No summary available.
ጥቅምት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - አክሉለ ተስፊዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ገዛኸኝ መንግስቱ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በመዝገቡ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ ለንግድ የሚውለ እህልችን ይዞ የነበረው መጋዘን በመታሸጉ ምክንያት ደርሶአል የተባለውን ጉዲት(ኪሣራ) ለማስከፈል በሚል የቀረበውን ክስ የሚመለከት ነው። ክርክሩ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። በአመልካች ላይ አቅርቦት የነበረው ክስ የተለያዩ እህልችን ሲነግድበት የነበረው የንግድ ቤት መጋዘን ከሕግ ውጪ አሽጏ ሁከት የፈጠረበት መሆኑን፣በዚህ ምክንያትም ሁከቱ ይወገድለት ዘንድ በፍ/ቤት ክስ መመስረቱን፣አመልካች ለክሱ መልስ እንዱሰጥ ታዞ መቅረቡና ክርክር መደረጉን፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ሁከቱ ይወገድ ሲል በመወሰኑ መጋዘኑ መከፈቱን በአንድ በኩል ሲገልጽ፤በልላ በኩል ደግሞ የቀረበው ክስ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ መጋዘኑ ለአራት ወር ያህል ተዘግቶ በመቆየቱ ምክንያት በእህል ዋጋ ረገድ ደረሰ የተባለው ኪሣራ ብር 9,959(ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) እንደሆነ ያመለክታል። ተጠሪ የጠየቀውም ይኸው ብር 9,959(ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) ከወለድና የጠበቃ አበል ጋር እንዱከፈለው እንዱወሰንለት ሲሆን፣ፍ/ቤቱም በጥያቄው መሰረት ወስኖለታል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤትም ውሳኔውን አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሐምል 23 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረም ዘንድ አቤቱታ አቅርቦአል።
በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። በመቀጠልም ክርክሩን አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
ከላይ እንደተገለጸው ተጠሪ ከጉዲዩ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ክስ የመሰረተው ሁለት ጊዜ ነው። የመጀመሪያው ከሕግ ውጪ ተደረገ የተባለውን እሽግ እንዱነሳለት የሚጠይቅ ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ መጋዘኑ በመታሸጉ ምክንያት ደረሰ ያለውን ኪሣራ እንዱከፈል የሚጠይቅ ነው። የኪሣራው መጠን ያሰላው የእሕለን የመሸጫ ዋጋ ነው(ነበር) ያለውን መሰረት በማድረግ እንደሆነም በክሱ ተመልክቶአል። አመልካች በበኩለ በሁለተኛው ክስ የተጠየቀው ኪሣራ በመጀመሪያው ክስ ሉጠየቅ ይገባው የነበረ በመሆኑ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና ኪሣራው በእርግጥ ለመድረሱ ማስረጃ እልቀረበም የሚል የፍሬ ነገር ነጥብ በማንሳት ተከራክሮአል። ፍ/ቤቱ ሁለቱንም የመከራከሪያ ነጥቦች አልተቀበለም።
ክሱን ያስተናገደው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ እንዲየነው ተጠሪ በመጋዘኑ መታሸግ ምክንያት በእህለ ላይ የደረሰውን ብልሽት ወይም ኪሣራ የሚያሳይ ማስረጃ እንዲላቀረበ ፍ/ቤቱ ስለመገንዘቡ በውሳኔው ላይ በግልጽ አመልክቶአል። “… ከሣሽ ከተለየ የእህል ንግድ ላይ ያጣውን የገንዘብ መጠን አሟልቶ በዚህ ላይ መዘረዘሩ ግልጽ ነው። ነገር ግን በዚህ ረገድ ይህንን ያሕል ገቢ ለማግኘቱም ሆነ ለማጣራቱ የተመሰከረ ነገረ የለም። ይህንን የራሱን ገቢ ተከሣሽ በክርክሩ ላይ እንደተቃወመው የተመዘገበ የገቢ ግብር የተከፈለበት ለመሆኑ ማስረጃ የለም..” በማለትም በውሳኔ ሐተታው ላይ ተችቶአል። የደረሰበት መደምደሚያ ይህ እንደሆነ ከገለጸ በኋላም ነው ተጠሪ ካሣ(ኪሣራ) ይገባዋል በማለት ገንዘብ እንዱከፈል የወሰነው።
በበኩላችን እንደምናየው ፍ/ቤቱ በተጠሪ ላይ ኪሣራ ለመድረሱ ምንም አይነት ማረጋገጫ አላገኘም።
ይህንንም እንዲመነበት በውሳኔው ላይ አመልክቶአል። ገንዘቡ መከፈል አለበት ለማለት የቻለው በእርግጥም ኪሣራው ስለመድረሱ በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጦ ሳይሆን፣መጋዘኑ ታሽጏ ከቆየ ተጠሪ ያጣው ማስረጃ አረጋግጦ ሳይሆን፣መጋዘኑ ታሽጏ ከቆየ ተጠሪ ያጣው ነገር የለም ለማለት አይቻልም ከሚል ግምት በመነሳት እንደሆነ በውሳኔው ማጠቃለያ ላይ በግልጽ አመልክቶአል። ኪሣራ ሉከፈል የሚችለው ጉዲት ስለመድረሱ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2090 እና 2091 ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ግን የደረሰ ጉዲት ለመኖሩ በምንም አይነት መንገድ አልተረጋገጠም። በመሆኑም ክሱ ለሁለተኛ ጊዜ እንደቀረበ ይቆጠራል ከሚል መነሻ አመልካች አቀርቦት የነበረው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቢታለፍ እንኳ በክርክሩ ፍሬ ነገር ተገብቶ የደረሰ ጉዲት አለ ለማለት የሚያስችል የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ምክንያት ስለላለ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለት ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ለተጠሪ የሚከፍለው ኪሣራ የለም በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።