No summary available.
ግንቦት 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ኂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የድሬዲዋ አስተዲደር ቀበላ 06 አስተዲደር ጽ/ቤት - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፊንታዬ ምትኩ - ወኪል ሻ/ል አባይነህ መብራቱ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች በላልች የቤቱ ተከራይ በተባለት አራት ግለሰቦች ላይ በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- የሟች አባታቸውን ወራሽነት በፍርድ ቤት ያረጋገጡ መሆኑን፣አባታቸው በሕይወት እያለ በቀድሞ ቀበላ 15(በአሁኑ ቀበላ 05) ክልል ውስጥ ከአዋጅ ቁጥር 47/67 በፉት በቦታ ካርታ ቁጥር 3911 የሚታወቅ፣በቦታ ስፊት 136 ካሬ ሜትር ውስጥ የተሰራ ቤትና ቦታ እንዲፈሩ፣ይህንኑ ቤትና ቦታ በተጠሪ ስም ካርታ ተሰርቶ እንዱሰጣቸው ለቀድሞ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለአሁኑ የቦታ አስተዲደርና የመሬት ልማት አቤቱታ አቅርበው ይኸው አካል ካርታው በተጠሪ ስም ተሰርቶ እንዱሰጥላቸው ለድሬዲዋ አጠቃላይ ምክር ቤት ደብዲቤ የፃፈላቸው መሆኑን፣ተጠሪም ሟች አባታቸው በቤቱ የበለትን አበል በደረሰኝ ለቀበላው ገቢ ማድረጋቸውን፣ሆኖም ከዚህ በኋላ እንዱመለስላቸው የተባለውን ቤት ቀበላው ከተከራዮች አስለቅቆ ለተጠሪ ሉያስርክባቸው ያልቻለ መሆኑን ገልፀው ቤቱን እንዱያስረክባቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክሮችን በማንሳት ተከራክሯል። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስቶ የተከራከረው ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሰ በመሆኑ ተጠሪ ክስ ለመመስረት መብት ወይም ጥቅም የላላቸው መሆኑን፣ጉዲዩም በይርጋ የታገደ መሆኑን፣ጉዲዩን ለማየትም ፍርድ ቤት ስረ-ነገር ስልጣን የላለው መሆኑን የሚያሳዩ ነጥቦችን ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ ተጠሪ ቤቱ እንዱመለስላቸው ተወስኗል የሚለት ስልጣን ያላቸው አካላት የሰጡትን ውሳኔ መሰረት በማድረግ አለመሆኑንና ክርክራቸው በተገቢው ማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የድሬዲዋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር በአመልካች በኩል የቀረቡትን የክርክር ነጥቦችን ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጏ አከራካሪውን ቤት አመልካች ተከራዮችን አስለቅቆ ለተጠሪ ሉያስረክብ ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለድሬዲዋ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ውሳኔው ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ወኪል ሰኔ 19 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡- አከራካሪው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረዥም አመታት ቀበላው ሲያስተዲድር የቆየው እና ተጠሪ ቤቱ እንዱመለስ ተወስኖልኛል በማለት ያቀረቡት ክርክር ሥልጣን የላላቸው አካላት የሰጡት ውሳኔ ሁኖ እያለ ቤቱ እንዱመለስላቸው ተወስኗል ተብል ቀበላው ቤቱን ለተጠሪ እንዱያስረክብ ተብል መወሰኑ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አመልካች ለተጠሪ ያስረክብ የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ የተጠሪ ወኪል ቀርበው ሕዲር 30 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ አራት ገጽ ማመልከቻ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አግባብነት ያሳያለ ያሎቸውን ነጥቦች በማንሳት መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ወኪል በበኩላቸው መጋቢት 08 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው ጭብጥ ጉዲዩን የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት ለማየት የሥረ-ነገር ስልጣን አለው ወይስ? የለውም? የሚለው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አመልካች ሉያስረከብ ይገባል የሚለት ቤቱ በወቅቱ ሥልጣን ባላቸው አካላት እንዱመለስ ተወስኖ የቤቱ ካርታም በተጠሪ ስም ተሰርቶ በቤቱ ማህደር ጋር ተያይዞ ይገኛል በሚል ሲሆን አመልካች በበኩለ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት ወርሶት ቀበላው የሚያስተዲድረውና ለተጠሪ ቤቱ እንዱመለስ ውሳኔ ተሰጥቷል የሚባለው ስልጣን ባላቸው አካላት አለመሆኑን ገልፆ የሚከራከር መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ክልል ውስጥ በሚገኙ ንብረቶች ወይም መነሻቸው በዚሁ አስተዲደር ክልል በሆኑ እጅግ በርካታ አይነት ጉዲዮች ላይ ሰፉ የዲኝት ሥልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አለ። ከዚህ ደግሞ መገንዘብ የሚቻለው በዚህ ረገድ በተለይ የሥረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን በሚመለከት ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባ መሆኑን ነው።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስም የከተማው አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ያላቸው የዲኝነት ሥልጣን በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/96 አንቀጽ 33 ሥር በዝርዝር ተመልክቷል። በዚህ አንቀጽ ለፍርድ ቤቶቹ የተሰጠው የዲኝነት ሥልጣን በንኡስ አንቀጽ 1/ረ/ የተመለከተው የከተማው አስተዲደር ከሚያስረዲድራቸው የመንግስት ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱት ጉዲዮችን ያጠቃልላል። የዚህ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ሲታይም የከተማው አስተዲደር ፍርድ ቤት የዲኝነት ስልጣን የሚኖረው አከራካሪው ቤት ባለቤትነቱ የመንግስት ሆኖ በከተማው አስተዲደር የሚተዲደር መሆን የሚገባው መሆኑን ያስገነዘባል። ይህም ማለት ቤቱ የማን ንብረት ነው የሚል ወይም ስለቤቱ ባለሐብትነት በተመለከተ የሚነሳ ክርክር ሉኖር አይገባም። ክርክር ቢነሳ ላሆን የሚችለው ከባለቤትነት መብት በመለስ ያለትን ለምሳላ ከኪራይ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ጉዲዮች በተመለከተ ብቻ ነው። በከተማው ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን ስር የሚወድቀውም ይኸው ከባለቤትነት በመለስ ያለ ክርክር ብቻ ነው። ክሱ ወይም ክርክሩ የባለሃብትነት ጥያቄ የሚያስነሳ ከሆነ ግን ከከተማው ፍርድ ቤቶች የስረ-ነገር የዲኝነት ሥልጣን ውጭ ነው። በዚህ ረገድ የሚነሳ ክርክር የስረ-ነገር የዲኝት ሥልጣን የሚኖራቸው የፋዳራል ፍ/ቤቶች ናቸው።
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ባለቤትነት አከራካሪ የሆነ በመሆኑ የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ክርክሩን የሰሙት የስረ-ነገር የዲኝነት ስልጣን ሳይኖራቸው ሆኖ አግኘተናል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የላላቸው በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ//99 ሚያዝያ 12 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በመ//2001 ሰኔ 15 ቀን 2001 ዓ.ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ጉዲዩ በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን ሥር የሚወድቅ ባለመሆኑ ፍርድ ቤቶቹ ወደ ክሱ ስረ ነገር ገብተው ውሳኔ የሚሰጡበት የሕግ ምክንያት የለም ብለናል።
ለክርርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.