No summary available.
ሚያዝያ 4 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች- የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት ተጠሪ፡-
ጉዲዩ ለሰበር ያቀረበው አመልካች የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሾች በመሆን ተክራክረዋል። አመልካች የተለያዩ አይነት ጤፍ የመሸጫ ዋጋ ከበፉቱ የጨመረ መሆኑ ከተነገራቸውና የፊክስ መልክት ከደረሳቸው በኋላ በፉት በነበረው ዋጋ የሽጡ በማስመሰልና ብር 16,818.10(አስራ ስድት ሺ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት ብር ከአስር ሣንቲም) ድርጅቱ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዱያጣ አድርገዋል በማለት አመለከቱ፣ አንደኛና ሶስተኛ ተጠሪዎች በሥር ቀርበው አልተከራከሩም ሁለተኛ፣ አራተኛ ተጠሪዎች በሥር ቀርበው ተከራክረዋል። ሁለተኛ ተጠሪ የእጅ በእጅ የጤፍ ሽያጭ እንዱከናውን ትእዛዝ እልሰጠሁም በደረሰኝ ላይም አልፈረምኩም የሥራ ድርሻዬ አይደለም በማለት መልስ ሰጥቷል። አራተኛ ተጠሪ በበኩላቸው በተከሳሽነት ቀርበው ከዚህ በፉት ከሳሼ ማለትም የአሁን አመልካች ብር 4,204.53(አራት ሺ ሁለት መቶ አራት ብር ከሐምሣ ሶስት ሣንቲም) በመክፈል ከሥራ አሰናብቶኝ ነበር። እኔ ለጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቤ እስከ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተከራክረን ወደ ሥራ የተመለስኩ ስለሆነና ከዚህ በፉት በጉዲዩ ተከራክረን ፍርድ ያገኘ ስለሆነ ሁለተኛ ጊዜ ክስ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት መልስ ሰጥታለች። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አራተኛ ተጠሪ ከዚህ በፉት በአሰሪና ሰራተኛ ችልት ተከራክሮ ተፈፀመ የተባለው ጥፊት የማያስጠይቃት መሆኑ ተረጋግጦ አራተኛ ተጠሪ ወደ ሥራ እንድትመለስ ተወስኗል። ይህ ውሣኔ እስከ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ድረስ ቀርቦ ፀንቷል ስለዚህ ተከሳሾችን የሚያስጠይቃቸው አይደለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ውሣኔው በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት ፀንቷል።
አመልካች ተጠሪዎች ለግል ጥቅማቸው ሲለ ከእያንዲንደ ኩንታል ብር 10.00/አስር ብር / ቀንሰው መሸጣቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አቅርበናል በአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት አራተኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) ጥፊት አልፈፀመችም ተብላ ወደ ሥራ እንድትመለስ መወሰኑ የፍትሐብሕር ኃላፉነትን የሚያስቀር አይደለም። ስለዚህ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት የሰበር አቤቱታውን አቅርቧል አንደኛ፣ ሁለተኛና አራተኛ ተጠሪ በየግላቸው መልስ ሰጥተዋል። የሰጡት መልስ ይዘትም ከጤፍ ሽያጭ ቀንሰው ለግል ጥቅማቸው ያዋለት ገንዘብ የላለ መሆኑንና ይህንንም የሚያስረዲ በቂ ማስረጃ ያላቸው በመሆኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም የሚል ነው። አመልካች የመልስ መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አራተኛ ተጠሪ አሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት ተከራክረው ከሥራ ለማሰናበት የሚያስችል ጥፊት አልፈፀሙም ተብል መወሰኑ ተጠሪዎች በድርጅቱ ላይ አድርሰዋል የተባለውን ኪሣራ እንዱከፍለ አመልካች ካቀረበው ክስ በኃላፉነት አይጠየቁም ብል ለመወሰን የሚያስችል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ እልባት ማገኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት ሰራተኛው ከሥራ የሚያሰናብት ጥፊት አልፈፀመም በማለት የሚሰጠው ውሣኔ አሰሪው ሰራተኛውን በፍትሐብሕር ክስ አቅርቦ ከመጠየቅ የሚገድብ እንዲልሆነና በፍትሐብሕር ሥነሥርአት ሕግ ቁጥር 5 ንኡስ አንቀጽ 1 መቃወሚያ ላሆን እንደማይችል ከዚህ በፉት የሰበር ችልት በመዝገብ ጥር 21 ቀን 2001 ዓ.ም አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት የሚወሰነው መሰረታዊ ጭብጥ ሰራተኛው በፍትሐብሕር ተጠያቂነትና ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም? የሚለው ሣይሆን አሰሪው ሰራተኛውን ከሥራ ለማሰናበት የሚያበቃ በቂ ምክንያት አለ ወይስ የለም? የሥራ ስንብቱ የሕጉን ሥርአት ተከትል የተፈፀመ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው። በያዝነው ጉዲይ አመልካች ተጠሪዎች ተሻሽል በተተመነው የጤፍ በመሸጫ ዋጋ በታች በመሸጣቸው ብር 16,818.10(አስራ ስድስት ሺ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት ብር ከአስር ሣንቲም) በድርጅቱ ላይ ጉድለት አድርሰዋል በማለት ክስ የቀረበ ሲሆን ክሱን ያስረደልኛል የሚላቸውን ማስረጃዎች አቅርቧል። ሁለተኛና አራተኛ ተጠሪ ለጉድለቱ ተጠያቂ አይደለንም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ይህንን ክርክር የሚደገፍ ማስረጃ ዝርዝር አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ደረሰ የሚለው የብር 16,818.10(አስራ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስምንት ብር ከአስር ሣንቲም) ኪሣራ በእርግጥ በድርጅት ላይ የደረሰ ጉዲት ነው ወይስ አይደለም? ጉድለቱ የደረሰ ነው የሚባል ከሆነ ተጠሪዎች በኃላፉነት ይጠየቃለ ወይም አይጠየቁም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመዘን ውሣኔ መስጠት ሲገባው አሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት የአራተኛ ተጠሪ ከሥራ መሰናበታቸው አላግባብ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ የፍትሐብሓሩን ክስ የሚያስቀር የመጨረሻ ውሣኔ አድርጏ በመውሰድ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበውን ክስና ማስረጃና ተጠሪዎች የሚያቀርቡትን መልስና ማስረጃ በመመርመር ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕግ 341/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የራሳቸው ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።