No summary available.
ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡-
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አመልካቾች በአንደኛ ተጠሪ ላይ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት የመሰረቱት ክስ ነው። አመልካቾች ከሟች አባታቸው በውርስ ያገኙትን በወረዲ 1 ቀበላ 8 ውስጥ የሚገኘውን የቤ/ቁ 1273 የሆነውን ቤት አንደኛ ተጠሪ ቀድሞ ከሚያስተዲድረው ሁለተኛ ተጠሪ መከራየታቸውን ምክንያት በማድረግ አለቅም ስላለ የቤቱ ኪራይ ከፍለው ቤቱን እንዱያስረክቡ ክስ መስርተዋል። አንደኛ ተጠሪ ለክሱ መልስ እንዱሰጡና ሁለተኛ ተጠሪም በክርክር ውስጥ እንዱገባ ከተደረገ በኋላ ፍ/ቤቱ የአመልካቾች የቤት ባለቤትነት ደብተር በአ/አበባ ከተማ መስተዲድር ምክር ቤት የስራና ከተማ ልማት ቢሮ የተሰረዘ በመሆኑ አመልካቾች ቤቱን ለመረከብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። አመልካቾች ውሳኔውን ለማስለወጥ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡት ይግባኝም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። የአሁኑም የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካቾች ዋነኛ ቅሬታ የአ/አበባ ከተማ መስተዲድር ምክር ቤት የስራና ከተማ ልማት ቢሮ የባለቤትነት ደብተሩን ለመሰረዝ ስልጣን የለውም የሚል ነው። ችልቱም የስራና ከተማ ልማት ቢሮ ደብተሩን የሰረዘው በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ሲል አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። ግራ ቀኙም ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው በሰበር ችልት ለመመርመር የቀረበው ነጥብ የአ/አበባ ከተማ የስራና ከተማ ልማት ቢሮ የአመልካቾችን የባለቤትነት ደብተር ለመሰረዝ ስልጣን አለው የለውም የሚለው ነው። ከክርክሩ የአ/አበባ ከተማ ስራና ከተማ ልማት ቢሮ ደብተሩን የሰረዘው የስራና ከተማ ልማት ሚ/ር በ22/07/1991 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ በሚ/ር መስሪያ ቤቱ ይገኙ የነበሩ የቤት ጉዲዮች ከስራተኞቹ ጋር ለአ/አበባ መስተዲድር ምክር ቤት እንዱያስረክብ ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት በተላለፈው ትእዛዝ መሰረት ከየካቲት 1 ቀን 1991 ዓ.ም ጀምሮ እነዚህ ጉዲዮች በአ/አበባ መስተዲድር ምክር ቤት ስራና ከተማ ልማት ቢሮ እንዱያስተዲድር በመግለፁ ምክንያት መሆኑን ጠበቃ አበራ ጣሰው ቀረቡ ተገንዝበናል። የጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ስራ የመከታተልና በበላይነት የመቆጣጠር ስልጣን ያለው እንደመሆኑ መጠን የስራና ከተማ ልማት ሚ/ር ቤቶችን የሚመለከት ጉዲይ ለአ/አበባ ስራና ከተማ ልማት ቢሮ እንዱያስተላልፍ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ስራውንና ሰራተኞቹን ለቢሮው አስተላልፎል። በዚህ መሰረት ቢሮው ስራውን ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም ወቅት ነው የአመልካቾች የቤት ባለቤትነት ደብተር የተሰረዘው። ስለሆነም አመልካቾች ደብተሩ ስልጣን በላለው አካል ነው የተሰረዘው በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም። የስር ፍ/ቤትም አመልካቾች የቤት ባለቤትነት ደብተር ስልጣን ባለው አካል የተሰረዘ በመሆኑ ክሳቸውን ተቀባይነት የለውም ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19448 ሐምል 28 ቀን 1996 የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 33840 ጥቅምት 13 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.