No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 4622ዐ ጥር 18 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የደቡብ ክልል የሐዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት - ነ/ፈጅ ከተማ ጌታነህ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የሐዋሳ ደብረ ምህረት ቅ/ገብርኤል ገዲም - ጠበቃ ቸርነት ገ/ሕይወት - ቀረቡ።
ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነ ተጠሪ በሐዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአመልካች እና በላልች ሁለት ተከሣሾች ላይ ያቀረቡት ክስ ነው። ተጠሪ በክሷ ከቤ/ክርስቲያኗ ይዞታ 1632 ካ.ሜ. ለሥር አንደኛ ተከሣሽ ለጊዜያዊ ማረፉያነት ተሰጥቷቸው የነበረ መሆኑን፣ ተከሣሹ አሁን ቤት መስራታቸውን፣ ተከሣሹ ካርታና ፕላን ጠፊብኝ ብለው አዱስ ካርታ እንዱሰጣቸው ለወረዲ ፍ/ቤት አመልክተው እንዱሰጣቸው ማድረጋቸውን፣ አመልካችም ተገቢውን ማጣራት ሳያደርግ አንደኛ ተከሣሽ ከያዙት ቦታ ላይ ለ832 ካ/ሜ ይዞታ ካርታ ሲሰጣቸው ቀሪው 8ዐዐ ካ/ሜ ለሥር ሁለተኛ ተከሣሽ በሉዝ በመምራት ካርታና ፕላን መስጠቱን በመግለጽ ለሁለቱም ተከሣሾች የተሰጠው ካርታና ፕላን ተሰርዞ ይዞታው ለተጠሪ ይመለስ በማለት ጠይቃለች። አመልካችም ለቀረበው ክስ ቤ/ክርስቲያኗ ያቀረበችው ማስረጃ ከአ/ቁ 47/67 በፉት የተሰጠ ስለሆነ ከአዋጁ በኋላ መሰረዙን፣ ከአዋጁ በኋላ የተሻሻለውን ምስክር ወረቀት አለመወሰዶን፣ ካርታውና ፕላኑ የተሰጠው በፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት መሆኑን፣ ለክርክር ምክንያት የሆነው ቦታ ከመንግሥት የተወረሰ መሆኑን፣ ለሥር ተከሣሾቹ ካርታና ፕላን የተሰጠው በሉዝ ኮሚቴ ስለሆነ አቤቱታ ላቀርብ የሚችለው ለሉዝ ቦርድ ኮሚቴ እንደሆነ፣ ለከፍተኛ ፍ/ቤት የሚቀርበው የካሣ ጉዲይ ብቻ እንደሆነ በመከራከር ክሱ ውድቅ እንዱሆንለት ጠይቋል። ላልቹም ተከሣሾች መልሳቸውን አቅርበዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ይዞታው ከአ/ቁ. 47/67 ወዱህ በተጠሪ እጅ አይደለም፣ አንደኛ ተከሣሽ ይዞታው በሰራተኛነት ሳይሆን በባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥቷቸዋል፣ ከይዞታቸው ከፉለ በሉዝ ኮሚቴ ፀድቆ ባለቤት ሆነዋል። ቀሪውን በሉዝ ኮሚቴ ለሁለተኛ ተከሣሽ ተሰጥቷል፤ አመልካች በሉዝ ኮሚቴ ውሣኔ መሰረት ነው የሚፈጽመው፣ በሉዝ ኮሚቴ ውሣኔ ቅር ከተሰኘች ቅሬታው ማቅረብ ያለበት ለሉዝ ኮሚቴ ነው፣ የባለቤትነት ምስክር ወረቀት በፍርድ ሉሰረዝ አይችልም፣ በመሆኑም ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሣኔ ላይ ተጠሪ ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባ ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል። ይህ ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን ችልቱ ይዞታው የተጠሪ መሆኑ ማስረጃዎች ያረጋግጣለ፣ ይዞታው የተሰጠው ለሕዝብ አገልገልት ሳይሆን ለላላ ግለሰብና መ/ቤት በመሆኑ ሕጋዊ አይደለም፣ ለሕዝብ ጥቅም ቦታ ስለማስለቀቅ በወጣው አዋጅ መሰረት ተገቢው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ እንዱለቁ የተደረገ ስላለሆነ ፍ/ቤቶቹ ስለቦታ ማስለቀቅ የተመለከቱት አዋጆች ተጠቅመው ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለውም ሉለ አይችልም በማለት ተከሣሾቹ ይዞታውን ለተጠሪ እንዱመልሱ ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም ካርታው እንዱሰረዝ በፍ/ቤት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። በዚህም መሰረት ግራ ቀኙ ቀርበው ክርክራቸው ተሰምቷል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
