No summary available.
መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ደረጀ ቸርነት - ጠበቃ አቶ በሻዲ ገመቹ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሕይወት የኋላሸት - ጠበቃ አቶ ደሣለኝ ዓለሙ ክብረት ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት በመዝገብ የካቲት 20 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ የታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች በከሳሽነት ቀርቦ ንብረትነቱ የእሱ የሆነውና የሰላዲ ቁጥሩ 3-00055 አዋሣ የሆነ ኤኔትሬ የነዲጅ መጫኛ መኪና ሐምል 22 ቀን 1990 ዓ.ም ከተጠሪ የነዲጅ ማደያና ዱፖ ነዲጅ መራገፍ ላይ እያለ በዚህ ክርክር ተሣታፉ ያልሆነውና በሥር ፍርድ ቤት ሶስተኛ ተከሳሽ በሆነው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የሚባለው የተጠሪ ሰራተኛ በአስነሣው እሳት ምክንያት መኪናው ሙለ በሙለ የወደመ በመሆኑ የመኪናውን ዋጋ ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በመኪናው አገኝ የነበረውን ገቢ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ክስ እስከተመሰረተበት ጊዜ ድረስ በወር 15,00(አስራ አምስት ሺህ ብር) ሑሳብ 120,000( መቶ ሃያ ሺህ ብር) በሥር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ቶታል ሜር ዩዥ ኤስ ኤ፣ተጠሪና አቶ አስጨናቂ ኩምሣ በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። በሥር አንደኛ ተከሳሽ የነበረው ድርጅት አመልካች በእሱ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ምክንያት የላለው መሆኑን በማንሣት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በሁለተኛ ተከሳሽነት ቀርበው ሶስተኛው ተከሳሽ አስጨናቂ ኩምሣ ሰራተኛ ባለመሆኑ በኃላፉነት የምጠየቅበት ምክንያት የለም። እሳት ሉነሣ የቻለው የከሳሽ(አመልካች) ሰራተኞች በመኪናው ጋቢና በኩል ባስነሱት ምክንያት ነው ስለዚህ ለጉዲቱ አላፉነት የምጠየቅበት ምክንያት የለም በማለትና የመኪናውን ዋጋ ግምትና የመኪናውን ገቢ በመቃወም ተከራክረዋል። በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበረው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የሁለተኛ ተከሳሽ (የተጠሪ ድርጅት) ሰራተኛና ድርጅቱን በመላላክ የሚያገለግል መሆኑንና ጆሮውም የማይሰማ መሆኑን ገልፆ አደጋው በተከሰበት እለት እኔ በቦታው አልነበርኩም ፍ/ቤቱ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ ያቁምልኝ በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በሥር አንደኛ ተከሳሽ ተደርጏ የተጠቀሰው ድርጅት ሙለ በሙለ ከክሱ እንዱወጣ ወስኗል። የሥር ፍርድ ቤት እሣቱ የተነሳው በአቶ አስጨናቂ ኩምሣ ኃላፉነት የጏደለው ተግባር መሆኑን በበቂ ማስረጃ መረጋገጡን ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪ በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበረው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ ለፖሉስ በሰጠው የተከሳሽነት ቃልና ለፍርድ ቤት በሰጠው መልስ ማረጋገጡንና ሶስተኛው ተከሳሽ የሁለተኛ ተከሳሽ (የተጠሪ) ሰራተኛ መሆኑ በልላ ምስክር ቃል የተረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ በእሳት አደጋው ምክንያት ለደረሰው ጉዲት ተጠሪ ኃላፉነት አለባቸው። ሶስተኛ ተከሳሽም ኃላፉነት አለበት። ስለዚህ ተጠሪና ሶስተኛ ተከሳሽ ለጉዲቱ በአንድነትና በነጠላ በኃላፉነት ይጠየቃለ ብል ወስኗል የካሣውን መጠን በተመለከተ የመኪናው የገበያ ዋጋ ብር 170,000 (አንድ መቶ ሰባ ሺ ብር) እንደሚያወጣ አግባብ ካለው አካል ተገለጿል። የመኪናው ወርሃዊ ገቢ ብር 12,000 (አስራ ሁለት ሺ ብር ነው) ስለዚህ ተጠሪና ሶስተኛ ተከሳሽ የመኪናውን ዋጋ ብር 170,000(አንድ መቶ ሰባ ሺ ብር) እና የአስር ወር ገቢ ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺ ብር) እንዱከፍለ በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በወቅቱ ሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 42/1985 ድንጋጌዎች በመጥቀስና በተጠሪና በአቶ አሰጨናቂ ኩምሣ መካከል ያለው የሥራ ውል በጽሐፍ የተደረገ ስለመሆኑ ማስረጃ ያልቀረበ መሆኑን በመግለጽ አመልካች አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ መሆናቸውን ስላላስረደ ተጠሪ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት የለባቸውም በማለት ወስኗል። አመልካች በከፍተኛው ፍርድ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታብሓር ይግባኝ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በሥር ፍርድ ቤት ሶስተኛ ተከሳሽ አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ መሆኑን በማመን መልስ ሰጥቷል። ፖሉስ ባጣራው የወንጀል የምርመራ መዝገብ በሰጠው የተከሳሽነት ቃልም አረጋግጧል በልላ ማስረጃም ይኸን ፍሬ ጉዲይ አስረድተናል። ለተጠሪ ያቀረበችው ማስረጃ ሣይኖር ተጠሪ በአስጨናቂ ኩምሣ ስም የከፈላቸው የገቢ ግብር አለመኖሩንና ላልች ህጋዊ መሰረት የላላቸውን ምክንያቶች በማቅረብ ተጠሪ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት የለባቸውም ተብል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምኝ በማለት ያላመለከቱ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው የሥር ፍርድ ቤት የምስክሮችን ቃል በአግባቡ አልገለጹም። መስቀለኛ ጥያቄ ያልቀረበበትን ለፖሉስ የተሰጠ የተከሳሽነትና የምስክርነት ቃል ተጠቅሟል። ነዲጁ እስከ ታንከሩ ተገልብጦ እስኪያልቅ ድረስ ለሚደርስ ጉዲት ኃላፉነት ያለበት ጫኙ (አመልካች) ነው። አስጨናቂ ኩምሣ ተቀጣሪ ሰራተኛ አይደለም ስለዚህ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያደረጉት የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው
ተጠሪ አደጋው ያደረሰው በአመልካች ሰራተኞች ጥፊት ነው በማለት በሰበር ደረጃ ያቀረበው ክርክር ህጋዊ መሰረት አለው ወይስ የለም?
ተጠሪ በእሳት አደጋው ምክንያት ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ ናቸው ወይስ አይደለም?
የሚለ ጭብጦችን አግባብነት ያላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እልባት ማግኘት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ ተጠሪ የእሳት አደጋው የተነሣው በአመልካች ሰራተኛ ጥፊት ነው በማለት በሰበር ሰፉ ክርክር አቅርበዋል። የእሳት አደጋው የተከሰተው በሥር ፍርድ ቤት ሶስተኛ ተከሳሽ በነበረው በአቶ አስጨናቂ ኩምሣ ጥፊት ምክንያት መሆኑን በማረጋገጥ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወስኗል። የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ተጠሪን ከኃላፉነት ነፃ ናቸው በማለት የወሰነው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ አይደለም በማለት ነው። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የእሳት አደጋው በአቶ አሥጨናቂ ኩምሣ ጥፊት ነው የሚለውን የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ አልሻረውም። ስለሆነም መኪናውን ለውድመት የዲረገው እሳት አደጋ የተነሳው በአቶ አስጨናቂ ኩምሣ ጥፊት መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም አደጋው ያደረሰው በአቶ አስጨናቂ ኩምሣ ጥፊት ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ የሚነቀፍ አለመሆኑን “ላልቹን በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ የሚነቀፍ ሆኖ ስላልተገኘ ጸንቷል” በማለት በግልጽ ትእዛዝ ሰጥቷል። ስለሆነም የእሳት አደጋው በአቶ አስጨናቂ ኩምሣ ጥፊት መሆኑን ማስረጃ የመመዘንና ፍሬ ጉዲይ የማጣራት ሥልጣን ያላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥተውበት እያለ ተጠሪ አደጋውን ያደረሰው በአመልካች ሰራተኛ ጥፊት ነው በማለት ለሰበር አቤቱታ በሰጠው መልስ ያቀረበው ክርክር ለሰበር ችልት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 80 ንኡስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ከተሰጠው ሥልጣን ውጭ የቀረበ ሆኖ ስላገኘነው አልተቀበልነውም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ የእሳት አደጋው የተነሣው በአቶ አስጨናቂ ኩምሣ ጥፊት መሆኑ በስር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ተጠሪ በአመልካች መኪና ላይ በእሳት አደጋው ምክንያት ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለባቸው ወይስ የለባቸውም? የሚለው ጭብጥ የሚፈታው ተጠሪ ለአቶ አስጨናቂ ኩምሣ ጥፊት ምክንያት ለደሰረሰው ጉዲት ተጠያቂነት አለባቸው ወይስ የለባቸውም?
