No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 5ዐ225 ሐምል 5 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጉዲት ካሣ ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ባለቤት ላይ በመሰረቱት ከውል ውጪ ኃላፉነትን መሰረት ባደረገ ክስ መነሻ ነው። የክሱ ፍሬ ይዘት ባጭሩ፡- የተጠሪዎች አባት በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ተገጭታ ሕይወታቸው በማለፈ አባታቸው በሕይወት እያለ በሚሰሩት ሥራ በቀን ብር 22.00 /ሃያ ሁለት ብር/ እያገኙ ከዚሁ ገቢ ስልሳ ከመቶ የሚሆነውን እየሰጧቸው ያስተዲድሯቸው የነበሩ መሆኑንና ሟች አባታቸው በመኪና ግጭት ሲሞቱ እድሜያቸው 4ዐ ዓመት እንደበሩ፣ ወደፉትም እስከ ስልሳ አምስት ዓመት ሉደርሱ ይችለ እንደነበር በመግለጽ በዚሁ ጉዲት ምክንያት በአጠቃላይ የብር 125,23ዐ.00 /አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሣ ብር/ ጉዲት እንደደረሰባቸው በመጥቀስ ይህንኑ የጉዲት መጠን እንዱተካላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የመኪናው ባለቤትና አሽከርካሪው በላለበት ጉዲዩ የታየ ሲሆን የአሁኑ አመልካች በጣልቃ ገብነት ወደ ክርክሩ ገብቶ የተጠሪዎች አባት በአመልካች ደንበኛ ተሽከርካሪ ተገጭተው ሕይወተቸው ሲያልፍ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆኑና ራሳቸውን መቻል እና ማስተዲደር የሚችለበትና ከዚህም አልፍ አባታቸውን ሉጦሩ የሚችለ መሆኑን በመግለጽና ለክሱ ኃላፉነት እንደላለው በመጥቀስ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ95/1/ ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ ዋቢ በማድረግ ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መሰረት በማድረግ የተሽከርካሪውን ባለቤት ለጉዲቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ81 መሰረት ኃላፉ አድርጎ አመልካችን ተጠያቂ አድርጎአል። የጉዲት መጠኑንም በአጠቃላይ ብር 21,ዐዐዐ.00 /ሃያ አንድ ሺህ/ አድርጎ አመልካች እስከ ሰላሳ ሺህ ብር በገባው የዋስትና ግዳታ መሰረት እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ሕዲር ዐ1 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪዎች ጉዲቱ ሲደርስ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ ሆነው እያለ ጉዲቱ በቀለብ መልክ እንዱከፈል ተብል መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ95/1/ እና ስለቀለብ የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን መንፈስ ያላገናዘበ የቀረበ የለም።
በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም እድሜያቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በላይ ለሆናቸው ተጠሪዎች አመልካቹ ከሟቹ አባታቸው ሲያገኙ የነበረውን ቀለብ በካሣ መልክ ይክፈል የመባለን አግባብነት ለማየት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ የግራ ቀኙ ክርክር ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በዋለው ችልት ተሰምቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች አባታቸው በአመልካች ደንበኛ ተሽካርካሪ ተገጭተው ሲሞቱ እድሜአቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በላይ መሆኑን፣ በወቅቱ ተማሪዎች ሆነው በሟች አባታቸው ሲረደና ሲተዲደሩ የነበሩ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ከማረጋገጡም በላይ አመልካች በዚህ የሰበር ችልትም ሆነ በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች እድሜአቸው አስራ ስምንት ዓመት ሞልቷቸዋል ብል ከመከራከር ውጪ በእርግጥም ራሳቸውን ይችለ የነበረ ሁኔታ ስለመኖሩ ግልጽ አለመከራከሩን ነው። እንዱህ ከሆነ ተጠሪዎች እድሜአቸው አስራ ስምንት ዓመት በላይ ስለሆነ ብቻ በመኪና ግጭት ሕይወቱን ያጣውን አባታቸውን ካሣ አይገባቸውም ልባል የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። የጉዲት ካሣ በቀለብ መልክ እንዱከፈል ሕጉ ሲፈልግ እድሜው አስራ ስምንት ዓመት የሞላው ሁለ ሉጠይቅ አይችልም ማለት እንደሆነ ስለቀለብ የተደነገጉት ድንጋጌዎች የሚያስረደት ጉዲይ ነው። ዋናውና ትልቁ ቁም ነገር ቀለብ ጠያቂው ያለበት ሁኔታ ነው።
ቀለብ ጠያቂው ቀለቡን ሉያገኝ የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ መሆኑ ከተረጋገጠ አካለ መጠን የመድረሱ ጉዲይ ግምት ውስጥ የሚገባበት ምክንያት የለም። ተጠሪዎች በወቅቱ ተማሪዎች የነበሩ መሆናቸው ሲታይም ትምህርታቸውን እየተማሩ በቀላለ ራሳቸውን የማስተዲደር አጋጣሚ ይኖራቸዋል ብል ለመደምደም ከነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሲታይ የማያስኬድ ነው። በመሆኑም ተጠሪዎች ሟች አባታቸው በመኪና ሲገጩ አስራ ስምንት ዓመት ስለሞላቸው ብቻ የጉዲት ካሣውን በቀለብ መልክ ሉያገኙ አይገባም በማለት አመልካች ያቀረበው ቅሬታ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ95/1/ እና ስለቀለብ ስለተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ውጪ በመሆኑ ይህ ችልት የሚቀበለው ሆኖ አላገኘውም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሣኔ በተጠሪዎች በኩል የቀረቡትን ክርክሮችንና ማስረጃዎችን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በሕጉ አተረጓጎምና አተገባበር ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ዐ1931 ሐምል 14 ቀን 1997 ዓ.ም. ተሰጥቶ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 3534ዐ ጥቅምት 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት ኀዲር ዐ4 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል፤ ይፃፍ።