No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የእርሻ መሣሪያዎችና የቴክ/አ/ማኀበር - ነ/ፈጅ ጌታቸው ደጉ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኢት/መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ጽጌረዲ ተሻገር - ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት እንዱመረመር የቀረበው የአ/አ/ ከተማ ማኀበራዊ ፍ/ቤት የግራ ቀኙ ክርክር የመዲኘት ሥልጣን በተመለከተ ነው። የጉዲዩ አጀማመር ሲታይ ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ ነበር። የተጠሪ የክስ ምክንያት ንብረትነቱ የአመልካች የሆነው መኪና የተጠሪን ደንበኛ መኪና ገጭቶ ጉዲት አድርሷል በሚል ተጠሪ የከፈለውን ብር አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት /4977.00/ አመልካች እንዱተካ እንዱወሰን የሚል ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ሥልጣን የተመለከተው በአ/አ ከተማ በቂርቆስ ክ/ከተማ የቀበላ ዐ4 ማኀበራዊ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ እንደ ክሱ አቀራረብ ወስኗል። በይግባኝ ሰሚ የአ/አ ከተማ ፍርድ ቤቶችም ይኸው ውሣኔ ፀንቷል።
ለዚህ ሰበር ከቀረበው አቤቱታ አንፃር ይህ ችልት የተመለከተው ማኀበራዊ ፍ/ቤቱ ይህንን ጉዲይ የመዲኘት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ሲሆን በዚህ ረገድ የተጠሪ ነ/ፈጅ ባቀረቡት የክርክር መልስ በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 5ዐ መሰረት ማኀበራዊ ፍርድ ቤት እስከ ብር አምስት ሺህ በሆነ የፍትሐብሕር ጉዲይ አከራክሮ የመወሰን ሥልጣን አለው ሲለ የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ እንዱፀና ጠይቀዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል ባጭሩ የተመለከትነው ሲሆን እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ሕጉን አገናዝበን መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዲት የተቻለው የተጠሪ ክስ ምክንያት ከውል ውጪ ኃላፉነት የሚመለከት ሲሆን ለመክስ መነሻው ግን ተጠሪ ከደንበኛው ጋር አለኝ በሚል የመድን ውል መነሻ በንግድ ሕጉ በተመለከተው የመዲረግ መብት የቀረበ ስለመሆኑ ነው። በዚህ መዝገብ የቀረቡት ተከራካሪ ወገኖች አንደኛው ብቻ ሳይሆን ሁለቱም በፋዳራል መንግሥት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ ስለመሆናቸውም መረዲት ችለናል። ስለሆነም በዚህ መነሻ የቀረበውን የዲኝነት ጥያቄ ተቀብል ለመወሰን የአ/አ ከተማ ማኀበራዊ ፍ/ቤት ሥልጣን አለውን? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት በተጠሪ የተጠቀሰውን አዋጅ ቁጥር 361/95 ከአዋጅ ቁጥር 25/88 ጋር በማገናዘብ መመርመር ያስፈልጋል። የአ/አ ከተማ ፍርድ ቤቶችና የመዲኘት ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት አደረጃጀት እና ሥልጣንና ኃላፉነት በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 361/95 ከአንቀጽ 39-5ዐ ድረስ ተደንግጎ እናገኛለን። ከእነዚህ ድንጋጌዎች አጠቃላይ ይዘት መገንዘብ የሚቻለው የዲኝነት አካላቱ ሥልጣን መሰረት ያደረገው የከተማው አስተዲደር ተቋማት ተግባር እና ኃላፉነት በሚመለከቱ አስተዲደራዊ ጉዲዮች እንዱሁም በከተማው ነዋሪዎች መካከል የሚነሱ የፍትሐብሕር እና የደንብ መተላለፍ ጉዲዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ኃላፉነት የተሰጠ ስለመሆኑ ነው። በተለይም ከተያዘው ጉዲይ ጋር አግባብነት ያለው የአዋጁ አንቀጽ 5ዐ/1/ የክርክር መጠኑ ከብር አምስት ሺህ ያልበለጡ የንብረት እና የገንዘብ ክርክሮችን ማኀበራዊ ፍ/ቤቶች እንዱዲኙ ሥልጣን ሲሰጥ ከፍ ሲል ከተመለከተው አጠቃላይ ዓላማ እና ወሰን ጋር መታየት ያለበት መሆኑን መገንዘብ አዲጋች አይደለም።
