No summary available.
መጋቢት 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ዶ/ር ተስፊነሽ በላይ - ጠበቃ አቶ ይርሣው ጌትነት ቀረቡ ተጠሪ፡- አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ - ነገረፈጅ መኮንን ሽፈራው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ ያታየው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርቦ የመድን ሽፊን የሰጠሁት የሰላዲ ቁጥር 3-15680 የሆነውን መኪና ንብረትነቱ የተከሳሽ (የአመልካች) የሆነው የሰላዲ ቁጥር 2-4443 አ.አ የሆነው መኪና ጥቅምት 12 ቀን 1999 ዓ.ም በመግጨት ጉዲት አድርሶበታል። ጉዲቱ ያደረሰውም የተከሳሽን (አመልካችን) መኪና ያሽከረክር በነበረው ሰው ጥፊት ምክንያት መሆኑ በትራፉክ ሪፖርትና መርመራ የተረጋገጠ ነው። ከሳሽ (ተጠሪ) ባለበት የውል ግዳታ መሰረት ብር 116,735.49 (አንድ መቶ አስራ ሰድስት ሺ ሰባት መቶ ሰላሣ አምስት ብር ከአርባ ዘጠኝ ሣንቲም) ወጭ በማድረግ የደንበኛውን መኪና አስጠግኖ ያስረከበ ስለሆነ ይህንን ገንዘብ ከነወለደ እንዱከፍለ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርበው የእኔን መኪና ያሽከረክር የነበረው ሰው በወንጀል ተከስሶ ነፃ በመሆኑ ጉዲቱ የደረሰው የእኔን መኪና በሚያሽከረክረው አሽከርካሪ ጥፊት ሣይሆን የከሳሽን መኪና በሚያሽከረክረው አሽከርካሪ ጥፊት ነው። ጉዲቱ በሁለት ተሽከርካሪዎች ግጭት የተከሰተ በመሆኑና የእኔም መኪና ጉዲት ደርሶበት በንብ ኢንሹራንስ የተጠገነ በመሆኑ የየራሳችንን መቻል ይገባናል። ተጠሪ(ከሳሽ) ፏርፍርማ ሣይሰበሰብ በሞኤንኮ ኩባንያ ብቻ ጥገናው እንዱከናወን ያደረገ በመሆኑ በቂ ማስረጃ አላቀረቡም የትራፉክ ፖሉስ የምርመራ መዝገብ ቀርቦ ይታይልኝ በማለት የተከራከሩ ሲሆን ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያም በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ አለኝ የሚለውን ክርክር አቅርቧል።
የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ያቀረበውን የትራፉክ ፖሉስ የምርመራ ሪፖርት ከመረመረ በኋላ አመልካች የፖሉስ የምርመራ መዝገብ ይቅረብ ብለው ያቀረቡት ጥያቄ የምርመራ መዝገቡ ከቀረበው ሪፖርት የተለየ የሚያስረዲ ስለመሆኑ አልገለፁም ስለዚህ ክርክራቸው ተቀባይነት የለውም። የአመልካችን መኪና የሚያሽከረክረው ሹፋር በወንጀል ተከስሶ ነፃ መውጣቱ የፍትሐብሕር ኃላፉነትን የሚያስቀር አለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2149 በግልጽ ተደንግጓል። ጉዲቱ የደረሰው በአመልካች ሹፋር ጥፊት ምክንያት መሆኑ ስለተረጋገጠና አመልካች የመኪናው ባለቤት በመሆናቸው ለደረሰው ጉዲት በኃላፉነት ይጠየቃለ በማለት ከወሰነ በኋላ የካሣውን መጠን በተመለከተ አመልካች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር እንደዚሁም ላልች ወጭዎችን ይክፈለ፣ክስ ከቀረበበት ገንዘብ ውስጥ ጣልቃገቡ ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ብር 75,000/ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ይከፈል በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል። አመልካች ለዚህ ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የእኔ መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ሹፋር በወንጀል ተከስሶ ነፃ ሆኖ እያለ የወንጀል መዝገብ አስቀርቦ ሣይመለከት ኃላፉነት አለባችሁ ብል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ለመኪና