የሚለውን ጭብጥ በመመለስ ነው። አመልካች የጉዲቱን መንስኤና ምክንያት የደረሰውን የጉዲት መጠንና ተጠሪ ለጉዲቱ ኃላፉ መሆናቸውን የማስረዲት ሸክም እንዲለባቸው ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2141 ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። አመልካች ይህንን የማስረዲት ሸክማቸውን ለመወጣት ስለአደጋው በፖሉስ የተጣራው የምርመራ መዝገብ ቀርቦ እንዱታይላቸው አመልክተዋል።
አመልካች ተጠሪ ለደረሰው ጉዲት በኃላፉነት መጠየቅ አለባቸው በማለት የሚከራከሩት ለእሳት አደጋው መከሰት ጥፊት የፈፀሙት አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ ናቸው በማለት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ሶስተኛ ተከሳሽ የነበረው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ ለሥር ፍርድ ቤት በሰጡት መልስ በተጠሪ ድርጅት በተላላኪነት የሚያገለግል ሰራተኛ መሆኑን በመግለጽ መልስ የሰጠ ሲሆን ለፖሉስ ባደረገው ምርመራም አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ እንደሆነ በአቶ አስጨናቂ ኩምሣና በላልች ምስክሮች መረጋገጡን በሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገልጿል።
አመልካች አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ የነበረ መሆኑን ሉያስረዲለት የሚችል ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን በጥፊቱ የእሳት አደጋውን ያስነሳው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ ለሥር ፍርድ ቤት በፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 92 መሰረት አረጋግጦ በሰጠው መልስ የተጠሪ ሰራተኛ እንደሆነ በማመን መልስ ሰጥቷል። ተጠሪ አቶ አስጨናቂ ኩምሣ ሰራተኛቸው አለመሆኑንና በእለቱ በቦታው የተገኘው በድንገተኛ አጋጣሚ ወይም በልላ እሳቸው በማያውቁት ሁኔታ መሆኑን ለማስተባበል ያቀረቡት ማስረጃ የለም። አመልካች ጉዲቱን ያደረሰው ሰው የተጠሪ ሰራተኛ መሆኑንና ተጠሪም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2130 መሰረት ለጉዲቱ ኃላፉነት ያለባቸው መሆኑን ለማስረዲት የሚችል ማስረጃ በማቅረብ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2141 የተጣለበትን የማስረዲት ሸክሙን የተወጣ ሲሆን ተጠሪ የአመልካችን ማስረጃ የማስተባበልና የማፍረስ ግዳታቸውን አልተወጡም።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት በተጠሪና በአቶ አስጨናቂ ኩምሣ መካከል ያለው የሥር ውል በጽሐፍ የተደረገ መሆኑን ማስረጃ ያልቀረበ በመሆኑ አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ አይደለም በማለት ወስኗል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ በአንድ ሰውና በአሰሪው መካከል የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መኖሩን በጽሐፍ በተደረገ የሥራ ውል በማቅረብ ካልሆነ በስተቀር በላልች ማስረጃዎች ለማስረዲት እንደማይቻል በመግለጽ የሰጠው ውሣኔ ህጋዊ መሰረት የለውም። የሥር ውል ቋሚ ወይም ጊዜዊ ላሆን እንደሚችልና የሥራ ውለ በጽሐፍ ወይም በልላ አይነት ሁኔታ ሉፈጸም የሚችል መሆኑ አሰሪው የሥራ ውለን በጽሐፍ በማድረግ በአስር ቀናት ውስጥ የመስጠት ግዳታና ኃላፉነት እንዲለበት በወቅቱ ሥራ ላይ በነበረው አዋጅ ቁጥር 42/1985 አንቀጽ 6 እና አንቀጽ 7 የተደነገገ መሆኑን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠቅሷል።
