No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አጤነሽ አበበ - ጠ/ታረቀኝ ተፈራ ተጠሪ፡- አቶ ማንተጋፍቶት አጥላው - ጠ/ደመቀ ሰገዳ - ቀረቡ
ለተጠሪ ባለቤት ያከራዩዋቸውን ቤት ባለቤታቸው ሲሞቱ ተጠሪ ይዘው ኪራይ ስላልከፈለና ቤቱንም ለመመልቅ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን እንዱለቁና ኪራዩን እንዱከፍለ ያቀረቡት ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ነው ተብል ስለተወሰነ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበላ 04 ክልል የቤት ቁጥር 34 በሆነው ቤት ውስጥ ያለው ለከብት ቤትነት ይጠቀሙበት የነበረውን ቤት በወር 100.00(መቶ ብር) ለተጠሪ ባለቤት አከራይተው ቆይተው ባለቤታቸው በ1992 ዓ.ም ሲሞቱ ተጠሪ ኪራይ ለመክፈልም ሆነ ቤቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን እንዱለቁ ኪራይ የአንድ አመት ብር 1200.00(አንድ ሺህ ሁለት መቶ) እንዱከፍለ እንዱሁም ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ቤቱን እስከሚያስረክቡ ድረስ የቤቱን ኪራይ እንዱከፍለ ጠይቀዋል።
ተጠሪ ለቀረበባቸው ክስ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወማያ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ሲለ ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተጠሪ ቤቱን ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱን የያዙና ቤቱን በአመልካች ፈቃድ የያዙ ለመሆኑ አመልካች ስላሳዩ ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ውሳኔው ፀንቶባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው ለተጠሪ ሚስት ያከራዩትን የግል ቤታቸውን ተጠሪ እንዱያስረክቧቸው እንጂ ሁከት እንዱወገድላቸው ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ማለቱ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው። ችልቱም ግራ ቀኙን ከሚያከራክረው ጉዲይ አኳያ ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1149 በይርጋ ቀሪ ነው የመባለን አግባብነት ለመመርምር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪም ቀርበው አመልካች በክሳቸው ቤታቸውን በተጠሪ በኃይል የተያዘባቸው መሆኑን ገልፀው ክስ የመሰረቱ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ስህተት የላለበት መሆኑን በመግለፅና በፍሬ ጉዲዩ ላይ ያላቸውን ክርክር በመዘርዘር አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ የመሰረቱት ተጠሪ ቤቱን ባለቤታቸው ከአመልካች ጋር ባደረጉት የኪራይ ውል ሰበብ ይዘው ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ኪራዩን ከፍለው ቤቱን እንዱያስረክቧቸው ነው። ከአመልካች ክስ በግልፅ ማየት የሚቻለው ክሱ ባለሃብት የሆኑበትን ቤት ለማስለቀቅ የቀረበ ባለቤትነትን የመፊለም ክስ ነው።
ተጠሪ በመልሳቸው አመልካች በክሳቸው ተጠሪ ቤቱን በሃይል መያዛቸውን በመግለፃቸው ክሱ ሁከትን የሚመለከት ነው ሲለ ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ አመልካች ክስ የመሰረቱት ባለሃብት የሆኑበትን ቤት ለተጠሪ ባለቤት አከራይተው የነበረ ቢሆንም ተጠሪ በዚህ ሰበብ ይዘው አለቅም በማለታቸው ቤቱን እንዱለቁ እንጂ ይዞታዬን በሃይል አስለቅቀውኛል በሚል ያቀረቡት ክስ የለም። በሃይል ይዘዋል ማለታቸው ብቻ ክሱን የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያሰኘው አይደለም። ባለሃብት የሆነው ሰው መብት ሳይኖረው እጁ ካደረገው ሰው ወይም ከያዘው ሰው ላይ ሃብቱ ይገባኛል ሲል ለመፊለም እና ማናቸውንም የሃይል ተግባር ለመቃወም እንደሚችል ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 1206 መገንዘብ ይቻላል። የስር ፍ/ቤት ግን የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው ይዞታን የሚመለከተውን የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1149”ን” መሰረት አድርጎ ነው። ይህ ድንጋጌ ተፈፃሚ የሚሆነው ይዞታው በሃይል የተወሰደበት ወይም ሁከት የተፈጠረበት ሰው ለሚያቀርበው ክስ ነው። ይዞታና ባለቤትነት የሚመለከቱ ጉዲዮች የተለያዩ እንደመሆናቸው የሚሸፈኑት በተለያዩ የህግ ድንጋጌዎች ነው። በተያዘውም ጉዲይ አመልካች ክስ የመሰረቱት ባለቤትነትን የሚመለከት በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በይዞታ ድንጋጌዎች ጉዲዩን አይቶ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ሲል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው። በልላ በኩል ተጠሪ በዋናው ጉዲይ ላይ ዝርዝር ክርክር ያቀረቡ ቢሆንም ዋናው ጉዲይ በስር ፍ/ቤት ክርክር ተደርጎበት የተወሰነ ባለመሆኑ በአሁኑ ደረጃ የሚታይ አይደለም።
በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ታህሳስ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ብይን እንዱሁም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 24 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም ብለናል። በመሆኑም በፍሬ ጉዲዩ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት ጉዲዩን ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ራ/ታ
ሐምል 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ ወ/ሮ ገብርኤላ ኒካላ ቶማስ ናክሶ - ጠበቃ አስቴር አርአያ ቀረቡተጠሪ፣ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ሚካኤል ጌታቸው ቀረቡ
አመልካች ተጠሪ በአደራ ያዘ የሚለትን ቤታቸውን እንዱመልስላቸው ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በመባለ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ የአባታቸው ንብረት የነበረና በአራዲ ክ/ከተማ ቀበላ 10 ክልል ውስጥ የሚገኘው ፍቅና ምድር የሆነ የመኖሪያና የድርጅት ቤት አባታቸው ሲሞቱ ልጆቻቸው በአገር ውስጥ ባለመኖራቸው የቤቶቹን ቁልፍ በግሪክ ኤምባሲ እጅ ቆይቶ በመጨረሻ ተጠሪ ቤቱን ከነንብረቱ ወራሾች እስኪመጡ ከውጪ ጉዲይ ሚኒስቴር በአደራ ተረክቦ በማከራየት ላይ የሚገኝ በመሆኑና የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴርም ቤቱን ተጠሪ ተረክቦ ወራሾች ሲመጡ ቤቱን ባለበት ሁኔታ ለወራሾች እንዱያስረክብ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑና አመልካችም ወራሽነታቸውን አረጋግጠው ቢቀርቡም ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ቤቱን በቤቱ ውስጥ ከነበሩት ንብረቶች ጋር እንዱያስረክባቸው ጠይቀዋል። ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም አመልካች ቤቱን የሚመለከት የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ስላላቀረቡ የመክስስ መብት የላቸውም እንዱሁም ክሱ የቀረበው ክርክር የተነሳበትን ቤት ተጠሪ ከያዘው ከአስር አመት በኃላ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው የሚለ የመጀመሪያ መቃወሚያዎች አቅርቧል። ፍ/ቤቱ ቀደም ስል አመልካች ክስ ለማቅረብ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በማለት ክሱን ውድቅ ያደረገ ሲሆን አመልካች እስከ ፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ቀርበው ተከራክረው በቤቱ ላይ መብት ወይም በጥቅም ስላላቸው ፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራቀኙን አከራክሮ የመሰለውን እንዱወሰን ጉዲዩ ለስር ፍ/ቤት ተመልሷል። በዚህ መሰረት ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በድጋሚ ካየ በኃላ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1677/1/ መሰረት ግዳታዎች ከውል የተገኙ ባይሆኑም በውል ህግ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ስለሚሆኑና አመልካች በውርስ የሚገኝ ንብረት ያለአግባብ በተጠሪ ተይዞብኛል ብለው ያቀረቡት የመብት ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 መሰረት በአስር አመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ሲገባው ከ25 አመት በላይ ቆይተው ያቀረቡ በመሆኑ ጥያቄው በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡት ይግባኝም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ብይን ላይ ነው ። የአመልካች ዋነኛ ቅሬታ ተጠሪ ቤቱን የተረከበው ወራሾች እስከሚመጡ በአደራ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው።፡ ይህ ችልትም የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ነው የመባለን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። በዚህ መሰረት ችልቱ የግራቀኙን የቃል ክርክር ሰምቷል። ተጠሪ በክርክሩ የአመልካች አባት የሞቱት በ1973 ዓ.ም በመሆኑና አመልካች ክስ የመሰረቱት በ1998 ዓ.ም በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677/1/ እና 1845 መሰረት ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ በአግባቡ ነው ብሎል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው አመልካች ክስ የመሰረቱት የአባታቸውን ንብረት አባታቸው ሲሞቱ ወራሾቻቸው እስከሚመጡ ተጠሪ በአደራ ተረክቦ እያስተዲደረው የቆየ በመሆኑና አመልካች ወራሽነታቸው አረጋግጠው ስለቀረቡ ተጠሪ ቤቱን እንዱያስረክባቸው ነው። ስለሆነም የአመልካች ጥያቄ በይዘቱ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 999 “ን” መሰረት ያደረገ የወራሽነት ጥያቄ ሳይሆን ተጠሪ በአደራ ተረክቦ የሚያስተዲድረውን ቤት እንዱያስረክብ የሚጠይቅ ነው። በዚህም ምክንያት የአመልካች ጥያቄ መታየት የሚገባው አደራን በሚመለከቱ ድንጋጌዎች መሰረት ነው። በመሆኑም የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ መሆን አለመሆኑን ስለአደራ ከተመለከቱት የፍ/ብ/ሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ እንመለከታለን። አደራ ማለት አደራ ተቀባዩ የአደራ አስቀማጩን እቃ ተቀብል በአደራ ጠባቂነት እንዱያስቀምጥለት የሚገባ የውል ግዳታ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2779 ይናገራል። አደራ ተቀባዩም እቃውን ይዞ የሚጠብቅ እንጂ የእቃው ባለቤት ሆኖ የሚቆየው አደራ ሰጪው ነው /የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2781/1/። በልላ በኩል አደራ ተቀባዩ በአደራ የሚጠብቀውን እቃ መመለስ ስለሚገደድበት የጊዜ ገደብ ስንመለከት አደራ ተቀባዩ በአደራ የተቀበለውን እቃ የሚመልስበት የጊዜ ገደብ በውለ ተመልክቶ ከሆነ ይህ ጊዜ ሲያበቃ እቃውን መመለስ የሚገባው ሲሆን /የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2781/2/ ይመለከቷል/ በውለ ላይ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ከላለ ግን አደራ ሰጪው እንደጠየቀ ወዱያውኑ እቃው እንደሚመልስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2989/1/ ስር ተመልክቷል። ከዚህ የህጉ ድንጋጌ አደራ ተቀባዩ እቃውን የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ከላለው በቀር አደራ ሰጪው በአደራ እንዱቀመጥ የሰጠው እቃ ያለምንም የጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ እንዱመለስለት ለመጠየቅ እንደሚችል መረዲት ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች የሚከራከሩት ተጠሪ ቤቱን በአደራ የያዘው ወራሾች እስከሚመጡ በማለት ነው። ከዚህም ክርክር ተጠሪ በአደራ ተረከበ የተባለውን ቤት የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ተወስኖ አለመቀመጡን መረዲት የሚቻል ነው።