መለዋወጫ አውጥቻለሁ በማለት ተጠሪ ያቀረበው ማስረጃ ታአማኒነት የላለው ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት ተቀብል መወሰኑ ተገቢ አይደለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት በርካታ የሕግና የፍሬ ጉዲይ ስህተት ፈጽሞ እያለ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሣያርም ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሶስት ገጽ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ ጉዲቱ የደረሰው የአመልካችን መኪና ያሽከረክር በነበረው ሹፋር ምክንያት መሆኑን የተሻለና ሚዛን የሚደፊ ማስረጃ በማቅረብ አስረድተናል። የፍርድ ቤት የወንጀል ውሣኔ በእኛ በኩል ያቀረበውን የትራፉክ ምርመራ ሪፖርት የሚያስተባብል አይደለም። በአጠቃላይ የማስረጃ አቀራረብ ስርአትን ተከትለው በስር ፍ/ቤትም ሆነ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያላቀረቡትን ማስረጃ የበታች ፍርድ ቤቶች እንዲለፈባቸው በመግለጽ በሰበር አመልካች የሚያቀርቡት ክርክር ህጋዊ መሰረት የላለው ነው። በማለት መልስ ሰጥቷል አመልካች በጽሐፍ የመልስ መልስ አቅርበዋል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመንው አመልካች የሥር ፍርድ ቤት ማስረጃ ሣያስቀርብና የእኔን መኪና የሚያሽከረክረው ሰው ከወንጀል ክስ ነፃ ሆኖ እያለ ለጉዲቱ ኃላፉነት አለብሽ ተብል መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረቡትን የመከራከሪያ ሐሳብ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ ምላሽ ማግኘት ያለባቸው ነጥቦች ሆኖ አግኝተናቸዋል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ በማስቀረብ አመልካች ተጠሪ ያቀረበባቸውን ክስ ለመከላከል በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 234 እና በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 223 ድንጋጌዎች መሰረት ያቀረቡትን የማስረጃ ዝርዝር ተመልክተናል። አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት የካቲት 19 ቀን 2000 ዓ.ም ባቀረቡት የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ የትራፉክ ፖሉስ የምርመራ መዝገብና አቃቤ ሕግ በቄራ ምድብ ችልት የወንጀል ክስ አቅርቦ የተከራከረበት የፍርድ ቤት መዝገብ ፍርድ ቤቱ በፍታብሓር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 145 መሰረት የጠየቁ መሆኑን በተራ ቁጥር 1 እና በተራ ቁጥር 2 ካቀረቡት የማስረጃ ዝርዝር ለመረዲት ችለናል። የሥር ፍርድ ቤት እነዚህን መዝገቦች አስቀርቦ ማየት ያላስፈለገበትን ምክንያት በውሣኔው በግልጽ አስፍሯል። አመልካች እንዱቀርብላቸው የጠየቁት የትራፉክ ፖሉስ የምርመራ መዝገብ በትራፉክ ፖሉስ የሚመለከተው ክፍል ተዘጋጅተው ከተላከው የትራፉክ ፖሉስ ምርመራ ውጤትና መግለጫ ከተገለፀው ፍሬ ጉዲይ ምን የተለየ ፍሬ ጉዲይ ሉያስረዲ እንደሚችል ባቀረቡት የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ አለመገለፁን እንዱሁም የወንጀል ችልት የአመልካች መኪና ሲያሽከረክር በነበረው ሰውና በዓቃቤ ሕግ መካከል ክርክር የተደረገበት መዝገብ አሽከርካሪው በወንጀል ተከስሶ ነፃ ከመሆኑ ውጭ ላላ የሚያስረዲው ፍሬ ነገር ያለ መሆኑን የማስረጃ ዝርዝር መግለጫው የማያሣይና በወንጀል ነፃ መሆን የፍትሐብሕር ተጠያቂነት እንደማያስቀር በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2149 የተደነገገ መሆኑን በመግለጽ ውሣኔ እንደሰጠ ለመገንዘብ ችለናል።