አመልካች ክስ ያቀረበችው ከይዞታዋ ላይ ተቀንሶ ለሥር አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሣሽ የተሰጣቸው ስለሆነ የተሰጣቸው ካርታና ፕላን ተሰርዞ ይዞታውን ተከሣሾቹ እንዱመልሱላት ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የሐዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክስ የቀረበበትን ጉዲይ ለማየት ስልጣን የለኝም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም መሰረት ያደረገው ሁለት ነገሮችን ነው። አንደኛው አከራካሪው ይዞታ ለሥር አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሣሾች የተሰጠው በሉዝ ቦርድ ኮሚቴ ስለሆነ በኮሚቴው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ወገን ቅሬታውን ማቅረብ ያለበት ለቦታ ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንጂ ለፍ/ቤት አይደለም የሚል ሲሆን ሁለተኛው የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በፍርድ ለመሰረዝ የማይቻል ለመሆኑ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ ውሣኔ ሰጥቷል በሚል ነው። ይህ ችልትም በቅድሚያ ክስ የቀረበበትን ጉዲይ ለማስተናገድ ፍ/ቤቶች ስልጣን ያላቸው መሆን አለመሆኑን መርምሯል።
ከመዝገቡ ሂደት ተጠሪ ይዞታዬ ነው የምትለውን የቦታ ይዞታ ቀንሶ ለሥር አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሣሾች ሰጠው የሉዝ ቦርድ ኮሚቴ መሆኑን ተረድተናል። የከተማን ቦታ በሉዝ ስለመያዝ የወጣው የፋዳራል አ/ቁ. 272/2994 እንዱሁም ክልለ ይህንን አስመልክቶ ያወጣቸው አዋጅና ደንቦች የሉዝ ቦርድ ኮሚቴ በሰጠው የቦታ ማስለቀቅ ውሣኔ ላይ ቅሬታ ያለው ሰው ቅሬታውን ማቅረብ ያለበት በቅድሚያ ውሣኔውን ለሰጠው አካል ሲሆን በዚህ አካል ምላሽ ካልተስማማ ይግባኙን ለቦታ ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ነው። በካሣ ጉዲይ ላይ ካልሆነ በቀር ጉባኤው የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ ይሆናል። በመሆኑም አንድ ሰው ይዞታውን እንዱለቀቅ የተደረገው በሕግ የተመለከቱትን ሥርዓቶች ሳይከተል ከሆነ ይህንን ጉዲይ አስመልክቶ ይግባኝ ሉያቀርብ የሚችለው ለጉባኤው ነው። ለፍ/ቤት ይግባኝ ላቀርብ የሚችለው የካሣውን ጉዲይ በተመለከተ ብቻ ነው።
No topics extracted.
በተያዘውም ጉዲይ ተጠሪ ከይዞታዋ ላይ ተቀንሶ ለሥር ተከሣሾች የተሰጠው በሉዝ መሆኑ ስለተረጋገጠ ይዞታው የተሰጠው በሕጉ አግባብ ካልሆነ ይህንኑ ቅሬታ በቅድሚያ ውሣኔውን ለሰጠው አካል፣ በመቀጠል ደግሞ ለቦታ ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ ነበረባት። በመሆኑም ከጅምሩም ቢሆን ክስ የቀረበበትን ጉዲይ ፍ/ቤቶች አይተው ለመወሰን ስልጣን አልነበራቸውም። ከፍ ሲል በተጠቀሱት ምክንያቶችም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በሉዝ ኮሚቴ የተወሰነውን ጉዲይ አከራክሮ ውሣኔ መስጠቱ ያለስልጣኑ በመሆኑ መሰረታዊ ሕግ ስህተት ፈጽሟል። ስለዚህም ተከታዩ ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
የደ/ብ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 27382 ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የሐዋሣ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ5446 ታህሣሥ 1 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እና የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 23971 የካቲት 4 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።