ሆኖም የከፍተኛው ፍርድ ቤት መልስ ሣይሰጠው ያለፈው አንድ ቁልፍ ጥያቄ ያለ መሆኑን ተገንዝበናል። ይኸውም አሰሪው በሕግ የተጣለበትን ግዳታና ኃላፉነት ሣይወጣ አንድ ሰራተኛ በቃል ወይም በልላ አኳኋን በተደረገ የሥራ ውለ ከአስር ቀናት በላይ ለወራት ወይም ለአመታት ሲያሰራ ቢቆይ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለው ነው። አሰሪው በአዋጅ ቁጥር 42/1985 አንቀጽ 6 እና በአንቀጽ 7 የተጣለበትን ግዳታና ኃላፉነት ሣይወጣ መቅረቱ በሥራ ውለ ህጋዊነት ላይም ሆነ በሰራተኛው መብትና ጥቅም ላይ የሚያስከትለው አንዲችም ጉዲት የላለ መሆኑ በአዋጅ አንቀጽ 8 በግልጽ ተደንግጓል። ስለዚህ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 48/1985 አንቀጽ 7 የተደነገገውን ግዳታና ኃላፉነታቸውን አለመወጣታቸው የተሰጠሪ ሰራተኛ መሆኑን በመግለጽ የሚከራከረውና የተጠሪ ሰራተኛ መሆኑ በላልች ማስረጃዎች የተረጋገጠው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ ጥፊት ምክንያት ለደረሰው ጉዲት ከአላፉነት ነፃ የሚያደርጋቸው አይደለም። ስለሆነም በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የሥራ ውል መኖሩን በጽሐፍ የተደረገ የሥራ ውል ለማቅረብ ብቻ ሣይሆን በጽሐፍ የተደረገ የሥራ ውል በላለ ወይም ሉገኝ ባልቻለ ጊዜ ማናቸውንም ተዓማኒነት ያለውን ማስረጃ በማቅረብ ለማስረዲት የሚቻል በመሆኑና አመልካች ጉዲቱን ያደረሰው ሰው የተጠሪ ሰራተኛ መሆኑን በበቂ ማስረጃ አረጋግጦ እያለና ተጠሪ የአመልካችን ማስረጃ ሉያስተባብል የሚችል ማስረጃ ባላቀረበበት ሁኔታ በሕግ ያልተደነገገ መስፈርት አላግባብ በማውጣት የሥራ ውለ መደረጉን የሚያሣይ በጽሐፍ የተዘጋጀ የሥራ ውል አመልካች በማስረጃነት ያላቀረበ በመሆኑ አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ አይደለም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሕግ በግልጽ የሥራ ውልን ለማስረዲት ተቀባይነት የላቸውም ያልተባለ ማስረጃዎች የስራ ውል ለማስረዲት ተቀባይነት እንደላላቸው በመግለጽ የሰጠው ውሣኔ በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የአሰሪና የሰራተኛ ግንኙነት መኖሩን ስለማስረዲት የተደነገጉ ከላይ የተጠቀሱትን ደንቦችን የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲቱን ያደረሰው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የተጠሪ ሰራተኛ መሆኑን በሥር ፍርድ ቤት ሶስተኛ ተከሳሽ የሆነው አቶ አስጨናቂ ኩምሣም በግልጽ በማመን መልስ የሰጠ ሲሆን በላልች ማስረጃዎችም ተረጋግጧል።
ተጠሪ በአመልካች ማስረጃ የተረጋገጠውን ይህን ፍሬ ጉዲይ የሚያስተባብል ወይም ለማፍረስ የሚችል የተሻለ ማስረጃ አላቀረቡም። ተጠሪ ሰራተኛው ላደረሰው ጉዲት ኃላፉነት ያለበት መሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2130 ተደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የተጠሪ ሰራተኛ የሆነው አቶ አስጨናቂ ኩምሣ የሥራ ተግባሩን ሲያከናውን እሳቱ የተነሣ መሆኑን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2131/1/ እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2032/1/ መሰረት ያስረዲ ሲሆን ተጠሪ ይህንን ለማስተባበል ወይም ለማፍረስ የሚቻል ማስረጃ እንዲላቀረቡ የሥር ፍርድ ቤት አረጋግጦል። ስለዚህ አመልካች ለጉዲቱ ኃላፉ መባላቸው ሕጋዊ መሰረት ያለው ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥራ ውለ መኖሩን ለማረጋገጥና ለማስረዲት የሚቻለው በጽሐፍ የተደረገ የሥራ ውል በማቅረብ ነው የሚል የተሳሳተ የሕግ ተርጉም በመስጠት ተጠሪ ለጉዲቱ ኃላፉነት የለባቸውም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል።
ተጠሪ በአመልካች መኪና ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ ናቸው ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.