አመልካች አንድ ማስረጃ ቢቀርብ ምን አይነት ጭብጥ ሉያስረዲላቸው እንደሚገባ በፍትሐብሕር ሥነሥርአት ሕግ ቁጥር 223 እና በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 145/2/ ድንጋጌዎች መሰረት በመግለጽና በመዘርዘር የመጠየቅ ግዳታና ኃላፉነት አለባቸው። አመልካች መዝገቦቹ ቢቀርቡ ለሥር ፍርድ ቤት በማስረጃነት ከቀረበው የትራፉክ ፖሉስ የምርመራ ውጤት መግለጫ ሉያስረደ የሚችለት የተለየ ፍሬ ጉዲይ ስለመኖሩ ሣያረጋግጡና ሣይገልጹ እንደዚሁ በደፈናው መዝገቦቹ ቀርበው ይታዩልኝ በማለት በማስረጃ ዝርዝር መግለጫው ስለጠየቁ ብቻ የሥር ፍርድ ቤት በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 145 መሰረት መዝገቦቹን የማስቅረብ ግዳታና ኃላፉነት የለበትም። ፍርድ ቤቱ መዝገቦቹ እንዱቀርቡ ትእዛዝ የሚሰጠው ይቅረቡ የተባለው ማስረጃ ከክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ ጋር ያለውን አግባብነትና ማስረጃው ቢቀርብ ሉያረጋግጥ የሚችለው ፍሬ ጉዲይ በመጀመሪያ ማስረጃው ይቅረብልኝ የሚለው አካል በበቂ ሁኔታ ዘርዝሮና በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 145 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት አረጋግጦ ሲጠይቅ ነው። ከዚህ አንፃር አመልካች በፍትሐብሕር በሥነ- ሥርአት ሕግ ቁጥር 145/2/ ድንጋጌዎች መሰረት እንዱቀርቡ የጠየቋቸው ማስረጃዎች ምን አይነት ፍሬ ጉዲይ እና ጭብጥ ለማስረዲት እንደሚጠቅሙ ሣይገልጽና ሣያረጋግጡ የሥር ፍርድ ቤት ማስረጃዬን ሣያስቀርብ ወሰነብኝ በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የሕግ መሰረትና ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ የአመልካችን መኪና ያሽከረክር የነበረው ሹፋር በወንጀል ተከስሶ ነፃ መሆኑ አመልካች በፍትሐብሕር ተጠያቂነት ነፃ የሚያደርግ አይደለም። አመልካች መኪናቸውን ከሚያሽከረክረው ሹፋር ጥፊት ውጭ በሆነ መንገድ በልላ ሰው ንብረት ላይ ጉዲት ያደረሰ መሆኑ ቢረጋገጥ እንኳን የመኪናው ባለቤት በመሆናቸው ብቻ ለጉዲቱ ተጠያቂ እንደሚሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2081 ንኡስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። በያዝነው ጉዲይ አደጋው ያደረሰው የአመልካችን መኪና በሚያሽከረክረው ሹፋር ጥፊት መሆኑን በፍትሐብሕር ክርክር የቀረበውን ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አረጋግጠዋል። አመልካች የወንጀል ችልት የሰጠው ውሣኔ መኪናቸውን ያሽከረክር የነበረው ሰው ጥፊት የላለበት መሆኑ የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ (conclusive Evidence) ተደርጏ መወሰድ አለበት በማለት ያቀረቡት ክርክር በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2149 በወንጀል ነፃ መሆን የፍታብሓር ኃላፉነትን የሚያስቀር አይደለም በማለት ሕግ አውጭው በግልጽ የደነገገውን ድንጋጌ ያላገናዘበና የሕግ ድጋፍ የላለው ነው። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የክርክሩን ሥርአት በሚመሩበት ጊዜም ሆነ ለጉዲቱ ኃላፉ ያለባቸው አመልካች ናቸው ብለው በሰጡት ውሣኔ የፈፀሙት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ውሣኔያቻውን አጽንተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የካቲት 10 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.