No summary available.
መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ብርሃነ ጥዐም - ሙለጌታ ወንድም ቀረቡ ተጠሪ፡- የጉምሩክ ባለሥልጣን - ዲንኤል ጥበቡ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ያላግባብ የተከፈለ ቀረጥ ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባሁኑ ተጠሪ ላይ ሚያዝያ 01 ቀን 1990 ዓ.ም በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም በዱክላራሲዮን ቁጥር 718/90፣ 719/90 እና 1600/90 የተመዘገቡትንና በቻይና፣ ማለዥያ፣ ኮሪያ እና ጃፓን ሃገር የተሰሩትን የኤላክትሮኒክስ እቃዎች ከባንክ በተገኘ የውጭ ምንዛሬ በመግዛት በምፅዋ ወደብ በኩል ወደሃገር ውስጥ ሲያስገቡ የተጠሪ ድርጅት ዛለአንበሳ ጣቢያ ብር 87,760.65(ሰማንያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ከስልሳ አምስት ሳንቲም) የቀረጥ ክፍያ አመልካች እንዱከፍለ ጠይቋቸው ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ተጠሪ ቀሪ የቀረጥ ሂሳብ አለብህ በማለት እቃዎችን በመያዙ ምክንያት ያላግባብ ብር 244,866.10(ሁለት መቶ አርባ አራት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም) እንዲስከፈላቸው ገልፀው ይህንኑ ገንዘብ ተጠሪ ከነወለደ እና ከክሱ ወጪና ኪሳራ ጋር ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚይሳይ ነው። ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ ቀረጡን በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ያስከፈለ መሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃዎችን በመመርመር ተጠሪ ቀረጡን ያስከፈለበት አግባብ ከመመሪያ ቁጥር 10/96 ውጪ ነው በማለት የተጠሪን ክርክር ውድቅ አድርጎ ለክሱም ኃላፉ በማድረግ ክሱ የተመሰረተበትን ገንዘብ ከሚያዝያ 08 ቀን 1990 ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ 9% (ዘጠኝ በመቶ) ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ በመሻር ተጠሪ የቀረጡን ገንዘብ የሚመልስበት ምክንያት የለም በማለት ወስኗል። ከዚህም በኋላ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጥር 04 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስር ፍርድ ቤት ያልቀረበውን የተጠሪ መከራከሪያ ነጥብ መሰረት አድርጎ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ መሻሩ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ስነ-ስርዓታዊ የሆነውን ምክንያት መነሻ በማድረግ የሰጠውን ዲኝነት ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329(1) አንፃር አግባብነቱንና የጉዲዩን ፍሬ ነገር የሕግ ክርክር ተመልክቶ ውሳኔ መስጠት ነበረበት ወይስ አልነበረበትም? የሚለትን ነጥቦች ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎአል። ተጠሪም በነገረ ፈጁ አማካኝነት ጥር 27 ቀን 2002 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ የአዋጅ ቁጥር 68/89 አንቀፅ 48(7/11)፣ 53 እና መመሪያ ቁጥር 10/1996 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ውሳኔው ሉፀና ይገባዋል በማለት ተከራክሯል። የአመልካች ጠበቃም የካቲት 15 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል ወይስ አልተፈፀመበትም? የሚለው ጥቅል ጭብጥ ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ክሱን ሉመሰርቱ የቻለት ያላግባብ የከፈልኩት የቀረጥ ገንዘብ ሉመለስልኝ ይገባል በሚል ሲሆን አመልካች በበኩለ ክፍያውን ያስፈፀመው በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የዋጋ መረጃን በማየት መሆኑን ገልፆና ያላግባብ የተከፈለ የቀረጥ ገንዘብ የላለ መሆኑን ጠቀሶ ተከራክሯል።
የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም እና አሰራሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀፅ 47 ላይ እንደተመለከተው ወደ ሃገር ውስጥ ለሚገባ ማናቸውም ዕቃ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ የሚሆነው በትክክል ለዕቃው የተደረገ ጠቅላላ ወጪ ነው። ዕቃው የተገዛበት ዋጋ ደግሞ ከወጪዎች አንደ ነው። ስለሆነም ለቀረጥ ማስከፈያ መሰረት የሚሆነው ትክክለኛ የዕቃው ዋጋ ስለመሆኑ ሕጉ በዋናነት ያስቀመጠው አሰራር ነው።
ከዚሁ የሕጉ መንፈስ መረዲት የሚቻለው ላላው ቁም ነገር ደግሞ በአስመጪው የሚቀርበው የእቃው ዋጋ ግምት ትክክለኛውንም የዕቃውን ዋጋ የማይናገር መሆኑ ከተረጋገጠ የቀረጥ ሂሳብን ለማስላት መነሻ (መሰረት) ላሆን የማይችል መሆኑን ነው። በመሰረቱ ወደ አገር ውስጥ የሚገባ ዕቃ ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ምን ያህል እንደሆነና እንዳት እንደሚሰራ በአዋጅ ቁጥር 60/1989 አንቀፅ 48 ስር ተዘርዝሯል። የተጠቀሰው የአዋጁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 7 እና 8 ድንጋጌዎች ሲታዩም የጉምሩክ ባለስልጣን በአስመጪው የቀረበለትን የዋጋ ግምት አልቀበልም በማለት የቀረጥ ሂሳቡን ለማስላት ላልች አማራጭ መንገድችን መከተል የሚችል ስለመሆኑ ያስገነዝባለ።
የተጠቀሰው የአዋጅ አንቀፅ ንዐስ ቁጥር 6 ድንጋጌ ደግሞ የጉምሩክ ባለስልጣን በአስመጪዎች የቀረበለትን የዋጋ ግምት አልቀበልም ስለሚልበት ሁኔታ የገቢዎች ቦርድ መመሪያ ማውጣት የሚችል መሆኑን ደንግጓል። በዚሁ ሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረትም የተጠቀሰው አካል መመሪያውን ማውጣቱ የተረጋገጠ ሲሆን በዚህ መመሪያ መሰረትም በትራንዛክሽን ዋጋ ላይ የተመሰረተ የጉምሩክ ዋጋ አተማመን ተግባራዊ የማይሆንባቸው ምክንያቶች ተቀምጠዋል። ከእነዚህም ምክንያቶች መካከል ወደ አገር ውስጥ የገባው እቃ ዋጋ ከአንድ ዓይነት እና ከተመሳሳይ ዕቃዎች ዋጋ በጉምሩክ ከሚፈቀደው ልዩነት በላይ አንሶ መገኘት ስለመሆኑ መመሪያው በአንቀፅ 1(5) ስር አስቀምጧል። ወደ ሃገር በገባ ወይም ከሀገር በወጣ ዕቃ ላይ የተከፈለው ቀረጥ በማናቸውም ምክንያት ሉከፈል ከሚገባው ቀረጥ ያነሰ መሆኑ በምርመራ የተደረሰበት እንደሆነ ደግሞ ባለሥልጣኑ የእቃውን ባለቤት ወይም ወኪለን በልዩነት ያልተከፈለውን ቀረጥ ማስከፈል እንደሚችል በአንቀጽ 57(1) ስር በግልፅ አስፍሯል። የዋጋ ኢንቮይስ ውድቅ የሆነበት ቀረጥ ከፊይ ቅሬታ ካለው በአዋጅ ቁጥር 60/1989 አንቀጽ 53 መሰረት ለተጠሪ መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፉ አቅርቦ ተገቢው ውሳኔ እንዱሰጥበት ማድረግ የሚችል ሲሆን፤ በዚሁ የበላይ ኃላፉ ውሳኔ ቅሬታ ካለው ብቻ ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት መሄድ የሚችል መሆኑን ተመልክቷል። ይህ ስርዓት ሳይፈፀም በቀጥታ በፍ/ቤት ክስ የሚመሰረትበት አግባብ የላለ መሆኑን ከተጠቀሰው ድንጋጌ መንፈስ እና ይዘት መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። ይህ በሕጉ ላይ የተመለከተው የስነ-ስርዓት ጥያቄ ነው። ይኸው የስነ-ስርዓት ጉዲይም በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት ባግባቡ መፈፀም አለበት። የራሱ የሆነ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብልም ይታሰባል።
በብልጫ የተከፈለ የቀረጥ ገንዘብ ለከፊዩ ሉመለስ እንደሚገባ አዋጁ በአንቀፅ 55 ስር በግልፅ ደንግጓል።
ተጠሪ ቀሪ የቀረጥ ክፍያ መኖሩን አረጋግጦ ተገቢ ነው ያለውን የክፍያ ጥያቄ አመልካች እንዱፈፅሙ ጠይቋል።
ይህም የሚያሳየው የአመልካች ኢንቮይስ ውድቅ የተደረገ መሆኑን ሲሆን አመልካች በአዋጁ አንቀፅ 53(1) መሰረት ያነሱት እና የተጠቀሙበት ተቃውሞ አለመኖሩን ነው። በመሆኑም አመልካች ክስ የመሰረቱበትን የቀሪ ቀረጥ ክፍያ ጥያቄ በተጠሪዎች በኩል በአዋጁ አንቀጽ 53(1) መሰረት ተቃውሞ ቀርቦ ተገቢው ለውጥ ባልተደረገበት ሁኔታ በፍርድ ቤት ክስ መስርተው ተቀባይነት ማግኘታቸው ስነ ስርዓቱን ያልጠበቀ ነው በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑ የሚነቀፍበት የስነ-ስርዓትም ሆነ የመሰረታዊ ሕግ ምክንያት የለም።
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ባለመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሕዲር 16 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 28 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.