No summary available.
ታህሣሥ 28 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አየለ አድማሱ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አጀቡ ሹሜ ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የጉዲት ካሳን የሚመለከት ነው። አመልካች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ የተጠሪ መኪና ገጭቶ የአካል ጉዲት ስላደረሰባቸው ጉዲት ካሳ ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ) እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። ተጠሪ ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ የጉዲት ካሳው መጠን የተጋነነ ነው፣አደጋው በአመልካች ላይ ቀሪ የአካል ጉዲት ለደረሰ በመሆኑና ለህክምና ያወጡት ወጪ ከግንዛቤ ሳይገባ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የተጠሪ መኪና አመልካችን ገጭቶ በአካላቸው ላይ 18% ጉዲት ማድረሱን ካረጋገጠ በኋላ አመልካች ከጉዲቱ በፉት ገቢ ያገኙ እንደነበር ስላላስረደ በአደጋው ምክንያት ያጡት የገንዘብ ጥቅም ስለላለ የሚከፈላቸው የጉዲት ካሳ አይኖርም በማለት የአመልካችን የካሳ ጥያቄ ውድቅ አድርጏታል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። ይህ ችልትም አመልካች ላይ የአካል ጉዲት መድረሱ ተረጋግጦ እያለ የጉዲት ካሳ ሉከፈላቸው አይገባም የተባለበትን የሕግ አግባብ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር አቅርበዋል። ችልቱም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተመለከትነው የተጠሪ መኪና አመልካችን ገጭቶ የአካል ጉዲት ያደረሰባቸው ስለመሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪም ቢሆኑ መኪናቸው አመልካች ላይ ጉዲት ማድረሱን አልካደም። አንድ ተሽከርካሪ በልላ ሰው ላይ ጉዲት አድርሶ ከተገኘ የተሽከርካሪው ባለቤት ለጉዲቱ አስተዋፆ ባይኖረውም እንኳን የመኪናው ባለቤት በመሆኑ ብቻ ለደረሰው ጉዲት አላፉነት እንደሚኖርበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2981/1/ ስር ተመልክቷል። በዚህ ምክንያት ተጠሪ ጥፊት ባይኖርባቸው እንኳን አመልካች ላይ ለደረሰው የአካል ጉዲት የአደጋው አድራሽ መኪና ባለቤት በመሆናቸው ብቻ የጉዲት ካሳ የመክፈል ሃላፉነት አለባቸው። የስር ፍ/ቤትም ተጠሪ ለጉዲቱ ኃላፉ መሆናቸውን ተቀብሎል። አከራካሪ የሆነው አመልካች የጉዲት ካሳ ሉከፈላቸው ይገባል አይገባም የሚለው ጉዲይ ነው። የስር ፍ/ቤት ምንም እንኳን አመልካች የአካል ጉዲት የደረሰባቸው ቢሆን ከጉዲቱ በፉት ገቢ ያገኙ እንደነበር ስላላረጋገጡ ያጡት የገንዘብ ጥቅም ስለላለ ካሳው ሉከፈላቸው አይገባም ብሎል። ይህ የፍ/ቤቱ ውሳኔ አንድ ሰው በደረሰበት አደጋ ምክንያት የአካል ጉዲት ቢደርስበት ካሳ ሉከፈለው የሚገባው ከአደጋው በፉት ገቢ የሚያገኝ መሆኑና ይህም ገቢው የተቋረጠ መሆኑን ካስረዲ ብቻ ነው ወደሚል መደምደሚያ የሚወስድ ነው። ይህም ድምዲሜ በዋናነት የሚያሳይው የታጣ የገንዘብ ጥቅም ከላለ በቀር ምንም አይነት የአካል ጉዲት ቢደርስ ካሳ ሉከፈል የማይገባው መሆኑን ነው። በመሆኑም ችልቱ የጉዲት ካሳ የሚከፈለው መቼ ነው? የሚለውን ጭብጥ መርምሯል።
በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 14 ሥር “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በህይወት የመኖር፣የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው” (ሰረዝ የተጨመረ) ተብል የተቀመጠ ሲሆን አንቀጽ 16 የአካል ደህንነት መብት ምን እንደሆነ ያብራራል። ማንኛውም ሰው በአካለ ላይ ጉዲት እንዲይደርስበት የመጠበቅ መብት እንዲለው የሃገሪቱ የበላይ ሕግ ያስገነዝባል። መንግስትም ሆነ ማንኛውም ሰው የላላውን ሰው የአካል ደህንነት የመጠበቅ የሕግ ግዳታ አለበት። ይህን ህግ በመተላለፍ በሰው አካል ላይ ጉዲት ማድረስ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለደረሰው የአካል ጉዲት ተጏጂው ካሳ የማግኘት መብት ይኖረዋል። በህገ-መንግስቱ የተቀመጠው ይህን የሰብአዊ መብት ከሚያረጋግጡ ዝርዝር ሕጏች ውስጥ በፍ/ሕጉ ውስጥ የጉዲት ካሳን አስመልክቶ የተቀመጡት ድንጋጌዎች ይገኙባቸዋል። በዚህም