በዚህም እጅግ ቀላል የሆኑ ጉዲዮች እና ውስብስብ የሕግ ጥያቄ የማያስነሱ ክርክሮች በአጭር እና በቅርበት ለማኀበረሰቡ አገልግልት እንዱሰጡ ማስቻል ስለመሆኑ መረዲት የሚቻል ነው። የአዋጁ ግብ ይህ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ የገንዘብ መጠኑ ከብር አምስት ሺህ በታች በመሆኑ ብቻ በማናቸውም ጉዲዮች ላይ የመወሰን ሥልጣን ያሰጠዋል የሚለውን የተጠሪ ክርክር ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንፃር መመልከት ተገቢ ይሆናል። የአዋጅ ቁጥር 25/88 የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን የዲኝነት ሥልጣን ሲዘረዝር በዋነኛነት ታሳቢ ያደረገው የፋዳራል መንግሥት አወቃቀር እና የፋዳራል ሥርዓቱን የሥልጣን ክፍፍል መርህ በመጠበቅ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የሥልጣን ወሰን በግልጽ በልላ ሕግ እስካልተሻረ ድረስ በዝምታ ወይም ኋላ በወጣ ሕግ ተተክቷል ልባል አይችልም። ስለሆነም በተጠሪ በኩል የቀረበው ክርክር ማለትም በአዋጅ ቁጥር 25/88 የተደነገገው ቢኖርም አዋጅ ቁጥር 361/95 ኋላ የወጣ በመሆኑ ተፈፃሚነት አለው የሚለው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። ይልቁንም በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 5/6/ እና 5/9/ ሥር በግልጽ እንደተደነገገው በፋዳራል መንግሥት የተቋቋመ ተቋም ተከራካሪ የሆነበት ጉዲይ ከመሆኑ አንፃር እና የክርክሩ መነሻም የመድን ውል መሆኑ ሲታይ በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የዲኝነት ሥልጣን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች መሆኑ በግልጽ በሕግ የተደነገገ ጉዲይ መሆኑን ነው።
ስለሆነም ለፋዳራል ፍርድ ቤቶች በግልጽ በተሰጠ የዲኝነት ሥልጣን የገንዘብ መጠኑን ብቻ መሰረት በማድረግ የአ/አ ከተማ ማኀበራዊ ፍ/ቤት ሥልጣን ነው በማለት በተጠሪ በኩል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም ብለናል።
ስለዚህ በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር ላይ ያለት ተከራካሪ ወገኖች ማንነት እና በክርክሩ የሚነሳው የሕግ ጥያቄን መሰረት በማድረግ ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንፃር ተመልክቶ ባለው አግባብ ሉስተናገድ የሚገባው ሆኖ ሳለ የአ/አ ከተማ ማኀበራዊ ፍ/ቤት ተቀብል የሰጠው ፍርድ የሥረ-ነገር ሥልጣን በሕግ በግልጽ ያልተሰጠው በመሆኑ ሉፀና የሚችል ፍርድ የለም ብለናል።
ስለሆነም የማኀበራዊ ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ተገንዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 231/1/ለ/ መሰረት መዝገቡን መዝጋት ሲገባው በጉዲዩ ላይ ውሣኔ መስጠቱ የመሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። ስለዚህም ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ በቂርቆስ ክ/ከተማ የቀበላ ዐ4 ማኀበራዊ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 953/97 የሰጠው ውሣኔ፣ የአ/አ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ2451 የሰጠው ፍርድ እና የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
ዐ82ዐ7 በ2ዐ/ዐ2/2ዐዐ2 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።
No topics extracted.