No summary available.
ሚያዝያ 13 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ታሪኳ ላዕከ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ቂጤሳ ገብሬ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድን የሚመለከት ነው።
ተጠሪ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ክሱን ያቀረቡት በአመልካች ድርጅት በጥበቃ ስራ ላይ ተመድቤ በማገልገል ላይ እያለሁ አመልካች በብረታ ብረት ብየዲ ስራ ሰራተኞችን አወዲድሮ ለማሳደግ የካቲት 19 ቀን 1999 ዓ.ም ባወጣው የውስጥ ማስታወቂያ የተጠየቀውን መስፈርት አሟልቼ በመስሪያ ቤቱ የውስጥ አሰራር መመዘኛ መሰረት 30% ሲቀየር 11/40/30 አምጥቻለሁ፣ ይህ ውጤት ከላላው የስራ ምዘና ውጤት ጋር ሲደመር 54.76% በመሆኑ የሚያሳልፈኝ ሆኖ ሳለ አመልካች የተግባር ፈተና ማለፉያ ነጥብ 60% በላይ መሆን ስላለበትና የስራ መደቡም ከፍተኛ ችልታና ጥንቃቄ የሚጠይቅ ስለሆነ በተግባሩ ስላላለፍክ እድገቱን ልታገኝ አይገባም በማለት ማስታወቂያ ስላወጣ ማስታወቂያ ተሰርዞ እድገቱ እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በሚል ነው። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። በዚሀም መሰረት የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የላለው መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስቶ የተከራከረ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ተጠሪ ዝቅተኛ ነጥብ ያመጡ በመሆኑ ቦታ ሉሰጣቸው እንደማይገባ እና በውድድር ቅጥሩን ለመፈፀም ማስታወቂያን ማውጣቱ ተገቢ መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ጉዲዩን ተመልክቶ በግራ ቀኙ በኩል የቀረቡትን ማስረጃዎችን በመመርመር ተጠሪ የተግባርና የፁሐፍ ፈተናውን ስለማለፊቸው ያቀረቡት ማስረጃ አለመኖሩን፣ በተቃራኒው አመልካች ድርጅት ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች የሚያስረደት ተጠሪ ፈተናውን ወስደው ከተቀመጠው መስፈርት ዝቅተኛ ያመጡ መሆኑን ጠቅሶ ክሱን ውድቅ አድርጎ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ ብቸኛ ተወዲዲሪ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በጠቅላላ ውጤት ከመቶ 54.76 በማግኘት ከ50% በላይ ያገኙ ሆኖ እያለ በተግባርና በፁሐፍ ፈተና ከመቶ 60 ስላጡ በሕብረት ስምምነት ወይም በልላ መመሪያ በግልጽ እስካልተደነገገ ጊዜ ድረሰ ይህንን ስላላሟላ ተብል ከውጪ ተወዲዲሪ እንዱቀርብ መደረጉ ያላግባብ ነው የሚለውን ምክንያት በመያዝ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ የቦታውን መስፈርትና ውጤት ስለሚያሟለ ሉሰጣቸው ይገባል ሲል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሐምል 14 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም ጉዲዩን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት ያሁኑ አመልካች ያቀረበው መቃወሚያ መታለፈ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ሕዲር 09 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ ተጠሪ ክሱን የመሰረቱት የእድገት ደረጃ ይሰጠኝ በሚል ሲሆን አመልካች ለተጠሪ ደረጃው ላሰጥ አይገባም በማለት የሚከራከረው ተጠሪ የተወዲደሩበት የብየዲ የሥራ መደብ በወጣው የውስጥ ማስታወቂያ ሆኖ እንዱወዲደሩ እድል ተሰጥቷአቸው በሕብረት ስምምነት አንቀፅ 17 ንዐስ አንቀፅ 2፣ 3 እና 7 ድንጋጌዎች መሰረት ከመስፈርቶቹ አንደ የሆነውን የተግባርና የፅሐፍ ፈተና ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የምርታማነት ማሻሻያ ማዕከል ፈተና እንዱወስደ ተልከው ፈተናውን ተፈትነው ያገኙት ውጤት 38% በመሆኑና የማለፉያ ነጥብ ደግሞ 60% እንደሆነ፣ ተጠሪ ያገኙት ነጥብም ዝቅተኛ መሆኑን ማዕከለ በፅሁፍ የገለፀው ውጤትም ለመራጭ ኮሚቴ ቀርቦ የተወዲደሩበት የስራ መደብ የብየዲ ስራ በመሆኑ እና ይህ ደግሞ የተግባር ስራ ሆኖ ከፍተኛ እውቀትና ችልታ እንደሚያስፈልገው ገልጾ ተጠሪ ይህንን ባለማለፊቸው ለቦታው ብቁ እንዲልሆኑ በመግለፅ መሆኑን ነው። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የተቻለው አመልካች ድርጅት ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ለመምረጥ የራሱ የሆነ መስፈርትና ሥርዓት የዘረጋ መሆኑን ነው። ተጠሪ ደግሞ የሚከራከሩት መስፈርቱና ሥርዓቱን ስለማሟላ ቦታው ይገባኛል በማለት ነው።
ይህ ሰበር ችልት በመ/ አግባብነት ያላቸውን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ድንጋጌዎችን በመመርመር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን የወል የስራ ክርክሮችን ማየት መሆኑን፣ አንድ የስራ ክርክር የወል የስራ ክርክር ነው የሚባለው ጉዲዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አለታዊም ሆነ አዎንታዊ የሆነ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ መሆኑን፣ ባንፃሩ አንድ የስራ ክርክር የወል ሳይሆን የግል የስራ ክርክር ነው ልባል የሚችለው የክርክሩ ውጤት በተከራካሪው ሰራተኛ (ሰራተኞች) ላይ ብቻ ተወሰኖ የሚቀር ሆኖ ሲገኝ ነው በማለት አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በልላ በኩል አንድ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከማየቱ በፉት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በራሱ ማረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231(1(ሀ)) ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ ያሰገነዝባለ። ክርክሩ በየትኛውም ደረጃ ቢገኝ ይኸው መረጋገጥ አለበት።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ የስራ መደቡ ይሰጠኝ በማለት ያቀረቡት ክስ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አለታዊም ሆኖ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሲሆን የወል የስራ ክርክር ነው። በመሆኑም ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው የሰራተኛ እና አሰሪ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ እንጂ ፍርድ ቤት አይደለም። ስለሆነም ጉዲዩን ፍርድ ቤቱ አይቶ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 05 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 14 ቀን 2001 ዓ.ም የተሻረው ውሳኔ ፍርድ ቤቶቹ ስልጣን ሳይኖራቸው የተሰጠው በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተነሳው ክርክር የወል የስራ ክርክር እንጂ የግል ባለመሆኑ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.