መሰረት አንድ ሰው በጥፊቱ በልላ ሰው ላይ ጉዲት ካደረሰ ላደረሰው ጉዲት አላፉ ሆኖ ካሳ ሉከፍል እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2028 አስቀምጧል። በመሆኑም በመርህ ደረጃ የጉዲት ካሳ ሉከፍል የሚገደደው በጥፊቱ ጉዲት ያደረሰ ሰው ሲሆን በአንዲንድ የተለያዩ ጉዲዮች ደግሞ አንድ ሰው ጥፊት ሳይኖርበትም ኃላፉ እንደሚሆን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2066 እና ተከታዮቹ መገንዘብ ይቻላል። ከእነዚህ ህጉ ለይቶ ካስቀመጣቸው ጉዲዮች አንደ የተሽከርካሪ ባለቤት ተሽከርካሪው ላደረሰው ጉዲት ጥፊት ሳይኖርበት አላፉ እንደሚሆን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2081/1/ ያመለክታል። በመሆኑም በልላ ሰው አካል ላይ ለደረሰ ጉዲት አላፉ የሆነ ሰው ለደረሰው ጉዲት ካሳ የመክፈል ግዳታ በፍ/ሕጉ ግዳታ ተጥልበታል። ከዚህ በመቀጠል ላታይ የሚገባው የካሳው መጠን ነው። ለጉዲቱ አላፉ የሆነ ሰው የሚከፍለው የካሳ መጠን ከጉዲቱ ጋር ተመዛዛኝ ላሆን እንደሚገባ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2090 እና 2091 ስር ተመልክቷል። ወደፉት ይደርሳል ተብል የሚገመት ጉዲት የተረጋገጠ ከሆነ እስኪፈፀም መጠበቅ ሳያስፈልግ ካሳው ሉከፈል እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2092 ይናገራል። በልላ በኩል ካሳ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ መመዘን አለበት ሲባል መታየት ያለበት በአጠቃላይ በተጏጂው ላይ ጉዲት በመድረሱ ምክንያት እንደሰው በአጠቃላይ የመስራት ኃይል ቅነሳ አንፃር እንጂ ከጉዲቱ በፉት ሲሰራው የነበረውን ስራ ላለመስራት ጉዲቱ ያስከተለው ልዩ ጫናና የቅነሳ መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት አለመሆኑን ለዚህም ምክንያት የሚሆነው እያንዲንደ የሰውነት ክፍል ስራ ለመስራት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ አንድ ሰው ለመኖር የተለያየ ፊይዲና ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ እንደሆነ ይህ የሰበር ችልት በመ/ቁ. 19338 ትርጉም ሰጥቶበታል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ላይ የደረሰው የአካል ጉዲት 18% ስለመሆኑ ተገንዘበናል። የስር ፍ/ቤት አመልካች ላይ ጉዲት መድረሱን ቢያረጋግጥም ከፍ ሲል እንደተገለፀው ከጉዲቱ በፉት ገቢ ያገኙ እንደነበር አላስረደም በሚል ካሳ ሉከፈላቸው አይገባም ብሎል። ነገር ግን ጉዲት መድረሱ በተጨባጭ እስከተረጋገጠ ድረስ ለተጏጂው ከደረሰበት ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ ሉከፈለው ይገባል። ምክንያቱም መታየት ያለበት ተጏጂው ከጉዲቱ በፉት ያገኘው ገቢ ሳይሆን በጉዲቱ ምክንያት ወደፉት በመስራት ችልት ላይ ሉያስከትል የሚችለው አለታዊ ተጽእኖ ነው። አመልካች ላይ የደረሰው አካል ጉዲት ሙለ ለሙለ የመስራትን ችልታቸውን ያሳጣ ነው ባይባልም በ18% በመቶ የመስራት ችልታቸውን የቀነሰ ስለመሆኑ በሕክምና ተረጋግጧል። በእርግጥ ለዚህ ጉዲት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ ለመወሰን አስቸጋሪ ቢሆንም የካሳውን መጠን በትክክል ለመወሰን ያልተቻለ እንደሆነ የካሳው መጠን በርትእ ሉወሰን እንደሚችል የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2102/1/ ያመለክታል። በመሆኑም አመልካች ላይ ጉዲት መድረሱና ጉዲቱም 18% የመስራት ችልታቸውን መቀነሱ ስለተረጋገጠ የካሳውን መጠን በትክክል ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳን በርእት መወሰን ሲቻል አመልካች ገቢ ያልነበራቸው በመሆኑ ብቻ ካሳ አይከፈላቸውን ተብል የተሰጠው ውሳኔ የጉዲት ካሳ ድንጋጌዎችን ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ ሚያዚያ 24 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 68949 ጥቅምት 28 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች ላይ 18% የአካል ጉዲት የደረሰባቸው በመሆኑ በርትእ ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍለ ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.