No summary available.
ጥር 12 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን - ነ/ፈጅ አክሉለ አበባው - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ድራጋድስ ኮንስትራክሽን - የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከውል ውጪ ኃላፉነትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ ጥቅምት 22 ቀን 1998 ዓ.ም. በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም፡- ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ ኮልፋ ቀራኒዮ አካባቢ የመንገድ ሥራ ሲያከናውን በአመልካች ንብረት ላይ ግምቱ ብር 25,569.85 /ሃያ አምስት ሺህ አምስት መቶ ስልሣ ዘጠኝ ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም/ የሆነ ጉዲት ማድረሱን ገልፆ ይህንኑ ገንዘብ ከነወለደ ወጪው ጋር እንዱተካ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ተከሣሽ ድርጅት በግሪክ አገር ሕግ መሰረት የተቋቋመ አድራሻውም አቴንስ የሆነ የውጭ ሀገር ኩባንያ ነው፣ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥም አልተመዘገበም ስለዚህ በመልካችና በተጠሪ መካከል የሚነሳ አለመግባባት በየትኛው ሀገር ሕግ ይታያል፣ በየትኛው ፍርድ ቤት ይታያል የሚል የግል ዓለም አቀፍ ሕግ ስለሚያስነሳ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አንስቶ ተከራክሯል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ይህንኑ የተጠሪን መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ጉደዩን መርምሮ ጉዲዩ የግል ዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስነሳ በመሆኑና ሥልጣኑም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አይቶ ለመወሰን ስልጣን የለውም ሲል የአመልካችን ክስ በብይን ዘግቷል። በዚህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ብይን ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ጥር 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ብይን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ በተጠሪና በአመልካች መካከል ያለው የፍትሐብሕር ክርክር ጉዲይ ጉዲቱ የደረሰው ተጠሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት ስለሆነ እና በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዲት ደግሞ ክሱ መመስረት ያለበት ጉዲቱ በደረሰበት ሀገር ሕግና ፍርድ ቤት መሆኑ እየታወቀ የአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11/2ሀ/ ያላግባብ ተጠቅሶ ክሱ መዘጋቱ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን መዝጋቱ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ጉዲዩ በቃል ሉሰማ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረቡ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ብይንና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአመልካች ክስ መሰረት ያደረገው ከውል ውጪ ኃላፉነትን በሚመለከት የሚገዙ ድንጋጌዎች መሆኑ፣ ተጠሪ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ጉዲት ያደረሰው ስራውን በኢትዮጵያ ውስጥ ሲያከናውን መሆኑን ክሱ የቀረበውም ጉዲቱ በደረሰበትና ንብረቱ በሚገኝበት ክልል በሚገኘው ፍርድ ቤት መሆኑን ነው። እንዱህ ከሆነ ደግሞ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተነሳው ክርክር የንብረት ጉዲት ካሣ በመሆኑ ክሱ ሉመሰረት የሚገባው የገንዘቡ መጠን ግንዛቤ ውስጥ ሲገባ የገንዘብ መጠኑን መሰረት አድርጎ የሚወስነው የሥረ- ነገር ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ጉዲቱ በደረሰበትና ንብረቱ በሚገኝበት ክልል በሚገኘው ፍርድ ቤት ነው።
ይህ ስለመሆኑም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 27/1/ ድንጋጌ ያሳያል። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በዚህ አንፃር ተገንዝቦ አይቶ የመወሰን ስልጣን የራሱ ሆኖ እያለ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11/2/ሀ/ ድንጋጌን ያለቦታው ጠቅሶ የአመልካችን ክስ መዝጋቱ እና ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ይህንኑ መቀበለ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ዐ9737 ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሕዲር 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን ያለው በመሆኑ የአመልካችን ክስ ተቀብል ግራ ቀኙን በቀሪ መከራከሪያ ነጥቦች ላይ በማከራከር ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341/1/ መሰረት መልሰንለታል።
No topics extracted.