ተጠሪም የጊዜ ገደብ ተወስኖ ተቀምጧል በማለት ያቀረበው ክርክር የለም። ይህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ቤቱ እንዱመለስላቸው ይርጋ ሳያግዲቸው በማንኛውም ጊዜ መጠየቅ ይችላለ። በእርግጥ ተጠሪ በዚህ የሰበር ችልት በተደረገው የቃል ክርክር ቤቱን በአደራ መያዛችንን በስር ፍ/ቤት አላምንም በማለት ተከራክሯል። ይህ ችልትም ቢሆን የአመልካች ክስ አደራን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በይርጋ አይታገድም አለ እንጂ ተጠሪ ቤቱን በአደራ ይዟል ወደሚለው መደምደሚያ ላይ አልደረሰም። ተጠሪ ቤቱን አመልካች በክሳቸው እንደገለፁት በአደራ የያዘው ነው ወይስ አይደለም? ቤቱንስ ሉያስረክብ ይገደዲል? ወይስ አይገደድም? የሚለው ክርክር ወደፉት ፍ/ቤቱ የግራቀኙ ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የሚወሰነው ነው።
ሲጠቃለል የአመልካች ክስ ተጠሪ በአደራ የያዘውን ንብረት እንዱመልስላቸው ሆኖ ሳለ የስር ፍ/ቤት ይህንን የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ በአግባቡ ሳይረዲ ክሱ የወራሽነት ጥያቄን የሚመለከት ነው በማለት ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸውን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1677/1/ እና 1845 “ን” መሰረት በማድረግ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ሲል የሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 25 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 17 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም ብለናል። በመሆኑም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ቤቱን በአደራ የያዘው ነው? አይደለም? ቤቱንስ ሉያስረክብ ይገደዲል? አይገደድም? የሚለውን ጉዲይ የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን ነው ያለውን ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ም.አ
ሐምል 27 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ ወ/ሮ ሶፉያ ሁሴን - ጠ/አለወርቅ ደጀኔ ቀረቡተጠሪዎች፣ 1. የአራዲ ክ/ከተማ መሬት አስተዲደር - ነ/ፈጅ ሰልሞን ተመቸው --ቀረቡ 2. አቶ ገዛኸኝ ሀብቴ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የመተላለፉያ መንገድ የማግኘት ጥያቄ አፈፃፀም የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአመልካች ከሣሽነት ነው የዲኝነት ጥያቄያቸውም የመተላለፉያ መንገድ ስለጠበባቸው ለአስተዲደሩ አመልክተው ከሁለተኛ ተጠሪ 1.10 ሜትር ተቀንሶ መንገድ እንዱያገኙ በአስተዲደሩ ከተወሰነ በኃላ ባልታወቀ ምክንያት አፈፃፀሙ በአንደኛ ተጠሪ ስለታገደ እና ሁለተኛ ተጠሪም የፈረሰውን አጥር መልሶ እያሰራ ስለሆነ ሁከት ተወግድ በቀድሞ የአስተዲደሩ ውሣኔ መሰረት መንገደ እንዱከፈት እንዱወሰን የሚል ነው።
አንደኛ ተጠሪ ሥር ፍ/ቤት የሰጠው መልስ የአስተዲደሩ ውሣኔ አፈፃፀም በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ከሚያደርስው ጉዲት አንፃር ቴክኒካዊ መፍትሓ በአስተዲደሩ ባለሙያዎች ቀርቦ አመልካች ባለመስማማታቸው ሉፈጸም ያልቻለ መሆኑን ሲገልፅ በሁለተኛ ተጠሪ በኩል ሥር ፍ/ቤት የቀረበው መልስ ለሚፈርሰው አጥርና ቤት እንዱሁም ለሚቀንስበት ይዞታ አመልካች ካሣ እንዱከፍለ በአስተዲደሩ የተሰጠውን ውሣኔ ባለመፈፀማቸው አፈፃፀሙ እንዱታገድ መደረጉ በአግባቡ ነው ሲል ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአ/አ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1221 በተደነገገው መሰረት አመልካች /የሥር ከሣሽ/ በቂ መተላለፉያ ለማግኘት ለባለይዞታው ተገቢውን ማካካሻ መክፈል ሲገባቸው ይህንን ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መንገድ እንዱከፈትላቸው ማስገደድ አይችለም በማለት የዲኝነት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል።
የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እና የሰበር ሰሚ ችልት ይህንኑ ውሣኔ አፅንተዋል።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ሲሆን የአመልካች ጠበቃ ጰጉሜ 2 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት አቤቱታ የመተላለፉያ መንገደን አጠር ለማስገመት ለባለሙያ ሃምሣ ብር /5ዐ/ አመልካች መክፈላቸውን ገልፀው ከሁለተኛ ተጠሪ ይዞታ ላይ ለሚቀነሰው 1.10 ሜትር የአጥር ግምት ኪሣራ ለሁለተኛ ተጠሪ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን ጠቅሶ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ተሽሮ ሁለተኛ ተጠሪ አጥር እንዱያፈርስ እንዱወስን ጠይቋል።
