No summary available.
ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ - ጠበቃ ረዲኢ ባራኺ ቀረበ ተጠሪዎች፡-
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ በመኪና ላይ ደረሰ የተባለውን ጉዲት መሰረት በማድረግ የቀረበ የካሣ ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ከሣሽ የነበረው አመልካች ነው። አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሰረተው የመድን ዋስትና የገባለት የደንበኛው መኪና በሁለተኛ ተጠሪ ሾፋርነት ሲሽከረከር በነበረው በአንደኛ ተጠሪዎች መኪና ተገጭቶ ጉዲት ስለደረሰበትና በዚህ ምክንያትም መኪናውን ለማስጠገን ወጪ በማድረጉ ይህንኑ እንዱተኩለት ነው።
በአንደኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ክርከሩ በላለበት የተሰማ ሲሆን፣ሁለተኛ ተጠሪ ግን ቀርቦ መልሱን እንደሰጠ ከመዝገቡ ተመልክተናል። ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም ከሁለቱ ወገኖች የቀረበለትን ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ሁለተኛ ተጠሪን ከክሱ ነፃ በማድረግ በአንደኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ብር 22,387.79(ሃያ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሰማኒያ ሰባት ብር ከሰባ ዘጠኝ ሣንቲም) ከነወለደ እንዱከፍለ ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች በውሳኔው ስላልተስማማ ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ፍ/ቤቱ ክሱ የቀረበው የግዛት ሥልጣን ለላለው ፍ/ቤት ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ይግባኙን ካለመቀበለም በላይ፣በሥር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔም ሽሮታአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች በሥር ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል። እኛም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። ተጠሪዎች በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ክርክሩ የተሰማው በላለበት ነው። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተደረገው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዛት ሥልጣንን መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን የተመለከተው ክሱን የሰማው ፍ/ቤት የግዛት የዲኝነት ሥልጣን ነበረው ወይስ አልነበረውም? የሚለው ጭብጥ አንፃር ነው። ለሰጠው ውሳኔ በዋቢነት የጠቀሰውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥሕ/ቁ. 27/1/ የተመለከተው ድንጋጌ ነው። ፍ/ቤቱ ይህን ድንጋጌ ለመጥቀስ የበቃው የክሱ መነሻ በሚንቀሳቀስ ንብረት የደረሰ ጉዲት ነው የሚል ምክንያት በመያዝ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
ይሁንና በተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው ድንጋጌ በቁጥር 27/1/ የተመለከተው ሳይሆን፣በቁጥር 24/3/ የተመለከተው እንደሆነ ነው በበኩላችን ለመገንዘብ የቻልነው። አመልካች በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ማህበር እንደመሆኑ ጉዲዩ በፋዳራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5(6) መሰረት በፋዳራል ፍ/ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን ሥር የሚወድቅ ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከተው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 24/3/ በግልጽ እንደተቀመጠው በኢንሹራንስ ውል አፈፃፀም ምክንያት ክርክር የተነሳ እንደሆነ ክሱ የኢንሹራንሱ ኩባንያ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ቦታ ባስቻለው ባለሥልጣን ፍ/ቤት ላቀርብ ይችላል።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች የኢንሹራንስ ኩባንያ ነው። ዋና መሥሪያ ቤቱ በዚህ በአዱስ አበባ ስለመሆኑም ይታወቃል። ክሱም የቀረበው በዚህ በአዱስ አበባ ላስቻለው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። በመሆኑም ፍ/ቤቱ በጉዲዩ ላይ የግዛት ክልል የዲኝነት ሥልጣን የለውም የሚባልበት የሕግ ምክንያት የለም። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ያየው የተሳሳተ ወይም ለጉዲዩ ተገቢነት የላለውን ሕግ መሰረት በማድረግ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 48183 ኀዲር 24 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተከፈተው የይግባኝ መዝገብ ጉዲዩን እንዱቀጥል በማድረግ እና ወደ ጉዲዩ ሥረ ነገር በመግባት ክርክሩን ሰምቶ ተገቢው ውሳኔ ይሰጥ ዘንድ ይመለስለት ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር አመልካች ወጪና ኪሣራውን ራሱ ይቻል።
No topics extracted.