No summary available.
ሚያዝያ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቆዲ አክሲዮን ማህበር - ጠበቃ ጌታቸው ዓለሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ኃይላ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድን ስልጣን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ክሱን ያቀረቡት በወጣው ክፍት በላጦ ክረስት አዘገጃጀት ምርት ፍርማን ስራ መደብ ላይ ከላልች ሰራተኞች ጋር ተወዲድሬ በማሸነፍ እድገቱ እንዱሰጠኝ መደረግ ሲገባው ስለተከለከልኩ እድገቱ እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። በዚህም መሰረት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪ ለግለ ባቀረበው ጥያቄ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላለው መሆኑን፣ በሕብረት ስምምነቱ ደንብ አንቀፅ 15(4) እና በደረጃ እድገት አፈጻፀም መመሪያ አንቀጽ 11/1 እና 11/2 መሰረት የተጠሪ የደረጃ እድገት ኮሚቴ ውሳኔ የአሰሪው ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሳያፀድቅ የሻረው በመሆኑ ከሕግና ስርዓት ውጪ ተጠሪ የደረጃ እድገቱ በወሳኝ ቦርደ እንዱወሰንላቸው ክስ ማቅረባቸው ተቀባይነት የላለው መሆኑን በመግለፅ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ሸዋ ዞን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድም የአመልካችን መከራከሪያ ነጥቦች ውድቅ አድርጎ ለተጠሪ የስራ መደቡ እንዱሰጣቸው ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ቦርደ የሰጠው ውሳኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ የካቲት 04 ቀን 2002 ዓ/ም በጻፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም ጉዲዩን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ለማየት ስልጣን የነበረው መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ መጋቢት 29 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ጠበቃም ሚያዚያ 08 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ይህ ሰበር ችልት በመ/ አግባብ ያላቸውን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ድንጋጌዎችን በመመርመር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን የወል የስራ ክርክሮችን ማየት መሆኑን፣ አንድ የስራ ክርክር የወል የስራ ክርክር ነው የሚባለው ጉዲዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አለታዊም ሆነ አዎንታዊ የሆነ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ መሆኑን፣ ባንፃሩ አንድ የስራ ክርክር የወል ሳይሆን የግል የስራ ክርክር ነው ልባል የሚችለው የክርክሩ ውጤት በተከራካሪው ሰራተኛ (ሰራተኞች) ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሆኖ ሲገኝ ነው በማለት አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ የስራ መደቡ ይሰጠኝ በማለት ያቀረቡት ክስ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አለታዊም ሆኖ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የስራ ክርክር አይደለም። በመሆኑም ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት እንጂ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ አይደለም። ስለሆነም ጉዲዩን ቦርደ ለማየት ስልጣን አለው ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሸዋ ዞን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ በመ/ቁጥር 650/01/2001 መስከረም 29 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 25 ቀን 2002 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተነሳው ክርክር የግል የስራ ክርክር እንጂ የወል ባለመሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.