወኪል አዲነች ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቹ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆኑን ገልፀው በሰበር ታይቶ እንዱታረምላቸው ስለጠየቁ ነው። በሥር ክርክሩ የታየው በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ንብረትነቱ የአንደኛ ተጠሪ የሆነ ተሽከርካሪ በሁለተኛ ተጠሪ ሹፋርነት ሲሽከረከር በሰበታ ሐዋሳ ወረዲ ቀበላ 01 ገጭቶ ጉዲት ያደረሰብኝ ስለሆነ ካሣ ይከፈለኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አንደኛ ተጠሪ አመልካች ክሱን በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 27 መሰረት ጉዲቱ በደረሰበት ቦታ የሥረ-ነገርና የክልል ግዛት ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ አለባቸው በማለት ተቃውመዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ጉዲዩን ለማየት የግዛት ክልል ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ያቅርብ በማለት ብይን ሰጥቷል። ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይኑ በይግባኝ መርምሮ አጽንቷል።
አመልካች በሁለት ክልል ኗሪዎች መካከል የሚነሣው ክርክር በፋዳራል ፍርድ ቤቶች መታየት እንዲለበት አዋጅ ቁጥር 25/88 ደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 10 እና በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 19 ሉወድቅ እንደሚችል ይደነግጋል። ስለዚህ ጉዲቱ የደረሰበት ቦታ ብቻ ነው መክሰስ ያለባቸው ተብል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ይታረምልኝ በማለት አመልክተዋል አንደኛ ተጠሪ በበኩላቸው የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 27 በጉዲት ካሣ ጊዜ የክልል ሥልጣን ያለው የትኛው የፍርድ ቤት እንደሆነ የሚደነግግ ልዩ ድንጋጌ ነው። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የሕግ ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል። ሁለተኛ ተጠሪ በላለበት ጉዲዩ ታይቷል።
በሥር የቀረበው ክርክርና በሰበር የቀረበው የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው አከራካሪው ጭብጥ ጉዲዩን የማየት የግዛት ክልል ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የትኛው ነው? የሚለው ነው። በመርህ ደረጃ በሰዎች ወይም በሚንቀሣቀስ ሐብት ላይ በደረሰ ጉዲት ካሣ ለማግኘት የሚቀርብ ክስ ጉዲቱ በደረሰበት ሥፍራ የሥረ-ነገረ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት መቅረብ እንዲለበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 27 ንኡስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። ይህም የሆነው የደረሰው የጉዲት እና ከጉዲቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዲዮች ላይ ጉዲቱ በደረሰበት አካባቢ በቀላለ ማስረጃ ለማግኘትና ማስረጃም ለማቅረብ የሚቻል በመሆኑ ነው። ሆኖም የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 27 ንኡስ አንቀጽ 1 ከላይ የተገለውን የሕጉን ዓላማ በአግባቡ ማሣካት የማይከለክል በሆነ ጊዜ በሰው ወይም በሚንቀሣቀስ ንብረት ላይ ለደረሰ ጉዲት ካሣ ለማግኘት የሚቀርብ ክስ ተከሳሽ በሚኖርበት ቦታ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚቻል ይደነግጋል።
በያዝነው ጉዲይ ጉዲቱ የደረሰው ሰበታ አካባቢ መሆኑ የተጠሪዎች የመኖሪያ ቦታ አዱስ አበባ ከተማ ውስጥ መሆኑና ምስክሮችና ላልች ማስረጃዎችን ለማቅረብ የሚያጋጥም የትራንስፖርትና ላልች ችግሮች ቀላል በመሆኑ አመልካች ክሱን ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ማቅረባቸው በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 27 ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት መንፈስና ዓላማ የሚቃረን ሆኖ አላገኘውም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ክሱን ተቀብልና አከራክሮ በፍሬ ጉዲይ ላይ ውሣኔ መስጠት ሲገባው የግዛት ክልል ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ስህተቱን ማረም ሲገባው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ብይን ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ብይንና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት የክልል ግዛት ሥልጣን አለው ብለናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪዎች በፍሬ ጉዲይ ላይ የሚያቀርቡትን ክርክርና ማስረጃ በመስማትና በመመርመር ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 341 ንኡስ አንቀጽ 1 መስረት መልሰንለታል ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.