ይህ ሰበር ችልትም የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ አመልካች የጉዲት ኪሣራ እከፍላለሁ እያለ የመተላለፉያ መንገድ መከልከላቸው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ተጠሪዎች ባለበት ለማጣራት ተጠሪዎችን አስቀርቧል። ነ/ፈጅ ስለአንደኛ ተጠሪ በሰጠው መልስ አመልካች ሥር ፍ/ቤት ላይ ማካካሻና የአጥር ግምት ለመክፈል ፈቃደኛ አልነበሩም ፍርድ ቤቶቹም ይህንኑ አረጋግጠዋል፤ በዚህ ሰበር ላይ የቀረበው አዱስ ክርክር ነው በማለት ኪሣራ ተወስኖ መዝገቡ እንዱዘጋ ጠይቋል ሁለተኛ ተጠሪ በበኩለ የመተላለፉያ መንገድ ለመክፈት በአመልካች በኩል እንዱፈፀም የቀረበውን መፍትሄ ባለመፈፀም ግዳታቸውን ሳይወጡ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም ሲል ተከራክሯል።
እኛም የግራቀኙን ክርክር እና ሕጉን በማገናዘብ መርምረናል። ከሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መረዲት የተቻለው አመልካች መንገድ እንዱሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ በአስተዲደሩ ተቀባይነት አግኝቶ በተጓዲኝ ደግሞ አመልካች ሉፈጽሙት የሚገባ ግዳታ በአስተዲደሩ በኩል የተወሰነ ስለመሆኑ ነው። በአስተዲደሩ የተወሰነው የኪሣራ ገንዘብ ለመክፈል አመልካች ፈቃደኛ መሆናቸውን በሰበር አቤቱታ የገለፁ ሲሆን በተጠሪዎች በኩል የቀረበው ክርክር አመልካች ፈቃደኛ እንዲልነበሩ በሥር ፍ/ቤት ተረጋግጧል የሚል ነው። በእርግጥም አመልካች በአስተዲደሩ የተወሰነውን ለመፈጸም ፈቃደኛ ያለመሆናቸው የሥር ፍ/ቤት በውሣኔው አረጋግጧል። አመልካች እዚህ ሰበር ችልት ላይ ያቀረቡት ክርክር በፍሬ ነገር ረገድ ሥር ፍ/ቤት ያልተረጋገጠ በመሆኑ በዚህ ደረጃ ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም። ስለሆነም አመልካች ግዳታቸውን ባልተወጡበት ሁኔታ የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔን መቃወማቸው በሕጉ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘንም።
የሥር ፍ/ቤት በውሣኔው በግልፅ ያመለከተው አመልካች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1221 መሰረት ተጠሪ ላይ ለሚደርሰው ጉዲት ተገቢውን ካሣ ሳይከፍለ ተጠሪ መንገድ እንዱሰጣቸው ሉያስገድደ እንደማይችለ ነው። ከላይ እንደተመለከተው አመልካች በአስተዲደሩ የተወሰነው የመካካሻ ግዳታ ሳይወጡ ተጠሪን ማስገደድ አይችለም የሚለው የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም።
በልላ በኩል አመልካች የሚፈልግባቸው ተነፃፃሪ ግዳታ በአስተዲደሩ ውሣኔ መሰረት ከፈፀሙ በሕጉ መሰረት የመተላለፉያ መንገድ የማግኘት መብታቸው ወደፉትም ሉጠይቁ አይችለም ተብል ውሣኔው የመጨረሻ ላሆን አይገባም ምክንያቱም አመልካች እዚህ ሰበር ላይ እያቀረቡ ያለው ክርክር ካሣ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸው እና በማንኛውም አካል ያለመጠየቃቸውን የሚያመለክት ሆኖ ስላገኘነው ነው።
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ አሁን ባለበት ሁኔታ እንዱፀና ብለን ይህ ውሣኔ ግን የአመልካችን መብት እስከመጨረሻው የሚያሳጣ ላሆን የሚገባ አይደለም ብለናል። በዚሁ መሰረት ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የአ/አ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ23/3/2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣ የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ በ12/06/2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ የሰበር ችልቱ በመ/ቁ 9816 የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
አመልካች በአስተዲደሩ ውሣኔ መሰረት ግዳታቸውን ከተወጡ በኃላ የመተላለፉያ መንገድ የማግኘት መብታቸውን ይህ ውሣኔ አይከለክልም ብለናል።
No topics extracted.